Translate

Monday, July 9, 2012

ብኩርናቸውን የሸጡ ኤሳዊያን


ከ ተስፋዬ  ዘነበ   ኖርዌይ (በርገን)                                                      05/07/2012
ሁሉን አውቃልሁ እኔ ያልኩት ብቻ ነው ትክክል ብፁህ ነኝ ብሎ ሃገርን በጭፍን  ግትርነት የሚመራ
መሪና ተከታዮቹ የሚያዩት እና የሚያሰተውሉት ወይም በማን አለብኝነት የሚሄዱበት መንገድ አገር
ከማፍረስ እና የዜጎችን ሰብአዊ መብት ከመጨፍለቁ በተጨማሪ ሃገርን እንደ ሃገር ማቆየት ተስኖአቸው
ብቻ ሳይሆን ሆን ብለው የሚከውኑት የቀን ተቀን ተግባራቸው ሆኗል፡፡ ዳሩ ግን እውነት በአደባባይ
ሲገለፅ እና ሲነገራቸው የውርደት ማቅ ለብሰው አንገታቸው እራሳቸውን መሸከም እሰኪያቅተው ድረስ
መጠውለጋቸው እማኝ ሳያሻን የወያኔ ዘረኛ ቡድን መሪ መለስ ዜናዊ    ጋዜጠኛ አበበ ገላው    በ
ኢትዮጵያችን ያለውን እውነታ ለአለም ህዝብ ካጋለጠ በሗላ በሞራልም በአካልም ኮስምኖ ማየታችን
የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ምንም እንኳን ስብእናቸውን የሸጡ፣ ለሆዳቸው ያደሩ እና ከሞያ ስነምግባር
ያፈነገጡ የስርዓቱ ደጋፊዎች የጋዜጠኛ አበበ ገላውን የጀግንነት ስራ ቢያጣጥሉም  በጌታቸው በመለስ
ላይ የደረሰውን ስነ ልቦናዊ ቀውስ ሊታደጉት አልቻሉም፡፡ በሃሳብ ደረጃ አንድም ቀን የተለየ ሃሳብ
ሳያቀርቡ ወይም ሳይቃወሙ መለስ ያለውን ብቻ እንደገደል ማሚቱ ሲያሰተጋቡ የከረሙ አፋሽ
አጎንባሽ የወያኔ ሹማምንትም አለቃቸው መለስ ላይ የደረሰው የመንፈስ ስብራት ወደነሱም ተጋብቶ
ሸብር ፈጥሮባቸዋል፡፡

ይህንን እኩይ ስርዓት ከስርዓቱ መሪዎች  በተጨማሪ በተለያየ የሞያ ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ ሰዎችም
አገር በማፍረስ እና የህዝባችንን  የመከራ  ቀንበር የመሸከሚያ እድሜውን ያረዘሙ የስርዓቱ ተከታዮች
ናቸው፡፡
ለዘመናት በድህነት የሚማቅቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ከለት ጉርሱ ከዓመት ልብሱ ቀንሶ ደህነቴን
ከጫንቃዬ ላይ ያወርዱልኛል ፣ጉስቁልናዬን ተረት ያደርጉልኛል ብሎ ሳይማር ያስተማራቸው ምሁራን
ተብዬዎች የህዝብ እና የሃገርን ጥቅም ከማስከበር ይልቅ የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ እና ከራሳቸው፣
ከቤተሰቦቻቸው ውጪ አሻግረው ስለ ህዝብ ፣ስለ ሃገር ማሰብ ተስኖዋቸው ይህንን አምባገነን ዘረኛ
ቡድን በአንቀልባ አዝለው የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያዊያንን የመከራ እና የግፍ ዘመን ሁለት አስርታት
አድርሰውታል፡፡
ነባር የወያኔን አባላት ተክተውም ሆነ ቀደም ሲል ተቀላቅለው፡ እራሳቸውን የህሊና ባርያ ያደረጉ ፣
እውቀታቸውን እና ችሎታቸውን እኩይ ለሆነ ተግባር የሚያውሉ ነፃ ያልወጡ ሹመኞች እንደ ጋሪ ፈረስ
መለስ በሚነዳቸው መንገድ ብቻ የሚነዱ ሃገር ለማፍረስና ለማውደም ተባባሪ ሆነዋል፡፡ እንዲሁም
መሃል ሰፋሪ ሆነው የህዝብን ሰላማዊ ትግል ለማደናቀፍ እና ለመበተን የዘረኛው ቡድን መጠቀሚያ
የሆኑ ለዘመናት ተሳስቦ፣ ተከባብሮ በአንድነት የኖረን ህዝብ በዘር በሃይማኖት ከፋፍለው የጌታቸውን
የስልጣን እድሜ ለማራዘም ከላይ እታች የሚዳክሩ በአፍቅሮተ ንዋይ ህሊናቸው ታውሮ ለዘረኛው
የወያኔ ቡድን መሳሪያ በመሆን ሃገር እና ህዝብን ያስነቡ ፣ህዝብ በፍርሃት ተሸብቦ በሰቀቀን እንዲኖር
የሚያደርጉ ሆድ አደሮች በተለያየ የሃገሪቱ ክፍል ማየት ብርቅ አይደለም ፡፡ለዚህ ነው ወላይታ ገጠር
ተገብቶ ስለመብት ማውራት ያቃተው ፣ ወለጋ አሶሳ ተወርዶ ሰለነፃነት ማውራት ያዳገተው ፣ አፋር
ዱብቲ ተጉዞ ስለ ፍትህ ማውራት ወንጀል የሆነው ፡ ሁሉም ጋር ሁሉም ጥግ ከህዝብ አብራክ የወጡ
ለሆዳቸው ያደሩ ስላሉ ነው የኛም ፍርሃት ተጨምሮ የህዝባችን የመከራ ዘመን የረዘመው፡፡
ህዝብ እንደ ህዝብ በአገሩ በነፃነትና በሰላም እንዳይኖር ከሚያደርጉት ሹመኞች በተጨማሪ ስርአቱ
የፈጠራቸው በግሉ ዘርፍ በተለይ በንግዱ የተሰማሩ የህዝብ እና የሃገር በደል የማይሰማቸው ብዙሃኑንጨፍልቀው ኪሳቸውን  በዚች ሃያ አንድ አመት የሞሉ ሀብት ንብረት ያፈሩ የታሪክ ተወቃሾች እጅግ
ብዙ ናቸው ፡፡
እሩቅ ማየት ተስኖአቸው ያለው አምባገነን ሰርአት የማቱ ሳላህ ዕድሜ ያለው ይመስል ከራሳቸው
አልፈው ለትውልድ የሚተርፍ ሃብትና ንብረት ያግበሰበሱ ፣በዛች ደሃ ሃገር እየኖሩ ሰርጋቸውን ሸራተን
የጫጉላ ጊዜያቸውን ዱባይና ታይላንድ ያደረጉ የስርሃቱ ተጠቃሚዎች ለነሱ የቆመው ስርዓት እንዳይነካ
ና እንዳይፈርስ የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡
ወያኔ የስነምግባር  እና የሞራል መሰረት የሆኑ ዕሴቶቻችንን በማርከስ ፣የነቀዘ ትውልድ ለማብቀል ቤተ
ዕመነቶቻችንን የነውረኞች እና የሌቦች ዋሻ   ያድርገው ገና በ እድሜው መጀመሪያ ነበር፡፡በተለይ የ
ኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት አንዷ ነች፡ ይህንን እኩይ ተግባር
ለማስፈፀም ዶክተር ጳውሎስ (አባ ጳውሎስ) ሐምሌ 5 ቀን 1984 ዓ. ም 5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያርክ ሆነው ከእምነቱ ስርአት እና ደንብ ውጪ    በአፋኙ አምባገነን ቡድን
ተሹመው ከተቀመጡብን    በሗላ እንሆ ላለፉት ሃያ አመታት    ከሃይማኖት አባትነታቸው ይልቅ
ወያኔያዊ ባህሬያቸው ሲስተዋል ይታያል፡፡ ለማሳያ ያህል ከሚጠረጠሩበት የሙስና ፣አመባገነንነት ፣
ሕገ-ቤተክርስትያን ጥሰት ወ.ዘ.ተ. . . .  ሁሉን ትተን  ማንም   ሰብአዊ ፍጡር  ሊያወግዝ  ሊኮንን
የሚገባውን  በሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም ንፁሃን  ዜጎች በአረመኔው መለስ ዜናዊ ትእዛዝ በአልሞ ተኳሾች
ግንባራቸውን እየተመቱ  ለህልፈተ ህይወት ሲዳረጉ  ካድሬው ፓትሪያርካችን  ይህንን ክፉ ስራ እንደ
ሃይማኖት አባትነት መቃወምም ሆነ ማውገዝ ሰዋዊም ይሁን አባታዊ ግዴታቸው ቢሆንም ይህንን
ለማድረግ ግን የሞራልም ሆነ የመንፈስ ብቃት አልነበራቸውም፡፡ከዚህም በፊት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ
ተማሪዎች በታጣቂዎች የደረሰባቸውን ጥቃት በመሸሽ ቅድስተ ማሪያም   ቤተ-ክርስቲያንን የሙጥኝ
ሲሉ ከለላ እንዳይሰጣቸው የተደረገው  በኝሁ  አባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና  ነበር፡፡ ብዙ ብዙ ማለት
ቢቻልም ዘረኛው እና አምባገነኑ የመለስ ቡድን  በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት  ላይ ካለው የመረረ
ጥላቻ በመነሳት የአገሪቱ  መገለጫ የሆኑ  ቅርስ እና ትውፊቶቻችን  ለማጥፋት  በታሪካዊው  የዋልድባ
ገዳም ላይ በልማት ስም የጀመረው፣ አለም በቃን ብለው የመነኑ መነኮሳትን  የማዋከብ እና የማፈናቀል
ስራ በካድሬው ፓትሪያርካችን ምንም ተቃውሞ  አልገጠመውም ፡፡
ለዚህ ግፈኛ ስርአት እድሜ መርዘም  ምክንያት  ህዝብ አጨብጭቦና  ከፍ አድርጎ ለዝና እና ለክብር
ያበቃቸው የኪነ-ጥበብ ሰወቻችን በጣት ከሚቆጠሩት በሰተቀር  የስተቀሩት የህዝብ ሀብትነታቸውን
እረስተው ኪነ-ጥበብን ንግድ  አድርገዋል፡፡ገሚሱ ገዳዩን እና አምባገነኑን ቡድን እያወደሰ፣ሌላው በራሱ
አለም ውስጥ እየዳከረ     የህዝቡን ብሶት እና አገራችን    በዚህ አደገኛ ስርአት እየጠፋች፣እየፈረሰች
መሆኗን እያየ እና እየሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ    ስለ ዳሌ፣ ባት እና ተረከዝ    እየፃፈ እና እያዜመ
ከስርአቱ ተጠቃሚዎች ጋር ዳንኪራ  ይረግጣል፡፡
በኔ አስተያየ    የኪነ-ጥበብ ሰወች    ድምፅ ለሌለው ህዝብ    ድምፅ ሆነው    የህዝቡን ማህበራዊ፣
ኤኮኖሚያዊ፣ ችግሮች    ኪነ-ጥበባዊ    ለዛ ሰጥትው እያዝናኑ ማሳወቅ፣እንዲሁም    ብሄራዊ ስሜቱን
የተቀማውን  ትውልድ  ወደ እራሱ ማንነት እንዲመለስ እና እራሱን፣ አገሩን፣ ታሪኩን እና የማንነት
መገለጫ    የሆኑ እሴቶቹን    ማሳወቅ፣ ትውልዱን    ማነፅ    የሞያውና የሞያተኛው    ግዴታ
ይመስለኛል፡፡
ሆኖም እየሆነ ያለው ይህ  አይደለም፡፡ አሉን የምንላቸው የኪነ-ጥበብ  ሰዎች አብዛኛዎቹ ብእራቸውን
ከወረቀት  የሚያገናኙት  ዕርዕሱ  ይለዋወጥ እንጂ  በፆታ ጉዳይ ላይ ብቻ ነው፡ አገር ፣ ህዝብ  ታሪክ
ለነሱ  ደንታቸው አይደለም ፡ አገር  በአውሬዎች  ተይዛ  እየቃተተች ፣ህዝብ  በአምባገነኖች  መዳፍላይ ወደቆ ፣ ፍትህ ሲጓደል ፣እውነት  ሲጠፋ እያዩ ብእራቸው  ሀቅን ለመፃፍ ነጥፎ በአንቺ እና በ
አንተ  ተወስነው ክብሩን ሞያ ያረክሳሉ ፡፡
እነኝሁ አርቲስት ምናምን እያሉ እርስ በእርስ የሚሞካሹ  ንፁሃን ዜጎች በጠራራ ፀሃይ  በታጣቂዎች
ሲረሸኑ ፣ስለ አንድነት፣  ስለ ዴሞክራሲ የፃፉ እና የታገሉ ወህኒ ሲወረወሩ ፣አገር ተቆረሶ ለባህድ
ሲሸጥ ፣  ምስኪኑ ገበሬ  ከቦታው ተፈናቅሎ ሲባረር ወ. ዘ. ተ. . . .አንዳችም  ያልተነፈሱ  የአገራችን
የኪነ-ጥበብ ባለሞያ ተብዬዎች  ባስረሽ  ምቺው እና  በፆታ ጉዳይ  ዙሪያ  ብቻ  የተሰራ  ስራቸው
ተቀዳ፣ ተባዛ የቅጂ መብት ይከበር ብለው    ሰልፍ ይወጣሉ ፡፡ በመሰረቱ የቅጂ መብት ይከበር
ከሚሉት አንዱ ነኝ ፡ ሆኖም ከላይ የዘረዘርኳቸው በአገር እና በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ልክ ያጣ
በደል ለምን የህዝብ ሀብት ነን  በሚሉት አርቲስት ተብዬዎች  አልተስተዋለም ?፡፡ በእርግጥ የህዝብ
ሃብት ከሆኑ  ስለምን አሁን ያለውን ሁኔታ ለመፃፍ ብእራቸው ቃተተ? ፣ሰለምን  የህዝብ ነን ካሉ
በሕዝብ እና በአገር ላይ የሚደርሰውን  ግፍና  በደል  አይቃወሙም ? ወይም በስራቸው  አያሳዩም?፡፡
የሚያሳዝነው አሁንም በባርነት ስር ነን ፣    አሁንም    ዜጎች በግፈኞች ይገደላሉ ፣ አሁንም    በሃያ
አንደኛው  ክፍለ  ዘመን  በየእስር ቤቱ  ብዙዎች  ስብእናቸው  እየተዋረደ እና  በዘራቸው  እየተሰደቡ
ይገረፋሉ ፣ ይደበደባሉ ፡፡ደግሞ  ለበደል  በደል  ብርቃችን ነው ? ፡ምን  እሩቅ ወሰዳችሁ  ምን ታሪክ
አስበደራችሁ እየኖራችሁ ያላችሁትን  ቀን ከሌትአይናችሁ ስር  የሚሆንውን  በስራችሁ  አታጋልጡም ?
፣ቀይ ስተት፣ ጤዛ ምናምን ምን  አሰባላችሁ፡ እሱንማ  ገዢዎቻችን  አሸነፍናችሁ ፣ አምበረከክናችሁ፣
ለማለት ዕርዕሰ እየለዋወጡ ኦፕሬሽን  እገሌ፣ አጋዚ ኦፕሬሽን፣ አሞራው ፣ሙሴ .እያሉ ያደነቁሩናል  ፡፡
በሌላ በኩል  ለወያኔ አምባገነን  ቡድን የ እግር እሳት የሆነው  በተለያየ የ አለም  ክፍል የሚኖረው
ኢትዮጵያዊ በግዞት ላለው እና ድምፁ  ላጣው ወገኑ  ድምፅ በመሆን  የጨካኙ ስርአት  ፊት አውራሪ
መለስ ዜናዊን  መውጫ መግቢያ  እያሳጣ በሄደበት ሁሉ  የውርደት ማቅ እያለበሰ አንገት  ማሰደፋቱ
የማይዋጥላቸው የስርዓቱ  አቀንቃኞች  የህዝቡን  አንድነት  ለመበተን እና  እንደ ሃገር  ቤቱ ሁሉ
በውጪ  የሚኖረውንም  ህዝብ  በነፃ  አገር ላይ  እየኖረ  በፍርሃት  እንዲሸማቀቅ  የማያደርጉት ጥረት
የለም ፡፡የሚደንቀው    በባእድ አገር    በነፃነት    እየኖሩ   የዴሞክራሲን    ትርጉም በተግባር    እያዩና
በሰርዓቱ    ያለ ገደብ    እየተጠቀሙ፣ በአንፃሩ ለህግ   የበላይነት    ፣ለኩልነት እና    ለዴሞክራሲያዊ
ስርአት ግንባታ  የሚደረገውን  ትግል  ሲቃወሙ  ይስተዋላሉ ፡፡ እንዴት  እነሱ  ያለገደብ  ያገኙትን
ዴሞክራሲያዊ   መብት  ለአገራቸው  እና  ለህዝባቸው  እንደሚሰስቱ  አይገባኝም ፡ ለነገሩ  < መቶ
አመት  ባህር ውስጥ የኖረ  ድንጋይ  ዋና  አይለምድም > እንዲሉ  ነፃ  አገር  ላይ ነፃነታቸውን  ያላወጁ
ድኩማን መሆን አለባቸው ፡፡
ማጠቃለያ አሁን ሁሉም  ነገር የመጀመሪያው  መጨረሻ ላይ ደርሷል ፡ ህዝብ ማን  ምን  እንደሆነ
ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ለውጥ   አምሮታል ፣ ለውጥ ሸቶታል  ይለውጣል ፣ ይለወጣልም ፡፡ይህ አፋኝ
ስርአት የመቃብር አፋፍ ላይ ነው፡፡ለዚህም ምልክቱ እንዳበደ ውሻ   አገሪቱን  ከዳር እዳር ማመሱ
ነው፡፡ ላለፉት ሃያ አንድ አመታት ህዝብን ስታስነቡ ፣ አገር ስትመዘብሩ  የኖራችሁ ፡ብኩርናችሁን
በመፍረክረክ ላይ ላለው አምባገነን ዘረኛ ቡድን ሸጣችሁ ስጋችሁንም ነብሳችሁንም ላረከሳችሁ
ኤሳዋዊያን ሳይረፍድባችሁ ለራሳችሁ ነፃነት ስትሉ የህዝቡን ትግል ተቀላቀሉ ፡፡ ሁላችንም    በዘር
በሃይማኖት  ሳንከፋፈል ፍትህ ለተራበው ፣ ነፃነት  ለተጠማ ወገናችን  እንድረስለት ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! ሞት ለወያኔ !       ለአስተያየቶ፦ ftih_lewegen@yahoo.com
http://www.ecadforum.com/Amharic/wp-content/uploads/2012/07/bekurnachehu.pdf

No comments:

Post a Comment