ወያኔ ሽብርተኝነትን(terrorism) ሲያራምድ የታየዉ የመንግስት ስልጣን ከመጨበጡ በፊት ብቻ ሳይሆን፣ ከዚያም በኋላ ነበር፡፡ ወያኔ በጫካ ትግል ዉስጥ በነበረበት ጊዜ ጀምሮ ህዝብ በግዳጅ ወደ ጦር ግንባር እንዲቀላቀሉ፣ ባንኮች የመዝረፍ ፣ ድልድዮችን እና ተቋማትን በቦንብ ማፈራረስ፣ በግድያ ተግባር ተሰማርቶ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸዉን ታጋዮች በመግደል የአሸባሪ ቡድን ተግባር በማከናወን ይፈረጃል፡፡የትግራይ ህዝብን ከብቶቻቸዉን እና እህሎቻቸዉን ሲዘርፉ እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡
ወያኔ ስልጣን ከተቆጣጠረ ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ ሰላማዊ ሰዎችን በግልጽ በአደባባይ የመንግስት መኪና እና መሳሪያ በመጠቀም ሲገድል ታይቷል፡፡ ከእነዚህ ዉስጥ ደግሞ አንዱ ማሳያ በጠራራ ፀሐይ አሰፋ ማሩን አይነት ሰዉ መግደሉ ነዉ፡፡ ከዚህ በመለስ ደግሞ፣ በስበብ አስባቡ በየጊዜዉ የሚደበደበዉ እና የሚፈነከተዉ የፖለቲካ ተቀናቃኝ እና ነፃ ጋዜጠኛ ቁጥር እስካሁን ድረስ እየተበራከ ሲሄድ የሚታይ ነዉ፡፡ ይህንን የመሰለ ጦረኛ እና ሽብርተኛ(Terrorist) ድርጅት ባንድ ቀን ጀንበር ጸረ-ሽብርተኛ(Anti-Terrorist) ሚስዮናዊ ሁኖ ለመታየት ሲሞክር መታዘብ በጣም ያሳፍራል፡፡ወያኔን የመሰለ ድርጅት እና መሪዉ በዚህ አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ በቅንነት ቢነሱ እንኳን፣ በሰዉ ዘንድ ለመታመን ከፈለጉ፣ ስለሚጠቀሙባቸዉ ቃላቶች ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዉ ነበር፡፡ ወያኔ(መለስ ዜናዊ) ይህን አቋሙን አስመልክቶ ከምዕራብያዉያን የሚያሳዬት ቀረቤታ፣ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ አክብሮትን እንደሚያስገኝለት አስበዉ ከሆነም ተሳስተዋል፡፡
መለስ ዜናዊ ከሞሞታቸዉ በፊት በእሳቸዉ አፍ ዘወትር የምንሰማዉ አክራሪነት እና አሸባሪነት ነበር፡፡ ከአክብሮነት ይልቅ የመጨረሻዉን ትዝብት እንዳተረፈለት መናገር ይቻላል፡፡
ወያኔ በማንነቱ እና በታሪኩ ምክንያት እና ቴረሪዝምን ለማዉገዝ የሞራል ስልጣን የለዉም፡፡ ወያኔ ለስልጣን የበቃበትም ሆነ፣ ላለፉት 22 ዓመታት በስልጣን ኮርቻ ላይ ሊቆይ ከቻለባቸዉ ዋነኛ መሳሪያቸዉ መሀል አንዱ ሽብርተኝነት ነዉ፡፡
መንግስቱ ኋ/ ማርያም (ደርግ) በስልጣን ዘመኑ የነፃነት ታጋዮችን የሚባሉትን ሽፍታ፣ ወንበዴ፣ የእናት ጡት ነካሽ፣ ገንጣይ አስገንጣይ እያለ የስድብ ዐይነት ሲሰጣቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ እና የህዝቦቿ ጥላቶች ይዉደሙ!!!!!
(Keep Ethiopia)
our hero long Live for those hard work
ReplyDelete