አልሀምዱሊላህ በሰላም ተፈተናል፡፡
ዛሬ ጠዋት 3፡30 ላይ ከሰፈር ከአቡበከር ጋር ሆነን ወደ ኮሚቴው ስብሰባ ስንሄድ ከወይራ ወደ ዘነበወርቅ ሰፈር ልንደርስ ስንቃረብ መንገድ ላይ ፒክአፕ መኪና መንገድ
ዳግም ትውልድህ የት ነው? ብለው ጠየቁ፡፡ ‹‹ጅማ ከተማ›› ስል መለስኩ፡፡የጅማውን ግጭት የት ሆነህ ነው ያስበጠበጥቀው? ሲሉ ጠየቁ፡፡ በንግግራቸው ሳቅሁ፡፡ ቆጣ ብለው ‹‹የብጥብጡ ጊዜ የት ነበርክ?›› ብለው ጠየቁኝ፡፡ ‹‹እዚሁ አዲስ አበባ››፡፡ የት ተማርክ? የት የት ሀገር ሄደሃል? ወዘተ ጠየቁ አከታትለው፡፡ ከዚያም ‹‹ስማ ከጸረ ሰላም ሃይሎች ጋር የምታደርገውን ሁሉንም እንቅስቃሴ መንግሥት ደርሶበታል፡፡ ዝም ሲልህ መንግስት የፈራህ እንዳይመስልህ፡፡ ከዘሬ ነገ ትታረም ይሆናል ብለን ታግሰን ጠብቀን ነበር፡፡›› ሲሉ ተናገሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ሳቅሁ፡፡ ተቆጡ፡፡ ‹‹እኛ ለስብሰባ አልያም እንድትናገር አይደለም፡፡ የመጨረሻ መስጠንቀቂያ ልንሰጥህ ነው፡፡ በየመስጊዱ በሰደቃ ሽፋን ሕዝቡን የምታነሳሳውን ታቆማለህ፡፡ ሕዝቡ ወክሎኛል ብለህ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ካላቆምክ ዋጋህን ታገኛለህ፡፡›› አሉ፡፡ ይህን ሁሉ ሲናገሩ እግሬን አነባብሬ ነበርና ተቆጡ፡፡ ‹‹እግርህን አውርድ›› አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ጣልቃ ገባሁና ‹‹መረጃ ካላችሁ ፍርድ ቤት ዉሰዱና ክስ መስርቱ፡፡ ምን ታስፈራራላችሁ? እንኳን ማስፈራት ለእምነታችን ሕይወት ለመስጠት ዝግጁ ነኝ፡፡ ማስራጃ ካላችሁ ያሻችሁን አድርጉ፡፡›› አልኩ፡፡ ለምን አልፈራም ብለው ነው መሰል ቆመው ቆጣ ብለው ‹‹ላንተ ፍርድ ቤት በመውሰድ ጊዜ አናባክንም፡፡ ዋጋህን እንሰጥሃለን፡፡ አንዲት ችግር ቢፈጠር የመጀመሪው ጥይት አንተ ላይ ነው የሚያርፈው፡፡ ትሰማ እንደሆን ስማ፡፡ መስጊድ እያደራጀህ ታስበጠብጣለህ፡፡›› ሲሉ ተናገሩ፡፡ ካዋጣችሁ ቀጥሉ-ስል ተናገርኩኝ፡፡ ‹‹መንግሥት አንተን ፈርቶ መሰለህ? አንተ ስለመጅሊስ ምርጫ ምን አገባህ? እንቅስቃሴህን አቁመህ እንደ ዜጋ አርፈህ የማትኖር ከሆነ የምናሳይህን እናሳይሃለን፡፡ ኮሚቴ ምናምን ትላለህ? ህገ ወጥ ናችሁ፡፡ ማን መረጣችሁ? ሕዝቡ መንግሥትን እንጂ እናንተን መች መረጠ? ታርፍ እንደሆን ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው!›› ብለው ጨርሰናል፡፡ ዳግም ‹‹ካዋጣችሁ ቀጥሉ›› አልኩ፡፡ ፖሊሶቹን ‹‹ጠሩና እቃውን ስጡትና ይሂድ›› ብለው ወጡ፡፡ እቃዬን ተቀብዬ 7፡30 ላይ ከዚያ ወጣሁ፡፡ ስወጣ አቡበከር ቀድሞኝ ወጥቶ ነበርና ከዚያ ሄድን፡፡ እርሱም እንደኔ ተመሳሳይ ሁኔታ ዉስጥ እንደነበረ ነገረኝ፡፡ የሁለታችንም ሂደት ተመሳሳይ ነበር፡፡ የዋህ ሰዎች! ሕጋዊውንና ሕገ መንግሥዊውን የሕዝበ ሙስሊሙን የመብት ማስከበር ሂደት በተራ ማስፈራት ሊያቆሙ ይሻሉን ? አልሀምዱሊላህ በሰላም ወጣን! ይቀጥላል…
No comments:
Post a Comment