Translate

Sunday, January 13, 2013

ፅናት እንደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች



እንደገና ጩኸት፣ አንደገና ዋይታ እንደገና ግድያ  በሀረር ከተማ! ባለፈዉ ሳምንት ሙስሊም ወገኖቻችን በሰላማዊ ተቃዉሞ ያቀረቡትን መበታችን ይከበር የሚል ጥያቄ ወያኔ አንደለመደዉ ነብስ ያላወቀ የሰባት አመት ልጅ በመግደል አረመኔያዊ መልስ ሰጥቷል። ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ታዳጊ ህጻን ላይመለስ በወያኔ ጥይት ተገድሏል፤ ረጅሙ ተስፋ ከዚህበፊት እንደተጨፈጨፉት ለጋ ህጻናት በወያኔ ጥይት ህይወቱ በአጭር ሊገታ ግድ ሆኗል።
የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን “በእምነታችን ላይ የዘረኛው ወያኔ የደም እጅ ጣልቃ ገብነት በአስቸኳይ ይቁም! የሃይማኖት ነጻነት ይከበር! “ሲሉ እያሰሙ ያሉት ተቃውሞ 365 ቀናትን በማስቆጠር በመላው ሀገሪቱ ተስፋፍቶ በሀረር የ7 አመት ህጻን ልጅና ወላጅ እናቱ የጨካኙ ወያኔ የጥይት ሰለባ በመሆን ወያኔ መንበረ ስልጣኑን እንደያዘ ለመቀጠል የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ እየሞተ ነጻነቱን ለማስከበር የሚደረገው ግብግብ ቀጥሏል።
በአወልያ የተጀመረውና ዛሬ ወደ ሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የተዛመተውና አሁን ወደክርስትና  እምነት ተከታዮችምም እያጠቃለለ ያለው የድምጻችን ይሰማ አመራሮች ጥያቄ ዛሬም ለነጻነታችን እንታገላለን እየሞትን እንወለዳለን፤ ወያኔ ለነጻነት ለጥያቄያችን የጥይትምላሽ እየሰጠ  ወገኖቻችንን እየጨፈጨፈ ቢሆንም ለቀቆምንለት አላማ፤  ለእምነታችን ነጻነትና፣ ለማንነታችን ባይተዋር ሳንሆን ትግላችን ድል እስከተገኘ ድረስ ይቀጥላል ሲሉ ለወያኔ በድጋሜ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።
ይሁን እንጅ ቅንጣት ያህል ለዜጎች መብት መከበር ደንታ የሌለው ወያኔ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት በመቅጠፍ፣  ርህራሄ የሌለው ግፈኛ መሆኑንና በስልጣኑ የሚመጣበትን ለመመከት ማናቸውንም ወንጀሎች ከመፈጸም እንደማይመለስ ለማሳየት የአርፋችሁ ተቀመጡ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ህጻናትን በመግደል የአውሬነት ባህሪውን ቀጥሎበታል።

ዛሬ በመላው አለም የዜጎች መብት ተብለው የተደነገጉት የንግግር፣ የመሰብሰብ፣ የመጻፍ፣ የመጠየቅ፣ የመምረጥና የመመረጥ ነፃነቶች በእኛ ሀገር ወይም በወያኔ መንደር እነዚህን መብቶች መጠየቅ የሽብርተኛ  ታርጋ የሚያስለጥፍና  የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት የሚያስቀጥፍ መሆኑ እየታየ ነው።
የእስልምና እምነት ተከታይ  ወገኖቻችን ላለፉት 365 ቀናት ለነጻነት ባላቸው ቆራጥነት፣ ፅናትና ፍቅር የተነሱለትን አላማ ከግብ ለማድረስ የትግል ስልታቸው አይሎ ከፍርሃት አረንቋ በመውጣት የሃይማኖት ነጻነት ይከበር ዘንድ በአንድ ድምጽ ትግላቸውን ቀጥለዋል፤ ይህም ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ትምህርት እየሰጠ በየአቅጣጫው የመብታችን ይከበር ጩኸቶች እየተነሱና እተፋፋሙ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ህዝብ የሙስሊሙ ህብረተስበ ጥያቄ የመብትና የነጻነት ጥያቄ መሆኑን ተረድቶ ትግሉን በመቀላቀል የአገሩን አንድነትና የራሱን መብትና ነጻነት እንዲያስከብር ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገራዊ ጥሪ ያደርጋል።
የዜጎችን የነጻነት ጥያቄ በወያኔ የጥይት አፈ ሙዝ ከቶ ማፈን እንደማይቻል የተረዱት ወያኔዎች፤ የእርስ በርስ ብጥብጥ ለማስነሳት ሙከራዎችን ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ራሱ ወያኔ እንጅ ሌላ አለመሆኑን ተረድቶ ህዝቡ ከዚህ የህወሃት መሰሪ እቅድ መጠንቀቅ ይኖርበታል።
ህዝቡ ነፃነቱን ለመከላከል አቅም የሚሰጡትን የራሱን ነጻ ማህበራዊ የእምነት ተቋማትን የሚያጠናክርበትን ግንባታ በንቃት መስራት ያስፈልገዋል። በተለይም አሁን በኦርቶዶክስ እምነት እየተስተዋለ ያለውን የወያኔን ጣልቃ ገብነት ለመታገል ህዝበ ምእመናኑ  በአንድ ድምጽ የሃይማኖታችን ነጻነት ይከበር ዘንድ እንደሙስሊሙ ወገናችን እጅ ለእጅ ተያይዞ በሀገራችን ሰላም፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ነጻነት እና አንድነት እንዲኖር በጽናት መታገል ያስፈልገዋል።
መደገገፍና ሰበአዊነት ከባህላችን የወረስናቸው ሲሆኑ፣ ለቆምንለት አላማና ለሃገራችን፣ ለነጻነታችን፣ ለአንድነታችን በእምቢተኝነት የምንታወቅ እኛ ኢትዮጵያውያን አሁንም ለወያኔ በየቦታው ጣልቃ ገብነትና ከፋፍለህ ግዛ ድርጊት በዝምታ እጃችንን አጣጥፈን ልንመለከተው አይገባም።
የሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ እንዲሁም የኢትዮጰያ ወጣቶች ስብስብ የሆነው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ጨምሮ እየተናገሩት ያሉት፤ ነጻነትና ፍትህ፣ መልካም አስተዳደር፣ ሰርቶ ማደግ፣ እኩልነትና ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብትና ሌሎች፣ በዜግነት የሚገኙ መብቶች እንጅ አምባገነኖች የሚቸሩህ ችሮታዎች አይደሉምና ለቆምንለት አላማ በጋራ በጽናት በመታገል ለቀጣዩ ትውልድ መልካም አሻራን ለመጣል አሁን ተነሱ ነው ጥሪው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ህዝባችን እንደሙስሊሙ ወገኑ በጽናት እየታገለ የሚያስፈልገውን መሰዋእት በመክፈል የህዝብ፣ የሀገር እድገትንና ደህንነትን አንቀው የያዙ ዘረኞችን በማስገደድ አሊያም በማስወገድ ለሀገራችን ነጻነትና የዴሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ ፈር ቀዳጆች እንሁን ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

No comments:

Post a Comment