ባለፉት ጊዜያት ተደርገው በነበረሩት ሁለት የኢድ ክብረ በዓሎች በሚሊዮን የሚቆጠር ሙስሊም በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በዙሪያው በሕብረት እና አንድነት ሆኖ የመንግስትን ጸረ እስልምና እንቅስቃሴ በተቃውሞ ትእይንት አማካኝነት ማውገዙ የሚታወቅ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞ ይካሄድብኛል ብሎ ስጋት የገባው መንግስት ይህን ስጋቱን ለመፍታት መፍትሄ ይሆነኛል ያለው ስታዲየሙን በራሱ ሰዎች መሙላት ነው፡፡ ለዚህም የሚረዳ መንግስት 20ሺ የሚሆኑ የመግቢያ ካርዶችን በመሳተም ላደራጃቸው መንግስታዊ ሃይማኖት ተከታይ ጥቂት ሰዎች ለማደል አስቧል፡፡
ሆኖም 20ሺ የሚሆኑ ሰዎችን በሚያስበው መልኩ ለማግኘት የሚቸገር በመሆኑ መንግስት የሌላ እምነት ተከታይ ጭምር ለሆኑ ደህንነት አባላት እና የፓርቲ ካድሬዎች የሚዘጋጀውን የመግቢያ ካርድ ለማደል ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በዚህም የኢድ ሰላቱ ዋና ማከናወኛ ቦታ የሆነው የስታዲየሙ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ሙስሊሙ እንዳይገባ በፌዴራል ፖሊስ አባላት ክልከላ በማድረግ ለማቀብ ታቅዷል፡፡ መንግስት ይህን በማድረግ የስታዲየሙ ውስጠኛ ቦታ ከሙስሊሙ ተቃውሞ የጸዳ እንዲሆንና ባለፉት ሁለት ዒዶች ሕዝቡ ንግግር እንዳያደርጉ ያቀባቸው የመንግስት እና የሕገ ወጥ መጅሊስ አመራሮች የሚሹትን ዲስኩር የሚያሰሙበት ሁኔታ ለመፍጠር ነው ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ዜጎች የእምነት ስርአታቸውን ለመፈጸምም ሆነ በጋራ ጸሎት ለማድረግ መሰባሰብ እንደሚችሉና እንደሚችሉና እገዳ እንደማይደረግባቸው ይገልጻል፡፡
No comments:
Post a Comment