July 14, 2012 | Filed underSlider Post,አማርኛ ዜናና መግለጫ | Posted by admin
አገራችን ኢትዮጵያንና ህዝቧን በመጥላት ተወዳዳሪ የሌለው መለስ ዜናዊ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለከፈበት የካንሰር በሽታ ምክንያት አእምሮውን ከሳተ ቦኋላ ለአፋጣኝ የህክምና እርዳታ በቻርተር አውሮፕላን ወደ ቤልጂዬም ብራስልስ መወሰዱን የብራስልስ ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ።
እንደ ምንጮቻችን መረጃ ሞት አፋፍ ላይ ያለውን መለስ ዜናዊን የጫነው አውሮፕላን ከአዲስ አበባ የወጣው ረቡዕ ሌሊት ሲሆን ብራስልስ ሆስፒታል የገባው በማግስቱ ሃሙስ ጠዋት እንደሆነና አውሮፕላን ማረፊያ ሲጠባበቀው የነበረው አምቦላንስ ወዲያውኑ ተቀብሎት ዘወትር ወደሚታከምበት የሴንት ሉክ ሆስፒታል አድርሶታል።
የግንቦት 7 ድምጽ የመለስ ዜናዊን መታመምና ለህክምና ወደብራስል ማቅናት ለመጀመሪያ ጊዜ የዘገበው ከ3 ወራት በፊት እንደፈረንጆች አቆጣጠር ባለፈው ሜይ ወር ውስጥ ሲሆን መረጃው ለህዝብ በተሰራጨ በሳምንት ጊዜ ውስጥ አሜሪካን አገር ተደርጎ በነበረው የ8ቱ ሃብታም አገሮች ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ስለነበር ህመሙ ቀላልና በህክምና እርዳታ የሚፈወስ መስሎ ታይቶ እንደነበር ይታወሳል።
በአፍቃሬ ወያኔና የጥቅም ተጋሪዎቹ ሥነልቦና ውስጥ በማንም ሃይል ሊደፈር የማይችል የጀግኖች ሁሉ አውራ አድርጎ የእራሱን ምስል ሲፈጥር የኖረው መለስ ዜናዊ በሰሜን አሜሪካው የጂ 8 ስብሰባ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ባደረሰበት አንገት የሚያስደፋ ተቃውሞ በህዝብ ዘንድ መሳቂያ እና መሳለቂያ ሆኖ ለሁለት ወራት ከሰነበተ በኋላ በእርሱ መዋረድ የደነገጡት አድናቂዎቹ ከደረሰባቸው የሞራል ኪሳራ ሊያገግሙ የሚችሉበትን አንድም ኦፊሴላዊ ንግግር ሳያሰማ ዳግም ወደማይመለስበት ዘላለማዊ እንቅልፍ እየተጓዘ የመሆኑ አጋጣሚ ብዙዎችን አስገርሞዓል።
ወያኔ ላለፉት 21 አመታት ሲፈጽማቸው የነበሩት ጸረ አገርና ጸረ ህዝብ ተግባሮች በሙሉ በዋናነት መለስ ዜናዊ የተመረዘበት የጥላቻና የበቀል ስሜት የወለዳቸው የበቀል እርምጃዎች እንደሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች ከህወሃት የወጡ አንጋፋ የድርጅቱ አባላት በተደጋጋሚ ሲናገሩት የኖሩት ሃቅ ነው። በዚህም ምክንያት በህወሃት ውስጥ ያሉ የትግራይ ብሄርተኞች ከላይ ሆኖ ያሽከረክራቸው የነበረው የዚህ ሰው ከጫንካቸው ላይ መወገድ በሚፈጥርላቸው ዕድል ተጠቅመው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ሂደት ለመፍጠር ተቃዋሚዎች እያደረጉ ያለውን ጥረት ሊደግፉና ከህዝብ ጋር የመታረቅ ዕድላቸውን እንደምርጫ 97 ሳያበላሹት እንዲጠቀሙበት አንዳንድ ለአመራሩ ቀረበታ ያላቸው ወገኖች ምክር መለገስ መጀመራቸው ይወራል።
ለግንቦት 7 ድምጽ የደረሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የመለስ ዜናዊ መጨረሻ በቀናት አለያም በወራት የተቆረጠ ሆኗል።
No comments:
Post a Comment