Translate

Wednesday, January 23, 2013

ኢትዮጵያ ፣ የ ጋዜጠኞቹ ገጠመኝና ዓላማ


ማርቲንና ዮሃን ቃልቲ ሳሉ ሌሎች እስረኞች «የስዊድን ኤምባሲ» የሚል ስያሜ ወደተሰጠው መኝታ ስፍራቸው ይመጡ እንደ ነበር በፈገግታ ያስታውሳሉ።
የኦጋዴን በረሃና የቃሊቲ እስር ቤት ገጠመኞቻቸውን የሚተርክ መጽሐፍ በጥቂት ወራት ውስጥ ሲያሳትሙ ገቢው በኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዳ ተቋም ለማቋቋም እንዲውል አቅደዋል፤
የኢትዮጵያ መንግስት ድንበሬን ያለፈቃድ አቋርጠዋል፣ አሸባሪዎችን ደግፈዋል በሚል ክስ ያሰራቸው ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቤና ጆሃን ፔርሰን ከእስር ከተለቀቁ አምስት ወራት አልፈዋል። ጋዜጠኞቹ በኦጋዴንና በቃሊቲ እስር ቤት ሳሉ ያጋጠማቸውን በመጽሐፍ ለማሳተም ዝግጅት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚደግፍ ድርጅትም ለማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ከእስር የተፈቱትን የስዊድን ጋዜጠኞች ሉድገር ሻዶምስኪ አነግሯቸዋል ገመቹ በቀለ እንደሚከተለዉ አሰባስቦታል።
ማርቲን ሺቤና ዮሃን ፔርሰን የኢትዮጵያን ድንበር በህገወጥ መንገድ በመግባትና ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ጋ ተባብረዋል በሚል ክስ ታስረው 14 ወራት በቃሊቲ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ ነው ባለፈው መስከረም ወር ከእስር የወጡት። በኦጋዴን በረሃና በእስር ቤት ያሳለፉትን ቆይታ በመጽሐፍ የማስፈር ሐሳብን የወጠኑት እዚያው ቃሊቲ እስር ቤት ሳሉ ነው፤ ማርቲን ሺቢዬ፣
ማርቲን ሽብዮ «ለ14 ወራት የመናገር፣ የመጻፍና የማሰብ መብታችንን ተነግፈናል። በነዚህ የስቃይ ወራት ምናልባት አንድ ቀን ወጥተን ይህን ታሪክ እንጽፋለን ብለን እናስብ ነበር። እንዲህ ዓይነቱ የጋዜጠኝነት የተስፋ አጥር ነው አዕምሮአችን ንቁ ሆኖ እንዲቆይ ያደረገ።»
ማርቲንና ዮሃን አሁን ከእስር ነጻ ሆነው ሀገራቸው ተመልሰዋል። ሆኖም በቃልቲ ያሉ የሌሎች ጋዜጠኞች ህይወት አሁንም እንደሚሳስባቸው ይናገራል ዮሃን ፔርሰን፣
«በርግጥ ከእስር በመለቀቃችን እድለኞች ነን። ሆኖም ግን አዕምሮያችን እረፍት አላገኘም ምክንያቱም ብዙ ባልደረቦቻችን አሁንም እዚያው ናቸው። ብዙን ጊዜ በምን ዓይነት ሁኔታ እንዳሉ ራሴን እጠይቃለሁ። አሁንም እዚያው ናቸው። ምክንያቱም እዚያ ከገባህ ጥሩ ስፍራ አይደለም። በዚህ እስር ቤት መሞት ቀላል ነው። እኛ ከመንግስታችን ባገኘነዉ ትልቅ ድጋፍ ነጻ ወጥተናል። በርካቶች ግን አልታደሉም አሁንም እዚያው ናቸው። »
ማርቲንና ዮሃን ቃልቲ ሳሉ ሌሎች እስረኞች አስፕሪንና ሌሎች መድኒቶችን ለማግኘት «የስዊድን ኤምባሲ» የሚል ስያሜ ወደተሰጠው መኝታ ስፍራቸው ይመጡ እንደ ነበር በፈገግታ ያስታውሳሉ። የኦጋዴን በረሃና የቃሊቲ እስር ቤት ገጠመኞቻቸውን የሚተርክ መጽሐፍ በጥቂት ወራት ውስጥ ሲያሳትሙ ገቢው በኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዳ ተቋም ለማቋቋም እንዲውል አቅደዋል፤
«እዚህ ስዊዲን ትልቅ ድጋፍ አለን። ህዝቡ 170 ሺ ዩሮ አሰባስበውልናል። ይህ ገንዘብ እስር ቤት እያለን በጣም ረድቶናል። በተቀረው ገንዘብ አንድ ቀና ተግባር ለመፈጸም አስበናል። ከመጽሃፉ ሽያጭ በሚገኝ ገቢም የዮሃንና ማርቲን ተቋምን አቋቁመን፣ በዚያ አስቀያሚ ሁኔታ የሚኖሩትን ጋዜጠኞች በመድሃኒት፣ በምግብና በህግ ድጋፍ ለመርዳት አቅደናል። እናም ወደ ፊት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና ቤተሰቦቻቸው ለተቋሙ በማመልከት የገንዘብ ማግኘት ይችላሉ።»
ገመቹ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ

No comments:

Post a Comment