Translate

Sunday, August 18, 2013

አሁን በደረሰን ዜና ድምፃዊ ኢዮብ መኰንን አረፈ

ድምፃዊ ኢዮብ መኰንን ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ባደረበት ድንገተኛ ሕመም ራሱን ስቶ በሕክምና ላይ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የተገለጸው ኢዮብ የሕመሙ መንስዔ ስትሮክ መሆኑ ታውቋል፡፡
የቅርብ ጓደኞቹ ድምፃዊው ይህ ነው የሚባል ሕመም እንዳልነበረበትና ታሞ እንደማያውቅ ገልጸው፣ ባለፈው እሑድ ድንገት እጁ ላይ በተሰማው ስሜት ምክንያት ሐያት ሆስፒታል ለመታየት ቢሄድም ሙሉ ጤነኛ እንደነበር ተነግሮታል፡፡
ባለፈው ማክሰኞ ብስክሌት እየነዳ ልጁን ከትምህርት ቤት አስመዝግቦ ሲመለስ ቤቱ በር ላይ ተዝለፍልፎ በመውደቁ፣ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ገብቶ እስካሁን ድረስ ራሱን ስቶ እንደሚገኝ ተረጋግጧል፡፡

ወደ ኬንያ ሄዶ እንዲታከም ለማድረግ የኢዮብ ወዳጆች ኮሚቴ አዋቅረው ገንዘብ አሰባስበውለታል፡፡ በአገር ውስጥ የአውሮፕላን አምቡላንስ ባለመኖሩ ምክንያትም በኬንያ ከሚገኝ የግል ኩባንያ ጋር በ25,000 ዶላር ወስዶ ለማሳከም ስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል፡፡
ለሕክምናው የሚያስፈልገው ወጪ ከጓደኞቹና ከጥበብ ማኅበረሰቡ እየተሰባሰበ ሲሆን፣ ባለፈው ዓርብ ሐኪሞቹ እስከሚፈርሙ ድረስ እየተጠበቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በከተማው ውስጥ አሉ የሚባሉ ኒውሮሎጂስቶችና ሌሎች የሕክምና ባለሙያዎችም እየመረመሩት ነበር፡፡
በማሽን እየተረዳ የሚተነፍሰው ኢዮብ እስካሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በግልጽ አልታወቀም፡፡ በጭጋጋማና ብርዳማዎቹ ቀናት አድናቂዎቹ፣ ዘመዶቹና ወዳጆቹ ስለጤንነቱ እየጸለዩና እስኪነቃም እየተጠባበቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በፌስቡክ ድረ ገጽ ላይ ‹‹ለኢዮብ መኮንን እንጸልይ›› የሚል ገጽ የተፈጠረለት በመሆኑ፣ በርካቶች መልካም ምኞታቸውንና ጸሎታቸውን ለድምፃዊው እያስተላለፉ ነው፡፡
ታዋቂው ሙዚቀኛ ኢዮብ ሬጌን በተለየ መልኩ በመዝፈን የራሱን አሻራ ማሳረፍ የቻለ ነው፡፡ ‹‹እንደቃል›› በሚለው አልበሙ ተወዳጅነትና ተደማጭነትም ማግኘት ችሏል፡፡ በመድረክ አያያዙና በመሳጭ ግጥሞቹ የብዙዎችን ልብ ማሸነፍ እንደቻለም ይነገርለታል፡፡
ጅጅጋ ከተማ ውስጥ የተወለደው የ37 ዓመቱ ኢዮብ፣ የሙዚቃው ተፅዕኖ ከዝነኛው ድምፃዊ አሊ ቢራና ከቦብ ማርሌ እንዳረፈበት መናገሩ ይታወሳል፡፡
አሁን በደረሰን ዜና  ኢዮብ መኰንን በ ማረፉን ሰምተናል ለቤተሰቡ መፅናናትን እንመኛለን
ethiopian reporter

No comments:

Post a Comment