ሚኒስትር ደኤታው በዚሁ ወቅት እንዳለው በምግብ እጦት የሚሰቃዩት ዜጎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጻር 16 በመቶ አሻቅቧል።
የተዛባ ዝናብ፣ የበልግ ምርት መቀነስ፣ ችግሩ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች የመግዛት አቅም ማጣት በምትኩ በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።ይሁንና ሌሎች የሚኒስቴሩ ባለሙያዎች ግን ምክንያቶቹ እነዚህ ብቻ አይደሉም፣ በተለይም በሱማሌ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በየጊዜው የሚታዩ አለመረጋጋቶች በዋነኛ ምክንያትነት ሊጠቀሱ ይገባል ይላሉ።
እነዚህ በምግብ እጦት የሚሰቃዩ ወገኖች 41 ከመቶው በሱማሌ፣ 27 ከመቶ በኦሮሚያ፣ 10 ከመቶ በትግራይ፣ 8.1 ከመቶ በደቡብና 7.7 ከመቶው በአማራ ክልሎች የሚገኙ ናቸው።
የግብርና ሚኒስትሩ በቅርቡ በምግብ ሰብል እራሳችንን እንችላለን ሲል መግለጫ በሰጠ በአጭር ጊዜ በሚኒስትር ደኤታው እንዲህ ዓይነት ተቃራኒ መግለጫ መሰጠቱ የወያኔ ባለስልጣናት ሀገር ያወቀውን እውነት ለመሸፋፈን ምንያህል እንደሚዋሹና እርስ በእርሱ የሚጋጭ መግለጫ ያለ እፍረት እንደሚያወጡ አመላካች ነው።
No comments:
Post a Comment