Translate

Saturday, August 31, 2013

መቶ የሚሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወዳልታወቀ ቦታ ተወሰዱ!

998402_581787228530546_531722766_nመቶ የሚሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወዳልታወቀ ቦታ ተወሰዱ!
አክራሪነት በጣም ሲያድግ ሲያድግ ሲያድግ አሸባሪ ደረጃ ይደርሳል ተብሎ ይሰጋል፡፡ አሸባሪስ ምን ያደርጋል… አሸባሪማ እገታ ይፈፅማል፡፡ በሆነው ባልሆነው፤ ህፃን፣ አዋቂ፣ ወንድ፣ ሴት ሳይለይ ይገድላል፡፡  እኔ ያልኩት ካልሆነ ሌላው ያለው በሙሉ ነውር ነው ብሎ ይደመድማል፡፡ ስለዚህ አክራሪነት እጅግ የከፋ አደጋ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ አክራሪነትን እቃወማለሁ፡፡ አዲሳባ ብሆን ኖሮ አክራሪነትን በሚቃወመው ሰልፍ ላይ መሳተፌ አይቀርም ነበር፡፡ (ለራሴ ሰላማዊ ሰልፍ እወዳለሁ…)
አሁን በሰማሁት ዜና መቶ የሚደርሱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መንግስት አግቶ ወዳልታወቀ ቦታ ወስዷቸዋል፡፡ ታድያ ከዚህ የበለጠ አክራሪነት ከዚህ የበለጠ ሽብርስ ከየት ይመጣል፡፡ አዎ በነገው ሰልፍ አክራሪነት በትክክል መወገዝ አለበት!!!
ኢህአዴግ አክራሪነት ይቁም!!!

Thursday, August 29, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ላይ ተቃውሞ አቀረበ

ፓርቲው ከ33ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር ተለያየ

yiliqal


በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. የመጀመሪያውን የተቃውሞ ሠልፍ ያካሄደው ሰማያዊ ፓርቲ፣ በመጪው እሑድ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተዘጋጀው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ተቃውሞ አቀረበ፡፡

የእኛ “መንግስት” (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

Journalist Temasegan Dasaleg
እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!

የሕወሐት ባለስልጣናት የአሜሪካ ቆይታ፤ የከዱ አሉ

ከኢየሩሳሌም አርአያ

በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” የሚለው ዋናው ግብ እንደነበር አስረድተዋል።

Tuesday, August 27, 2013

ተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?

bbbተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?
አብዲሳ የብዙ ጊዜ ወዳጄ ነበር፡፡ በየገጠሩ እየዞርን በርካታ ስራ አብረን ሰርተናል፡፡ የዋህነቱ እጅግ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ በየክልሉ ስንዞር አበሉን የሚጨርሰው “ቸገረኝ” ላለው ሁላ መበስጠት እንደነበር አብረነው የሰራ ሁላ እርሱን የምንለይበት ባህሪው ነው፡፡ ይሄ ልጅ በአንዱ ቀን ለስራ ልንሄድ የተቀጣጠርንበት ቦታ ሆነን ስንጠብቀው ስንጠብቀው ሳይመጣ ቀረ… ስልኩን ብንደውልልት አይሰራም፡፡ ካለንበት እየተንቆራጠጥን… ወደ ሶስት ሰዓት ድረስ ዘግይተን ጠበቅነው የውሃ ሸታ ሆነብን… ምን ሆነ ብለን እየተጨነቅን እንጀራ ነውና ጉዟችንን ቀጠልን…
አብረን ስንጓዝ ከነበርነው መካከል አብዲሳን በቅጡ የምናውቀው ሰዎች “ይሄኔ አንድ የታመ ሰው አጋጥሞት ሆስፒታል ሳላደርስ አልሄድም ብሎ ነው…” ….ወይ ደግሞ “…አንዱ ገንዘብ ተቸግሮ አጋጥሞት  ምንም ሳያስቀር ገንዘቡን ሰጥቶ ወደ እኛ መምጫ ራሱ ተቸግሮ ይሆናል …” ካልሆነ ግን “…ዘራፊዎች አግኝተው ጉድ አድርገውት ሊሆን ይችላል…. እያልን መገመታችንን ተያያዝነው…
ግምታችን ሁሉ ትክክል አልነበረም፡፡

ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በህንዳዊ ፕሮፌሰር ሲማሩ ነበር(ተመስገን ደሳለኝ)

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

Sunday, August 25, 2013

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል (ኢየሩሳሌም አርአያ)

ከኢየሩሳሌም አርአያ

Azeb Mesfin, the wife of Meles Zenawiለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ ሳይሆን ስብሃት ነጋ ባቀነባበሩት ጣልቃ ገብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል። በኤፈርት የተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች አዜብ በመባረራቸው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ አያይዘውም ደስታቸውን በስብሰባ ጭምር ከመግለፅ ባለፈ፥ « አዜብ ከኤፈርት ጀምሮ ለፈፀሟቸው የሙስና ወንጀሎች በሕግ መጠየቅ አለባቸው» በማለት አቋም እስከ መያዝ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

Saturday, August 24, 2013

የዕርቁ ካርድ እንዳይባክን!! የተደበቃችሁ ተገለጡ!!

(ርዕሰ አንቀጽ)

final move

“አገራችንን በእርቅ እንታደጋት” ዶ/ር ተጋ

"ዋስትና የናፈቃቸው ባለስልጣናት አሉ"

faces-of-ethiopia
የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ከየትኛውም ዜጋ በላይ ዋስትና እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ። በአገራቸው ጉዳይ ላይ በተለይም በዕርቅ ዙሪያ በርካታ ጽሁፎችን ሲያቀርቡና ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በኃላፊነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከአገራቸው ውጪም በኬንያ፣ በሞዛምቢክ፣ በስዊትዘርላንድና በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በከፍተና ኃላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

ኖርዌይ ኤምባሲ እና ኢ/ር ኃይሉ እየተወዛገቡ ነው

ኖርዌይ ኤምባሲ እና  ኢ/ር ኃይሉ እየተወዛገቡ ነው
 
“ያከራየኋቸውን ቤት ለመልቀቅ እምቢተኛ ስለሆኑ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቄያለሁ”
- ኢ/ር ኃይሉ
ኖርዌይ ኤምባሲ ከኢ/ር ኃይሉ ሻውል የተከራየውን ባለ ሁለት ፎቅ የመኖሪያ ህንፃ ለ15 አመታት ሲጠቀምበት እንደቆየ የገለፁት የአዲስ አድማስ ምንጮች፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውዝግብ የተፈጠረው ቤቱን ልቀቅ፣ አልለቅም በሚል ነው ብለዋል፡፡

Friday, August 23, 2013

አምስተኛው ባርነት – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

በጥንቱ ስርዓት፣ አንድ ሰው ከአራቱ በአንዱ መንገድ ባሪያ ይሆናል። የመጀመሪያው በጦርነት ተሸንፎ ከተማረከ ፣ ሌላው እዳውን መክፈል አልችል ብሎ በእዳ ከተያዘ ፣ ሶስተኛው ከባሪያ ቤተሰብ የተወለደ ከሆነ በውርስ፣ አራተኛው ደግሞ ባሪያ ፈንጋዮች ይዘው ከሸጡት ነው። በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ ቢጠፋም፣ ባርነት ግን አልጠፋም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲያውም አምስተኛውን የባርነት መንገድ እያየን ነው፤ ይሄ ባርነት በባህሪው እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየና አስገራሚም ነው። እመለስበታለሁ።
ባሪያ ማለት፣ የጌታውን እጅ አይቶ የሚያድር፣ በራሱ ነጻነት የሌለው፣ ሰምቶ የመቀበል እንጅ ሰምቶ የመመለስ መብት የሌለው፣ በግዑዝና በነጻ-ሰው መካከል ያለ ፍጥረት ነው። ባርያ ሰውን ሰው የሚያደርገውን ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተገፈፈ በመሆኑ፣ ከሰው ተርታ የሚመደበው ስለሚመገብ፣ ስለሚለብስ፣ መጠለያ ስላለው፣ ቋንቋ ስለሚጠቀም እና አውራጣት ስላለው ብቻ ነው፤ ከዚያ በተረፈ ግን የጭነት እንስሳ ማለት ነው። ባሪያ በእግዚአብሄር አምሳል በመፈጠሩ ክፉና ደጉን የመለየት ስልጣን ቢሰጠውም ፣ ስልጣኑን በጌታው በመነጠቁ ፣ ሁልጊዜ የጌታውን ደግ ነገር ብቻ እያየ እና እያመሰገነ የሚኖር ፍጥረት ነው።

ሆስኒ ሙባረክ በነጻ ተፈቱ

ኢ.ኤም.ኤፍ. – በዛሬው እለት በ እስር ላይ የነበሩት የቀድሞው የግብጽ ፕሬዘዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር በነጻ ተፈተዋል። የ85 አመቱ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ከአንድ አመት በላይ በ እስር ላይ የቆዩ ቢሆንም፤ አሁን ግን ፍርድ ቤት ቀርበው፤ ዳኛው በነጻ እንዲሰናበቱ አድርጓል። ፍርድ ቤቱ የቀድሞውን ፕሬዘዳንት በነጻ ሲያሰናብት፤ ወታደራዊው አመራር ደግሞ ፕሬዘዳንቱን፤ በሄሊኮፕተር ጭኖ ወደ ጦር ኃይሉ ሆስፒታል ወስዷቸዋል።

የሥላሴዎች እርግማን (ሦስት) ፦ አዳክሞ ማደህየት – ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም


አንድ በጣም የተገረመ ደቡብ አፍሪካዊ ይህንን ሁሉ መንገድና ሕንጻ በአንድ ጊዜ ለማሠራት ገንዘቡን ከየት ነው የምታገኙት? ብሎ ጠየቀኝና ከወርቅ-ቡና አልሁት፤ ሳቅ አለና እኔኮ ከልቤ ነው የምጠይቅህ አለኝ፤ እንግዲያው ዘክዝኬ ልንገርህ አልሁት፤ ለወትሮው ብዙ የምክር ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም ለመንግሥትህ እንዳትናገርና የዚሁ ዓይነት ሥራ በደቡብ አፍሪካ እንዳይጀመር ቃል ግባልኝ አልሁትና ቀጠልሁ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመንግሥት ባንኮች ደጃፍ ላይ የነበረውን መጨናነቅ አይተሃል ወይ? ብዬ ጠይቄው ማየቱን ካረጋገጥሁ በኋላ ጉዳዩን እንደሚከተለው አስረዳሁት፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚመጡ ተጠቆመ

ፓስፊክ ሊንክ ኢትዮጵያ ሪል ስቴት የ73.3 ሚሊዮን ብር ክስ ተመሠረተበት

ermiyas

የሰማያዊ ፓርቲ ያላቻ ጋብቻ (ከአቶ ይድነቃቸው ከበደ)

መንግስት ተግባሩን ሣይወጣ ቀርቶ መንደርተኛና ቧልተኛ ሲሆን እንዴት ያሳፍራል ! ይህን ለመፃፍ ያነሣሣኝ አዲስ ዘመን ጋዜጣ “ የሰማያዊ ፓርቲ ጥቁር ተግባራት ” በሚል በገፅ 3 አጀንዳ ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪን በተጨማሪ ዛሚ ሬዲዮ ጣቢያ የክብ ጠረጴዛ ውይይት እና በሬዲዮ ፋና በዜና እና በልዩ ዘገባ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች፤በተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄዱ ጥቃቅን አነስተኛ ስብሰባዎችና ሰልፎች የሚሰሙ መፈክሮች የመንግስትን ፍርሃቱን እና ውንጀላ በሚገባ የሚያሳዩ በመሆናቸው ነው፡፡

Yidenachew Kebede
መንግስት ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለጥያቄ አቅራቢዎች የሚያስርበት እና የሚያሰቃይበት አዋጅ ማውጣት ይቀለዋል፤ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም መነሻውን 4 ኪሎ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መድረሻውን ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ያደረገ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ተደርጓል፡፡ በዕለቱም ለመንግስት የቀረበለት ጥያቄ የሰብዓዊ ጥሰቶች እንዲስተካከሉ፣የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣በዓይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንዲቆም በዚህም ምክንያት የታሰሩት እንዲፈቱ፣የኑሮ ውድነቱ ማሻሻያ እንዲደረግበት እና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚል ጥያቄዎች ናቸው፤እጅግ በሰለጠነ እና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄው ለመንግስት የቀረበ ሲሆን መንግስትም ለዚህ ምላሽ የሦስት ወር የጊዜ ገደብ ተሰጥቶታል፡፡

Thursday, August 22, 2013

ህወሓት ወያነ አይደለም! Abraha Desta

ህወሓትን ለመጥቀስ ‘ወያኔ’ የሚለው ቃል ተጠቅሜ አላውቅም። ከወራት በፊት ታድያ ለምን ‘ወያነ’ የሚል ቃል እንደማልጠቀም አንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ በውስጥ መልእክት ልኮልኝ ነበር። በሆነ ምክንያት መልስ አልሰጠሁም ነበር።
አሁን ግን ትንሽ ልበል። ምክንያቱም ከሁለት ቀናት በፊት ከዞን ዘጠኝ አባላት (ጓደኞቼ) በአካል ተገናኝተን ‘ወያነ’ ስለሚለው ቃል ተጫውተን ነበር። ርእሰ ጉዳዩ ‘የህወሓት /ኢህአዴግ መንግስት ወያነ እንዲባል አይፈልግም፤ ወያነ ብለው ለሚፅፉ ወይ ለሚናገሩ ሰዎች በተለየ ሁኔታ ይጠምዳል’ የሚል ነበር።
እኔ ግን በዚህ ሓሳብ በከፊል አልስማማም። ምክንያቱም ህወሓቶች ‘ወያነ’ የሚል ስም አይጠሉትም። የሚኮሩበት ስማቸው ነው። ‘በህወሓት ምትክ ‘ወያነ’ የሚል ቃል የሚጠቀሙ ዜጎች በጥቁር መዝገብ ውስጥ ይገባሉ’ በሚል ግን እስማማለሁ። ምክንያቱም አንድ ሰው ህወሓትን በመጥፎ ለማንሳት ፈልጎ ‘ወያኔ’ የሚል ቃል ሲጠቀም የህወሓት መሪዎች ሁለት ነገሮች ይገነዘባሉ።

በአሜሪካ ግቢ ቦምብ እላያችን ላይ ሳይፈነዳብን ተገኘ


ምስጋና ለኢትዬጲያ ፌደራል ፖሊስ እና ለብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ጥምር የጸረ ሽብር ቡድን ግብረ ሃይል በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በተለምዶ በአሜሪካ ግቢ ራስ ስዩም ሆቴል አጠገብ ወደ አርባምንጭ ከተማ ጭነት የሚጫንበት ቦታ አካባቢ በሚገኘው ራህመት ኤጀንሲ በር ላይ ኮድ 3 የታርጋ ቁጥር 73189 በሆነ አንድ |የጭነት ማመላለሻ አይሱዙ ጎማ ስር የአጅ ቦምብ ተገኘ ተባለላቹ፡፡፤
ይህን የእጅ ቦምብ የአዲስ አበባ ከተማ መደበኛ ፖሊሶች ቀደም ብለው በእጃቸው ይዘውት እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፤የእጅ ቦምቡን ጠዋት ይዘውት ከነበሩት ሁለት ፖሊሶች መካከል የአንዱ ፎቶ ከዚህ በታች ተያይዞ ቀርቧል|፡፡ሙስሊሙ የመረጃ ሰው ሆኗል፡፡አልሃምዱሊላህ ይህ ቦምብ አፈንጂው እና ቦምባ አምካኞች ያደረጉት ትንቅንቅ አንድ ወንድም ያደረሰኝን መረጃ ላካፍላችሁ፡፡

Wednesday, August 21, 2013

በሰሜን ኮሪያ የደናግላት ቁጥር መመናመን ፕሬዚዳንቱን አሳስቧል!

በኢትዮጵያስ?

north korea


ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ እን ለሚያካሂዱት የዳንስ ስኳድ በቂ ደናግልት ለማግኘት መቸገራቸውን የደቡብ ኮሪያ ዜና ቾሱን ኢልቦ ገለጸ፡፡ ሰሜን ኮሪያ ለፕሬዚዳንቷ ክብር የምትጠቀምባቸው ዳንሰኞች የሚውጣጡት ከደናግልት ሴቶች ነው፡፡ ለዚህ ፕሬዚዳንቱን ለማዝናናት የሚደረገው የዳንስና ሙዚቃ ሙያ አባል ለመሆን የሚችሉ ድንግል ሴቶች በአብዛኛው ወጣቶችና የኮሌጅ ተማሪዎች እንደሆኑ ተዘግቧል፡፡ ክብረንጽህናን መጠበቅም ዋንኛው ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

ሃይማኖትና ፖለቲካ በኢትዮጵያ (ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ)

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

1. መግቢያ:
Ginbot 7 movement chairman Dr. Berhanu Negaካለፈው ሁለት አመት ግድም ጀምሮ “መንግሥት በዲናችን ጣልቃ አይግባብን” በሚል ሰፊ ማእቀፍ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እየተደረገ ያለው ትግል፤ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ደግሞ ሁለት አስርት አመታትን ያስቆጠረ ከቀኖናው ውጭ መንግሥት የቤተክርስቲያኑን መሪ አይምረጥብን በሚል በመሰረታዊ ሀሳቡ ከሙስሊሙ ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዳይ በተነሳ ውዝግብ ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ ያለችበት ሁኔታና በዚህም ምክንያት በመንግሥት የተገፋው “ስደተኛው ሲኖዶስ” በራሱ ላይ የደረሰውን ሁከት በመቃወም የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ተዳምረው ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ጤነኛ የሆነው የሀይማኖትና የፖለቲካ ግንኙነት ምንድን ነው? ወይንም ደግሞ የመንግሥትና የሀይማኖት ግንኙነት ምን መሆን አለበት?

Tuesday, August 20, 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች ከተለያዩ ምንጮች)

water line


ነዋሪዎች በውሃ እጦት ተሰቃየን አሉ
በሳምንት አንድ ቀን ውሃ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች፣ በውሃ እጦት አካባቢያቸውን በመጥፎ ጠረን የሚበክሉ የኮንዶሚኒየም መኖሪያዎች፣ ለተደጋጋሚ አቤቱታ ምላሽ ሳያገኙ በርካታ ወራት እየተቆጠሩ የሚማረሩ ነዋሪዎች የአዲስ አበባ የዘመኑ ገጽታ ሆነዋል፡፡ በቂ ውሃ ስለሌለ በራሽን ለማከፋፈል እየሞከረ መሆኑን የሚልፀው የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበኩሉ፤ የኤሌክትሪክ መቆራረጥና የአንዳንድ ሰራተኞች እንዝህላልነት፣ ለመንገድ ግንባታ የሚቆፈሩ ቧንቧዎች እንዲሁም በከንቱ የሚባክን ውሃ መብዛቱ የውሃ እጥረትን እንዳባባሱ ይናገራል፡፡

Monday, August 19, 2013

ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!

“እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!'' ኦባንግ

recon-e
እሳት ሲነሳ የመጀመሪያው ተግባር እሳቱን በፍጥነት ማጥፋት ለሚችለው የእሳት አደጋ ብርጌድ መደወል ሲሆን፣ ቀጣዩ ተግባር እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ነፍስ አትርፈው እሳቱን በተገኘው መንገድ ለማጥፋት መረባረብ ነው። ይህ የተለመደው ተግባር ዛሬ በኢትዮጵያ ስለመስራቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክትር ስጋት አላቸው። እናም “እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ያሰማሉ።

ቀዳማዊ ኃይለስላሴና አዲሱ የኢትዮጵያ ሞዴል

(ክፍል አንድ -በጃፋር ሐሰን)

hailes


1930ቹ ዓመታት ለመላው ዓለምና ለኢትዮጵያ አስቸጋሪ ጊዜያት ነበሩ፡፡ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት እየተፋፋመ በመጣበት ጊዜ ኢትዮጵያም በእብሪተኞች ወራሪዎች ዓይን ውስጥ ገብታ እንደነበር በታሪክ ይታወቃል፡፡

ታሎው ኦይል የተባለው ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያውን የነዳጅ ክምችት ማውጣት እንደሚችል ገለጸ

http://api.ning.com/files/uHRAM*dGlS-LmWsm337OZ6BEglttsbvpfPbxSHGm9FJDkyr-usatxf1PiO0iM-XNfEPd*2amUqb2oyvjr4yhddifHjfSxocZ/sabisa.jpg
የኬንያን የነዳጅ ክምችት ያገኘው የእንግሊዙ ታሎው ኦይል እንደገለጸው የነዳጅ ክምችቱ ወደ ጎረቤት ሀገር አትዮጵያ ሊቀጥል ይችላል የሚል እሳቤ ላይ እንዳለ ዋሰሽንግተን ፖስት ዘገበ፡፡ በዚህም መሰረት ታሎው ኦይል ፣ አፍሪካ ኦይል ኮርፖሬሽንና ማራቶን ኦይል ኮርፖሬሽን በደቡብ ኦሞ አካባቢ የሳቢሳ ፕሮጄክት ጉድጓዶችን እንደሚያጠናቅቁ ተገለጸ፡፡
ማርቲን ሙቦጎ የተባለ በኬንያ የታሎው ኦይል ማኔጀር እንዳለው “ የመጀመሪያው የነዳጅ ግኝት በኢትዮጵያ ትልቅ ይሆናል ለሀገሪቱም ትልቅ ታሪክ ነው ፡፡’’ ብሏል
ታሎው ኦይል ባሁኑ ሰዓት የምስራቅ አፍሪካን ተራራማ ቦታዎች በመቃኘት ላይ ሲሆን እይታው በኡጋንዳና በኬንያ የነዳጅ በረከት አስገኝቶለታል፡፡ ለድርጅቱ አዲስ የነዳጅ ክምችት በኢትዮጵያ ተገኘ ማለት አዲስ የነዳጅ ግዛት ሲሆን ለሀገሪቱ መንግስት ደግሞ ከውጭ የሚገዛው የሀይል ምንጭ ቀርቶ እንዲሁም አብዛኛው ኢኮኖሚ ከቡና ሽያጭ ቀረጥ ከማግኘት ይልቅ በነዳጅ ዘይት የተደገፈ ኢኮኖሚ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡

Sunday, August 18, 2013

አሁን በደረሰን ዜና ድምፃዊ ኢዮብ መኰንን አረፈ

ድምፃዊ ኢዮብ መኰንን ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ባደረበት ድንገተኛ ሕመም ራሱን ስቶ በሕክምና ላይ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የተገለጸው ኢዮብ የሕመሙ መንስዔ ስትሮክ መሆኑ ታውቋል፡፡
የቅርብ ጓደኞቹ ድምፃዊው ይህ ነው የሚባል ሕመም እንዳልነበረበትና ታሞ እንደማያውቅ ገልጸው፣ ባለፈው እሑድ ድንገት እጁ ላይ በተሰማው ስሜት ምክንያት ሐያት ሆስፒታል ለመታየት ቢሄድም ሙሉ ጤነኛ እንደነበር ተነግሮታል፡፡
ባለፈው ማክሰኞ ብስክሌት እየነዳ ልጁን ከትምህርት ቤት አስመዝግቦ ሲመለስ ቤቱ በር ላይ ተዝለፍልፎ በመውደቁ፣ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ገብቶ እስካሁን ድረስ ራሱን ስቶ እንደሚገኝ ተረጋግጧል፡፡

Saturday, August 17, 2013

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከኤፈርት ዳይሬክተርነት ተነሱ

“ የወያኔ ባለስልጣን ማን ሁነዉ ነዉ ሌላዉን ቴረሪስት (Terrorist) እያሉ የሚከሱት” አብዲሳ አጋ(ገሞራዉ)

ወያኔ ሽብርተኝነትን(terrorism) ሲያራምድ የታየዉ የመንግስት ስልጣን ከመጨበጡ በፊት ብቻ ሳይሆን፣ ከዚያም በኋላ ነበር፡፡ ወያኔ በጫካ ትግል ዉስጥ በነበረበት ጊዜ ጀምሮ ህዝብ በግዳጅ ወደ ጦር ግንባር እንዲቀላቀሉ፣ ባንኮች የመዝረፍ ፣ ድልድዮችን እና ተቋማትን በቦንብ ማፈራረስ፣ በግድያ ተግባር ተሰማርቶ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸዉን ታጋዮች በመግደል የአሸባሪ ቡድን ተግባር በማከናወን ይፈረጃል፡፡የትግራይ ህዝብን ከብቶቻቸዉን እና እህሎቻቸዉን ሲዘርፉ እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡

“ተቃዋሚዎች ከአክራሪዎች ጋር የፈፀሙት ያልተቀደሠ ጋብቻ ለህዝቡ ስጋት ሆኗል” – አቶ ሽመልስ ከማል (ሚ/ዴኤታ)

“ተቃዋሚዎች ከአክራሪዎች ጋር የፈፀሙት ያልተቀደሠ ጋብቻ ለህዝቡ ስጋት ሆኗል” – አቶ ሽመልስ ከማል (ሚ/ዴኤታ)
አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፣ በመቀሌና በወላይታ ሶዶ ከተሞች ሠላማዊ ሠልፍና ህዝባዊ ስብሠባ ለማካሄድ የነበረው እቅድ በተለያዩ ጫናዎች መጨናገፉን የፓርቲው ሊቀ መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገለፁ። 
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጠበቁትን ያህል የህዝብ ድጋፍ ሲያጡ የራሳቸውን ድክመት ለመሸፈን መንግስትን ይወነጅላሉ ብለዋል፡፡ 

Friday, August 16, 2013

አንድነት ፓርቲ: የሙስሊሞችን ጥያቄና የሸኽ ኑሩን ግድያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ማያያዝ ወንጀል ነው!!!

ነሐሴ 10 ቀን 2005 ዓ.ም

Unity for Democracy and Justice (UDJ) partyከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
እንደተለመደው የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በመረጃና ደህንነት አገልግሎት ተሰናዳ ያለውን ‹‹ሸህ ኑሩን ማን ገደላቸው?›› በሚል ርዕስ ዶክመንተሪ አዘጋጅቶ አስተላልፏል፡፡ ይህ ዶክመንተሪ የገዥውን ፓርቲ ብፅእና ከመተረክም በላይ ጉልበተኝነትንና ፍረጃን ማእከል አድርጎ ከአኬልዳማ እና ከጃሀዳዊ ሀረካት የቀጠለ በፓርቲያችን እና በዜጎች ላይ የተቃጣ ህገ ወጥ የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው፡፡ የመንግስትነት ስልጣን የያዘ አካል ሀገራዊ ችግሮችን ለምን በዶክመንተሪ ፊልም ለመፍታትና ለማዳፈን እንደሚጥር እንቆቅልሽ ቢሆንብንም አሁንም ከዜጎች የሚነሱ ሰላማዊና ህጋዊ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት እንዳለባቸው ፓርቲያችን በፅኑ ያምናል፡፡ የሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄም በውይይትና በመግባባት ላይ ተመስርቶ ሊመለስ እንደሚገባና የሀይል እርምጃው መቆም እንዳለበት ያለንን ጽኑ እምነትና አቋም ደግመን እናረጋግጣለን፡፡

Thursday, August 15, 2013

ነሀሴ 26ን በደቦ ሸኝተን 2006 ዓ.ምን በተስፋ!

(አርአያ ጌታቸው)

semayawiparty

Wednesday, August 14, 2013

አሳዛኝ ዜና እህታችን ፍርዶስ በ ዶ/ር ሽፈራዉ የድህንነት ሀይሎች በደርሰባት የ ኤሌክትሪክ ሾክ እና ድብደባ ከዚህ አልም በ ሞት ተለየች

muslim1

አሳዛኝ የግፍ ዜና ኢናሊላሂወኢና ኢለይሂ ራጂኡን በሴት ሙስሊሞች ላይ የሚደረሰዉ ግፍና መከራ እንደቀጠለ ነዉ:: ይህም የግፍ ዜና ምንጮቻችን እንደዘገቡልን እናቀርበዎል:: ጉዳዩ እንደሚከተለዉ ነዉ በቅርቡ የፌደራል ጉዳዮች ከየክፍለ ከተማዉ የተመረጡ ሰዎችን በመጥራ ስብሰባ አካሂዶ ነበር:: በዚህም ስብሰባ ላይ ከኮልፌ ክ/ከተማ ሶስት ሰዎች የተሳተፍ ሲሆን ሁለት ወንድ እና አንዲት ሴት ይገኙበታል:: በዚህ ስብሰባ ላይ የኮልፌ ክ/ከተማ ነዎሪ የሆነችዉ ፍርዶስ የተባለች እህታችን ትገኝበት ነበር:: 
በስብሰባዉ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራዉ ተገኝተዉ ስብሰባዉን አካሂደዉ እንደነበር ምንጮች ገልፀዎል:: በስብሰባዉም ላይ ዶ/ር ሽፈራዉ እጅግ አፀያፊና ድንበር ያለፍ ንግግሮችን በህዝበ ሙስሊሙ በተመረጡት ኮሚቴዎች ላይ በመናገራቸዉ ይህንን የሰዉየዉን ዘለፉና ስም ማጥፉት መሸከም እና መታገስ ያቃታት እህታችን ፍርዶስ ዶ/ር ሽፈራዉ ለተናገረዉ ንግግር እልህ በተሞላበት ቃል ተቃዉሞአን በመግለፅ “ዶ/ር ሽፈራዉ ሴት የሴት ልጅ ነህ” በማለት የስብሰባ አዳራሹን ጥላ ወታለች::

‘‘የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ገዥ እንጂ መሪ አግኝቶ አያውቅም’’ ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ

ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ

Semayawi Party- Ethiopia (Facebook)
ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ በተደጋጋሚ ጊዜአት በአደባባይ ከማይታዩ የሀገራችን አንጋፋ ሊህቃን አንዱ ናቸው። ምሁሩ በበርካታ መድረኮች ባለመቅረብ በቁጥብነታቸው ቢታወቁም ባገኙት መድረክ ግን አነጋጋሪ ርዕሰ ጉዳዮችን ያነሳሉ።
ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው የመወያያ መድረክ ላይ ቀርበው ታዳሚዎችን የመሰጠና ያወያየ ኃሳብ አንሸራሽረዋል። በፓርቲው ጽ/ቤት የተገኙ ወጣት ምሁራንም የፕሮፌሰሩን ኀሳብ በሌላ ኀሳብ በመሞገት ምሁራዊ አስተሳሰቦችና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ጥልቅና ማራኪ ውይይት ተደርጓል።
ፕሮፌሰር በፍቃዱ በመወያያ መድረኩ ላይ ቀርበው የመነጋገሪያ ኀሳቦችን ያቀረቡት ፓርቲው በወጣቶች የሚመራ በመሆኑ አቅጣጫ የሚጠቁሙ ኀሳቦችን ለማሳየት ነበር። ጎን ለጐንም ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ፕሮፌሰሩ በዋናነት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ማነቆዎች ላይ የመንግስትና የሕዝቡ ሚና ምን መሆን እንዳለበት የራሳቸውን የመፍትሄ ኀሳቦች ሰጥተዋል። ከሁሉም በፊት ግን ፕሮፌሰሩ የሰሞኑ ወቅታዊና አነጋጋሪ ጉዳይ ስለሆነው የኃይማኖት ጉዳይ የተናገሩትን እናስቀድም። ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያ ክርስትናና እስልምና ምን ያህል መስተጋብር ፈጥረው እየኖሩ መሆኑን ከራሳቸው የቤተሰብ አወቃቀር በመነሳት የተናገሩት የታዳሚውን ቀልብ ያሳበ ነበር።

የአሜሪካ ፓሊስ ኢትዮጵያውያኑን በማደን ላይ ናቸው

 ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ ፖሊሶች ከኢትዮጵያ ለምስክርነት መጥቶ የጠፋን ኢትዮጵያዊ ዱካ ለማግኘት ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ሲአትል ኒውስ ዛሬ ዘገበ፡፡ ካሳይ ወልደ ፃድቅ የተባለው ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊያኖቹ ጥንዶች ከኢትዮጵያ በማደጎ ያመጧትን ልጅ ገድላችኋል ተብለው ለተከሰሱበት ወንጀል አቃቢ ህግ ለምስክርነት ማስረጃ ይሆን ዘንድ ብለው ነበር ከኢትዮጵያ ያመጡት፡፡
ካሳይ በፍርድ ሂደት ላይ ላለው ጉዳይ ባለፈው አርብ በማውንት ቬርኖን ካውንቲ ፍርድ ቤት በመቅረብ የመጀመሪያ ዙር ምስክርነቱን ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ከተያዘለት ማረፊያ ክፍል መጥፋቱን አቃቢ ህጎች ለፖሊስ አስታውቀዋል፡፡
አሜሪካዊ ጥንዶቹ ወደ አሜሪካ ላመጧት የ13 ዓመቷ ታዳጊ ሀና ዊሊያምስ ካሳይ የቅርብ ቤተሰብ ሲሆን የምስክርነት ቃሉን ሳይሰጥ መጥፋቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡

Tuesday, August 13, 2013

መሰረቱ ውሸት ሆኖ የማፈርስ ራሱ ውሸት ብቻ ነው (ሸንቁጥ፤ ከአዲስ አበባ)

1069387_203643919793903_873502461_nAbe Tokchaw
አንድ ጊዜ ፈርዶበት መዋሸት የጀመረ ሰው፤ ውሸቱ ሲደጋገምና ሲለምድበት ዋሾው በየቀኑ፤ጥቂት ቆየት ብሎ ደሞ በየሰአቱ፤ ቆየት ሲል ደሞ በየደቂቃው፤ ውሎአድሮም በየሴኮንዱ ካልዋሸ ሱሱ ቀስፎ ይይዘውና ችግር ይፈጠርበታል፡፡ ራስ ምታት ይነሳበታል፡፡ ጩህ ጩህ ዋሽ ዋሽ ያሰኘዋል፡፡በዚህ ሁኔታ ለጥቂት ጊዜያት ከቆየ በኋላ ደሞ ውሸቱ ከመጠን ሲያልፍና አድማጭ ሲያጣ፤ አድማጫ ለማግኘት ሲል ወጪ በማውጣት አድማጮችን
እየጋበዘ ‹‹መተርተሩን ሊጀምር ነው እየተባለ›› እየታማ ያወርደዋል፡፡የሚዋሽበት ቢያጣ እንኳን ሰማይን ተቀዶ ሲሰፋና፤ ዝናብም የጠፋው የተቀደደውን ስሰፋ የዝናቡን መውረጃ በስህተት ሰፍቼው ነው እስከማለት ይደርሳል፡፡ ከዚያም ያልፍና የምን ላውራ በሽታው ስለሚያስቸግረው ውሸት በመፍጠርም ይባዝናል፡፡መዋሸቱ ከቅሌት ይልቅ እንደመልካም ሙያ ሆኖ ስለሚታየው በመዋሸቱ ሊደነቅና ሊከበር ያምረዋል፡፡ ከአድማጭ ባለፈ በዚህ ውሸቱ ሕሊና ያለው ቤተሰብ ካለው፤ ወዳጆች ካሉት፤ ውሸቱን እንዲተው ከመምከርም አልፈው ‹‹ዳግም ብትዋሽ አብረንህ ላንቆም፤ በተገኘህበት ላንኖር፤ በምትውልበት ላንቀላቀል እርም ብለን ልንምል ነው በማለት ማስጠንቀቂያ ይሰጡታል፡፡

ሌሊሴ ተፈታች! ቀጥሎስ?

ሌሊሴ ተፈታች! ቀጥሎስ?

lelissie
ላለፉት 5 ዓመታት ያህል ከልጆቿና ባለቤቷ ተለይታ በእስር ስትማቅቅ የነበረችው ሌሊሴ ወዳጆ መፈታቷ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ማስደሰቱ ተጠቆመ፡፡

Monday, August 12, 2013

ስንቅና ውሸታም እያደር ይቀላል! – ፈቃዱ ለሜሣ (ፕሮፌሰር)

የኮርስ ስም ፤ በኢትዮጵያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ላይ የሚሠነዘሩ የፈጠራ ወሬዎችና ተጨባጩ ሃቅ
የኮርስ ቁጥጥር ፤ ‹hist101› (ልቦለድና ፈጠራ በኢትዮጵያ ኦሮሞዎች ላይ)
የኮርስ መምህር፤ ፕሮፌሰር ፈቃዱ ለሜሣ
ኮርሱ የተጀመረበት ወር፤ ሐምሌ 2005
ትርጉምና ቅንብር፤ ይነጋል በላቸው

Sunday, August 11, 2013

በማሸበር የሚኖሩ በመግደል የሚከብሩ የሰው አረሞች

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

አረም ማለት ያልተዘራበት የሚበቅል ገበሬ የዘራውን ሰብል የሚሻማ፣ ውሀውን የሚጠጣበት፣ ለበሽታና ተባይ መጠለያ በመሆን ለሰብል ጉዳት ምክንያት የሚሆን እጽዋት ማለት ነው። አረም በስሮቹ አማካይነት የሰብሉን ስር አንቆ የሚገድል፣ አንዳንዱም እንደ ፓራሳይት ሰብል ላይ ተጣብቆ የሚበቅል እንደ አቀንጭራ ያለ ማለት ነው። አረሞች በፈጣን አስተዳደጋቸው ሳቢያ አልሚ ንጥረ ነገሮችን ከመሬት የፀሀይ ብርሃን ከሰማይ በመሻማት የሚያቀጭጩና የሚገድሉ ናቸው። የስንዴ ማሳ ውስጥ የበቀለ በቆሎም እንኳ ቢሆን አረም ነው፣ ገብስም ቢሆን አረም ነውና ተነቅሎ ይጣላል።Tigray People Liberation Front Split
አረም ዘሩን በማባዛትና የመኖር እድሉን ለማራዘም በርካታ ዘዴዎችን እየተጠቀመ በብዛት የሚንሰራፋና በወቅቱ ካልታረመ ሰብል የሚያጠፋ ነው። ጎበዝ ገበሬ አርሞና ኮትኩቶ ሰብሉን ካልተንከባከበ በሰብል ምርት ምትክ አረሙን ማፈስ ይገደዳል። ልክ እንደ ምሳሌው ኢትዮጵያዊነትን የሰው አረም ውጦታል።

ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ቁስላችሁን አስራችሁ ከወያኔ ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ተቀላቀሉን!!!


Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracyበእስልምና እምነት እጅግ በደማቅ ሁኔታ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው ኢድ አልፈጥር ለ1434ኛ ጊዜ ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ. ም.  በመላው ዓለም በደስታ ሲከበር ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ግን ለዚህ አልታደሉም። በእለቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የኢድ ሰላታቸውን ሰግደው ወደ የመኖሪያ ቤቶቻቸው ሲመለሱ ለድብደባ በሠለጠኑ የወያኔ ወታደሮች አሰቃቂ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። በዚህ እለት በአዲስ አበባና እና ሌሎች ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች በርካታ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ አሁን  ሕፃናት የወያኔ የጥይት ሰለባ ሆነዋል፤ ከዚያ እጅግ አሰቃቂ ግድያና ወከባ ያመለጡት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአስር ሺዎች የሚገመቱ ሙስሊሞች በዓሉን ያሳለፉት በወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ በሕመምና በረሀብ እየተሰቃዩ  ነው።

Thursday, August 8, 2013

በመንግሰት የችግር አፈታት ዘዴዎች ዛሬም አዝነናል፧ አፍረናልም!!!!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ከሁሉም በማሰቀደም ሰማያዊ ፓርቲ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳቹ፣ በዓሉ የሰላምና የደሰታ እንዲሆንላቹ ኢድ ሙባረክ በማለት ምኞቱን ይገልፃል ::Blue Party Ethiopia
ኢሕአደግ መራሹ መንግሰት ተቋማትን የመቆጣጠር አባዜው ከግዜ ወደ ግዜ እየባሰባት በመምጣቱ ዛሬም እጁን ያላሰገባበት ምንም አይነት ተቋምና አሰተሳሰብ ባይኖርም በተለይ ባለፈው አንድ አመት ተኩል ጀምሮ ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በፈጣረው እሰጥ አገባ መፍትሔ አጥቶ እሰከ አሁኗ ሰአት ቀጥሏል:: ሰማያዊ ታርቲ የመንግሰትን በሐይማኖት ጣልቃ መግባት አጥብቆ በመቃወም የራሳቸውን የእሰልምና እምነት መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲፈታና ችግሩም በውይይት እንዲፈታ በተደጋጋሚ ግዜ ጥሪውን አቅርቧል::

Ethiopian repression of Muslim protests must stop | Amnesty International

Ethiopian repression of Muslim protests must stop | Amnesty International

ሰበር ዜና ! የፌደራል ፕሊስ እርምጃ እየወሰደ ነው !!

ድምፃችን ይሰማ

እስከ አሁን ባለው መረጃ በአዲስ አበባ፣ በወልቂጤ፣ በደሴ፣ በአዳማ፣…የመንግስት ታጣቂዎች የዒድ ክብረ በዓልን ለመፈጸም የወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ኃይል የተቀላቀለበት ድብደባ ፈጽመዋል፡፡ መንግስት ለኢትዮጵያውያን ሙስሊም ዜጎቹ ያለውን ከልክ ያለፈ ጥላቻ በዛሬውም በኢድ በዓል ቀን አሳይቷል፡፡
Ethiopian Muslims

በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ ፖሊስ ጥቃት እየፈጸመ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ ፖሊስ ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ ሰማሁ!

Wednesday, August 7, 2013

ወያኔ እንደ ቆሰለ አውሬ…


Author and writer Tesfaye Zenebe from Norway
ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)
ዘመንኑ ያለቀበት ስርዓት፣ መዋቅሩ የፈረሰ ስርዓት፣ ሁለመናው እኩይ በሆነ በሕዝብና ሃገር ጥላቻ የተተበተበ ስርዓት፣ የእድሜ ዘመኑ እያለቀና የማስተዳደርና የመምራት አቅም ማጣት ሲጀምር ለስልጣኑና በስልጣን ዘመኑ የመዘበረውን የሕዝብና የሃገር ሃብት ለማስጠበቅ የውር ድንብሩን ዪዳክራል፡፡
ይህው በመቃብር አፋፍ ላይ ያለው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት በሕዝብና በሃገር ላይ ሲያደርስ የነበረውን  እጅግ ዘግናኝ ክህደት ከማንም ኢትዮጲያዊ አህምሮ የሚፋቅ ባይሆንም ስርዓቱ ቤሔራዊ ስሜት(ሃገራዊ ስሜት) በማጣቱ ምክኒያት የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ ችግር የተቃወሙ ንፁሃን ዜጎች ወይም እንደ ዜጋ በሃገራቸው ውስጥ በሰላም የመኖር ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በግፈኞች ተነጥቀው ነፃነታቸውን ለማስመለስ ፍትህ የጠየቁ ሁሉ በአሸባሪው ስርዓት አሸባሪ ተብለው ሲፈረጁ መመልከት የተለመደ ድራማ ነው፡፡

ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ ከአመታት በኋላ መድረክ ላይ ተገናኙ

“ጥቁር ሰው” በድጋሚ ሲዘፈን ሌላ የሚያስጮህ ነገር እንደሚመጣ ያልጠበቀው የአውሮፓ ታዳሚ፤ ጉሮሮው እስኪነቃ እንደገና ጮኸ። ታዳሚው ከፊት ወንበር ላይ በVIP ላይ ታማኝ በየነ መቀመጡንም ሆነ፤ በስፍራው መገኘቱን አያውቅም። ቴዲ አፍሮም “ጥቁር ሰው”ን እንደገና ከማቀንቀን ውጪ፤ የድሮ ጓደኛው ወደ መድረክ ይመጣል ብሎ አልጠበቀም። የሆነው ግን እንዲህ ሆነ።
ሁለቱም ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው የዘመኑ እውቅ አርቲስቶች ናቸው – ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ።

“መብታችንን ለማስከበር ስንሞክር ገደሉን ” ትግራይ ተወላጆች በሙሉ Abraha Desta

ዜጎች ነንና ፍትሓዊ ልማት ያስፈልገናል’ ሲንል አሰሩን። ‘ደማችን ገብረናልና ሰለማዊ ሰልፍ የመውጣት መብታችን ይከበርልን’ ስንል ደበደቡን። ‘ብዙ መስዋእት ከፍለናልና ነፃነታችንን አትንፈጉን’ ስንል ትጥቃችንን አስፈቱን። መብታችንን ለማስከበር ስንሞክር ገደሉን።
ግን ይህን ሁሉ ወላጆቻችን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የከፈሉት መስዋእት ዓላማው ምን ነበር? ደርግን ደምስሶ ሌላ ደርግ መመስረት? ይሄማ ሊሆን አይችልም። ደርግ’ኮ ደርግ ያሰኘው ተግባሩ ነው።

በፀረ-ሽብር አዋጁ ፓርቲዎች ሊከራከሩ ነው ! ኢህአዴግ፣ መድረክ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ

በዘሪሁን ሙሉጌታ
ከፀደቀ አራት ዓመታት በላይ በማወዛገብ ላይ ያለው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ላይ ፓርቲዎች በመጪው ቅዳሜ ክርክር ሊያደርጉ ነው። የክርክር መድረኩን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ነው።
ተቋሙ በፀረ-ሽብር አዋጁ ላይ እንዲከራከሩ ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ መድረክ አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ጋብዟል። መኢአድ ግን ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ በክርክር መድረኩ አለመጋበዙን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል። ባለፈው አርብ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ፓርቲዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ክርክር መድረክ እንዲመጡ በደብዳቤ ጥያቄ ቢያቀርብም፤ አንድነት ፓርቲ በቂ ጊዜ ይሰጠን በማለቱ ትናንት ይደረጋል የተባለው ክርክር ወደ ቅዳሜ እንዲተላለፍ መደረጉን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ተናግረዋል።

በመንግስት የተዘጋጁ 20 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ብቻ ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ታቅዷል!

የፊታችን ሐሙስ ወይም አርብ የሚከበረውን የኢድ አልፊጥር በአል ታክኮ በኢትዮጵያውያን ሙስሞች ሊካሄድ የታሰበውን ልዩ አገር አቀፍ ተቃውሞ ለማፈን መንግስት አብዛኛውን ሙስሊም ህብረተሰብ ወደ ስታደየም ከመግባት ለማቀብ ማቀዱ ታወቀ፡፡ ይህ እቅድ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተቋሙ እንዲሁም በፌዴራል መጅሊስ እና በአዲስ አበባ መጅሊስ አማካኝነት መሆኑ ታውቋል፡፡ እነደ እቅዱ ከሆነ መንግስት 20ሺ የሚጠጉ ሰዎችን በመመልመልና ወደ ስታዲየሙ ውስጥ እንዲገቡ በመፍቀድ የኢዱን ስርአት ለብቻቸው እንዲፈጽሙ ማድረግ ማስቻል ሲሆን በእለቱም የመጅሊስ ሕገ ወጥ ሹመኛ ግለሰቦች እና የመንግስት ተወካዮች ያለ ተቃውሞ ዲስኩር እንዲያሰሙ እድል ለመፍጠር መሆኑ ታውቋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያደረጉት ቃለ-...

በቃለ-ምልልሱ የአዲስ ዘመን ጋዜጠኞች አቶ የማነ እና ኦቶ ብሩከ በቃለ-ምልልሱ ከዚህ በታች የተገለፁትንና መሰል ጥያቄዎች አንስተዋል
• ሰማያዊ ፓርቲ የእምነት ነፃነትን አስመልክቶ በእስልምና እምነት ተከታች ላይ መንግስት የያዘውን አቋም መቃወሙን አስመልክቶ ጥያቄዎች አንስተዋል
• አቶ ታዲዎስ ታንቱ በፓርቲው ውስጥ ማስተማራቸውን ተቃውመዋል
• እስክንድር ነጋን የነፃነት ታጋይ ነው ፓርቲው ማለቱን ከመንግስት አቋም አንፃር አንሰተው ወቅሰዋል
• ፓርቲው በወጣቶች መገንባቱን አንስተው ልምድ የላቸውምና ለመሪነት አትበቁምና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተው ሰፊ ቃለ-ምልልስ አድርገዋል እንድትከታተሉት በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡




Tuesday, August 6, 2013

ለዜጎች የሚቆረቆሩ የመንግስት ተወካዮችን አፋልጉኝ!

ኮንትራቱስ ይቁም፣ የቀሩትን ዜጎች መብት ማን ያስከብር?

haile saudi


ሳውዲዎች ከኢትዮጵያ ከኬንያና ከኢንዶኖዥያ የቤት ሰራተኛ ቅጥር ካቆሙ ሰነባበተ! ይህነኑ ተከትሎ የቤት ሰራተኛ እጥረት የሳውዲዎች መነጋገሪያ ሆኗል። ባለጸጎቹ የሳውዲ ዜጎች በያዝነው የረመዳን ወር ብቻ 32 ቢሊዮን ሪያል የሚገመት ገንዘብ በሃገር ውስጥ ገበያ ልውውጥ ላይ እንደዋሉ በሰማን መባቻ የሳውዲዎች ችግር ሆኖ በመነገር ላይ ያለው የቤት የሰራተኛ አቅርቦቱን ጉዳይ ነው። ይህንንም የሃገሪቱ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተው በመዘገብ ላይ ናቸው ።

ሰባር ዜና-አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ ከአገር ሸሽተው ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ገቡ!

ድምፃችን ይሰማ

ማክሰኞ ሐምሌ 30/2005
‹‹ህሊናዬ የማያምንበትን እንድሰራ ተገድጃለሁ›› አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ
የመንግስት ክስ መጨረሻው በውል እንኳ አልታወቀም፤ ቀጠሮውም ም እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም!
Ethiopian Musilmsየሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን፣ አሊሞችንና ዳኢዎችን መንግስት በሀሰት በሽብር ወንጀል ጠርጠሮ ከከሰሳቸዉ አንድ አመት ቢያልፍም እስካሁን እልባት ላይ አለመደረሱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ክስ ውስጥ ከከሳሽ መንግስት አቃቢያን ህግ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ቴድሮስ ባህሩ ‹‹ህሊናየ የማያምንበትን እንድሰራ ተገድጃለሁ›› በማለት አገራቸውንና ስራቸዉን ጥለዉ ከአገር ሸሽተው ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ መግባታቸው ተረጋገጠ፡፡ አቃቤ ሕግ ቴዎድሮስ ባህሩ ሲሰሩ የነበረበትን የስራ ጉዳይ ሰነድ እንኳን ሳያስረክቡ ጥገኝነት ጠይቀዉ ከነቤተሰባቸዉ አሜሪካ እንደገቡ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማ ሊሆኑ ከሚችሉ አገራት መካከል ባለመመደቧ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገባ!

መንግስት በመጪው አርብ በኢትዮጵያ የሽብርተኞች ጥቃት ሊፈጸም ስለሚችል ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ ሲል ለበርካታ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልክት (ኬብል) ላከ!
የዩናይትድ ሰቴትስ መንግስት በመላው ዓለም የሚገኙ 22 ኤምባሲዎቹና የቆንስላ ጽ/ቤቶቹ የድንገተኛ ሽብር ጥቃት ሊፈጸምባቸው ይችላል በሚል ባወጣው የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ኢትዮጵያ ባለመካከተቷ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ መግባቱ ታወቀ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በስለላ መረጃዎች ተመርኩዛ በተለያዩ አገራት በሚገኙ ጥቅሞቿ ላይ በአሸባሪዎች ሊፈጸም ይችላል በሚል ባወጣችው መረጃ 22 አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ጥቅሞች ቦታ የተጠቀሰ ሲሆን፤ በእነዚህ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ መሰል የሽብር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል የሚያሳይ መረጃ ባለመገኘቱ ኢትዮጵያ ሳትካተት ቀርታለች፤ በዚህም መንግስት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ መግባቱ ተረጋግጧል፡፡

ወያኔዎች ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በሽብር ተግባር ለመወንጀል ቦምብ አያፈነዱም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው

እንደልቡ ወርቁ

ባለፉት ሀያ አንድ አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ “የሽብር ተግባራት” የሚመስሉ “ሽብሮች” ተከናውነዋል። በሚኒባስ ዉስጥ፣ በሆቴሎች ዉስጥ፣ በቤተ ክርስትያን ቅጥር ግቢ ዉስጥ ወዘተ… ይሁንና ለአንዳቸውም የሽብር ጥቃቶች ባለቤት ተገኝቶላቸው አያውቅም፣ ባለቤት መገኘቱ ይቅርና የረባ ተጠርጣሪ ተይዞ ፍርድ ቤት ሲመላለስ እንኳ አልታየም።A bomb exploded near a court in the west of Ethiopia's capital Addis Ababa
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ህዝቡ ግን “ሽብሮቹን” የሚፈጽመው እራሱ ወያኔ ነው በማለት ያጉረመርሙ ነበር።
ህዝቡም ሆነ ተቃዋሚዎች በሽብር ተግባራቱ ወያኔን ክፉኛ ከሚጠረጥሩባቸው ምክንያቶች ውስጥ፣
1) ወያኔዎች በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻን እንዳተረፉ ስለሚረዱ ማናቸውም አይነት የፖለቲካ ድርጅት ሀገር ውስጥ መንቀሳቀስ ከቻለ ህልውናቸው እንደሚያከትም እርግጠኛ ሆነዋል። ስለዚህም የሚያስፈራቸውን የተቃዋሚ ድርጅት በሽብር ተግባራት ፈርጆ ከጫወታ ውጭ ማድረግ የዘወትር ተግባራቸው ነው። ታድያ እንዚህን ያስፈሯቸውን ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ድርጅቶች በሽብር ተግባር ለመወንጀልና ለመክሰስ ሽብር ቢጤ መከናወን አለበት።

የዘመኑ መንፈስ

Bewketu Seyoum

Bewketu Seyoum

ባገራችን
 ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት ይባላል፡፡የብሄርተኝነት ምእመን ከሆንክየነፍስ አባት ይኖርሀል፣በጭፍን የምትቀበለው ቀኖና ይኖርሀል፣ነገ የምትገባባት የተስፋ ምድርይኖርሀል፣ከሁሉ በላይ ደግሞ ብርቱ ችግርህን የምትደፈድፍበት የመስዋእት በግ 
ይኖርሀል፡፡

ሃይማኖቶች ምእመናንን ብቻ ሳይሆን መናፍቃንንም ያፈራሉ፡፡ብሄርተኞች በስሜት የሚነድደውን ምእመንብቻ ሳይሆን የኔ ቢጤውን መነፍቅም እንደሚያፈሩ አንርሳ፡፡በነገራችን ላይ ሃይማኖትን መካድ ማለትሃይማኖት የሚያነሳቸውን አብይ ጥያቄዎች መካድ ማለት አይደለም፡፡እንዲሁም፣ ብሄርተኝነትን መካድማለት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ህልውና መካድ ማለት አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ፣መናፍቅ መሆንማለት፣ የብሄርተኛ ነቢያት ሰለ ጭቆና ስለ ነጻነት ብሎም ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀርቡትን አጉል እምነትመጠራጠር ማለት ነው፡፡