ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአቡነ ጳውሎስ የስልጣን ዘመን በጎንደር አደባባይ እየሱስ ህዝቡን በመቀስቀስ ግጭት አስነስተዋል ተብለው ለ12 አመታት በእስር የማቀቁት፣ አባ አመሀ እየሱስ አቡነ ጰውሎስ ከማረፋቸው ከ10 ቀናት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ አቡኑን ከፉኛ ተችተዋል።
አባ አምሀእየሱስ ከደርግ ጊዜ ጀምሮ ዋልድባ ገዳምን ሊደፍሩ በተነሱት ላይ ሁሉ የእግዚአብሄር ተአምራት ታይቷል። አባ አምሀ እየሱስ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 21 አመታት የሀይማኖት አባት ነበር ብለው እንደማያምኑ ገልጠዋል።
በዋልድባ ገዳም ነዋሪ የሆኑት አባ ገብረ እየሱስ በበኩላቸው አቡነ ጰውሎስ በህይወት ኖረው ንሰሀ ገብተው ቢሞቱ ኑሮ ጥሩ ይሆን እንደነበር ይገልጣሉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባለፉት 20 አመታት የመከራ ጊዜ ማሳለፉዋን አባ ገብረእየሱስ ይናገራሉ::
በጀርመን አገር የፍራንክፈርት መድሀኒአለም ቤ/ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ መዊ ቀሲስ ልሳነ ወርቅ በበኩላቸው አቡነ ጰውሎስ የቤተክርስቲያኑዋን ቀኖና ሽረው ቤተክርስቲያኑዋን ለሁለት መክፈላቸውን ፣ በታሪክ ያልታየ ውድመት መድረሱንም ይገልጻሉ ::
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምእመናንና የሀይማኖት አባቶች ቅርሶች እንዳይመዘበሩ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አባ ገብረየሱስ እና መላከ መቂ ልሳነ ወርቅ ይመክራሉ::
No comments:
Post a Comment