የኢትዮጵያ የገዥዉ መንግስት፣የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ተቋማት፣ድርጅቶችና በአጠቃላይ ግለስቦች ኢትዮጵያ የሚያገለግሉ እንጂ ከኢትዮጵያ በላይ አይደሉም :: በኢትዮጵያ ሊጠቀሙና ሊጠናከሩ የሚችሉትም ለኢትዮጵያ ሲሰሩና ለኢትዮጵያ ሲቆሙ ብቻ ነዉ።
ኢትዮጵያን እያፈረሱ እንድትነካ ፣ እንድትጎዳ እየሰሩና እየተንቀሳቀሱ ለኢትዮጵያ ቆሜያለሁ ማለት አይቻልም።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነት፣ የመስመር ልዩነት፣ የአመለካከት ፣የአስተሳሰብና የአፈጻጸም ልዩነት ሊኖር ይችላል ቢኖርም አያስደንቅም :: የአመለካከት ልዩነት ያለባትንና ዲሞክራሲ የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለመገንባት ነዉ የምንመኘዉ የምንሰራዉም ነገር ግን የአመለካከትና ሌላም ሌላም ልዩነት ቢኖርም ኢትዮጵያን በመጠበቅ ፣በማክበርና በማስከበር ልዩነት ሊኖረን አይገባም:: እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን ከሆንን ማለት ነዉ።

ይኧዉ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተዳድረዉ ወያኔ የህዝብ መብት በመንቀፍ ፣ዘረኝነትን በማስፋፋት ፣ሃገርን በመከፋፈል ፣ጎሰኝነትን በማስተማር፣ አገር በመዝረፍ ፣አገርን በመሽጥ፣ ሰዉን ከሚኖርበት ቅዬ በማፈናቀል፣ በመቻቻል እንዳይኖር በማድረግ፣ ዘር ከዘር ጥላቻን ማስፈን፣ ቀጥሎበት ሃያ ሁለት ዓመታትን አስቆጠረ። እስከመቸ ይኧን ነገር ዝምብለን ማየት እንችላለን ::
የሚያሳዝነዉ ግን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ስም ኢትዮጵያን የሚጎዳና የሚነካ እንቅስቃሴ በአገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም እየተደረገ ነዉ:: ዘረኝነትን በማስፈን የሚታወቀዉ ወያኔ ዛሬ ለተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ፈተና እንዳይሆንባችሁ ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል :: ልዩነታችሁን አጥባችሁ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ አብራችሁ ሰርታችሁ ኢትዮጵያን አንድ ማድረግ እንጂ እንደ ወያኔ በዘር ተከፋፍላችሁ ብትሰሩ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ፣ አንድነት ስላልያዛችሁ ለእኛ ኢትዮጵያን ምን ትጠቅሙናላችሁ?
የተለያያ የተቋዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ልትኖሩ ትችላላችሁ ቁም ነገሩ ግን የኢትዮጵያን አንድነት ፣ዲሞክራሲ የሰፈነበት አገር ገንብቶ ብሔርን ሳያበላልጥ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ አስፍኖ መስራት ተቀዳሚ ተግባር ማድረግ አለባችሁ::
በትግል ላይ ያላችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች ተጠናክራችሁና በርትታችሁ ከሌላዉ የትግል የፖለቲካ ድርጅት ጋር አብራችሁ ሰረታችሁ ልዩነታችሁን አስወግዳችሁ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በመስራት አምባገነኑን የወያኔ መንግስት ለመጣል ከሕዝብ ጋር ሆናችሁ መስራት ይጠበቅባቸዋል ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ይጠቅማልም ይደግፋልም ነጻነት የሚሻ ሕዝብ ከዚህ በላይ መስዋትነት ይከፈላልና የአገርን ጥቅምና ኢትዮጵያዊነት መንፈስን የሚያስቀድም ተቃዋሚ ይደግፋል ብቻ ሳይሆን ሊጠናከርና ሊበረታታም ይገባዋል::
በሰለጠኑ አገሮች ጠንካራ የመንግስትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አሉ የፈለገዉ ልዩነት ቢኖርም አገርን አይነኩም አገርን አትንኩ አትከፋፍሉ በሚል መፈክር ሁሉም ወገኖች ይስማማሉ::
ኢትዮጵያን አትከፋፍሉ አትንኩ የሚለዉ አባባል የወያኔ መንግስት ብቻ አይደለም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሆናችሁ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የማታምኑ በአንድነት በእኩልነት የማታምኑ ዘረኝነት የምታራምዱ ካላችሁ አሁንም እንላለን ኢትዮጵያን አትንኩ አትከፋፍሉ!!
ለግል ጥቅምና ለግል ክብር ለስልጣን ቅድሚያ እየሰጡ የአገርን ጥቅም የሚዘነጉ የሚረግጡ ሰዎችንም እያስተዋልን ነን በተቀመጡበት የስልጣን ወንበር ኢትዮጵያን ለማጠናከር ሳይሆን ኢትዮጵያን ለመዝረፍ( ለመቦርቦር) ሲጠቀሙበት እያስተዋልን ነን እነሱንም ኢትዮጵያን አትንኳት እንላለን::
ከሰብኣዊ

No comments:
Post a Comment