ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
1. መግቢያ:
ካለፈው ሁለት አመት ግድም ጀምሮ “መንግሥት በዲናችን ጣልቃ አይግባብን” በሚል ሰፊ ማእቀፍ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እየተደረገ ያለው ትግል፤ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ደግሞ ሁለት አስርት አመታትን ያስቆጠረ ከቀኖናው ውጭ መንግሥት የቤተክርስቲያኑን መሪ አይምረጥብን በሚል በመሰረታዊ ሀሳቡ ከሙስሊሙ ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዳይ በተነሳ ውዝግብ ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ ያለችበት ሁኔታና በዚህም ምክንያት በመንግሥት የተገፋው “ስደተኛው ሲኖዶስ” በራሱ ላይ የደረሰውን ሁከት በመቃወም የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ተዳምረው ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ጤነኛ የሆነው የሀይማኖትና የፖለቲካ ግንኙነት ምንድን ነው? ወይንም ደግሞ የመንግሥትና የሀይማኖት ግንኙነት ምን መሆን አለበት?
የሚለውን ጥያቄ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የሀይማኖቱ ተከታዮች አልፎ ያጠቃላይ የፖለቲካ ማህበረሰቡ (የሀገሩ) ትልቅ የመወያያ አርዕስት እየሆነ ነው:: ይህ ጉዳይ ግን ጥቅል ከሆነ ያመለካከትና የንድፈ ሀሳብ ጥያቄ በተጨማሪ ጥልቅና አስቸኳይ የሆነ የተግባር ፖለቲካ ጥያቄም ነው ይዞ የመጣው::
No comments:
Post a Comment