የበረከት-አዜብና የስብሃት ፍጥጫ (ከእየሩሳሌም አርአያ)
በሽማግሌው ስብሀት ነጋና በረከት ስምኦን መካከል ስር ሰዶ የቆየው የውስጥ ሽኩቻ እየከረረ ሔዶአል ።አዜብ መስፍን ከበረከት ጎንተሰልፈዋል። አዜብ ለፓርቲው ሊቀምንበርነት «ይመጥናሉ» ያሉዋቸውንና «መለስን ይተካሉ» ሲሉ በድፍረት የተሟገቱላቸው ሁለት አመራር አባላት ተቀባይነት አለማግኘታቸው አበስጭቶአቸዋል አዜብ የጠ/ሚ/ር እንዲሆኑ የተሟገቱላቸው ቴዎድሮስ አድሀኖም ከእጩነት ራሳቸውን በማግለል ኩም አድርገዋቸዋል።
ሕወሀትን ከጀርባ በማሽከርከር የሚታወቁት ስብሀት ነጋ ለቀጣዩ ፍልሚያ ሀይል እያደራጁ ነው። ለበረከት ያላቸው ጥላቻ-ንቀት ጭምር የተላበሰ ነው። አዜብን ለመበቀል ግዜው አሁን እንደሆነ አረጋግጠዋል።የስብሀትና አዜብ ቁርሾ የተጠነሰሰው ከአምስት አመት በፊት ነበር። በወቅቱ የተወሰኑ የህውሀት ማ/ኮሚቴ አመራሮችን የሰበሰቡት አዜብ«ስብሀት ከኤፈርት ሃላፊነቱ መነሳት አለበት » ይላሉ። ትእዛዙንየተቀበሉት እነቴዎድሮስ ሀጎስ መልእክቱን ለሽማግሌው ያደርስሉ።
ስብሀትም በቁጣ«ጉአል ጎላ ክትቅመጠሉ ድያ?ሞይተ ድየ ብደወይ?» ማለትም «የጎላ ልጅ ልትቀመጥበት ነው? ሞቼ ነው በቁሜ?» ነበር ያሉት። «የሚስቱን ትእዛዝ ሳያወላዳ ተግባራዊ ያደርጋል» ሲሉ በገረሜታ የሚገልጹአቸው መለስ በወቅቱ በአዜብ የቀረበውን ስብሀት ነጋን የማስነሳት ሀሳብ ከመተግበር ወደሁዋላ አላሉም።«ፉከራ»ብቻ ሆነው የቀሩት ሽማግሌው ከኤፈርት፣በሁዋላም ከፓርቲው አመራር እንዲወጡ በማድረግ አዜብ የበላይነታቸውን አሳዩ።
ስብሀት ነጋ ከስልጣን ከተነሱ በሁዋላ የባልና ሚስቱን ስም እየጠቀሱ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከማውገዝ አልቦዘኑም። አዜብ ከሽማግሌው አልፈው «ታማኝ» የተባሉ ጄኔራሎችን ሳይቀር ከሀላፊነት እንዲወገዱ አድርገዋል። ከነዚህም ጄ/ል ወዲ አሸብር እና ጄ/ል ዮሀንስ(ጆኒ) ሲጠቀሱ፣ የዛሬ አምስት አመት ለጄ/ል ሳሞራ በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ወዲ አሽብር ለአንድ አመት የቁም እስረኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል።በወቅቱ አስገራሚ ሀይለ ቃል እስከመለዋወጥና እስከ መዘላለፍ ደርሰዋል። ከአመት በሁዋላ ወደ ስራቸው ቢመለሱም ብዙ አልቆዩም።ሁለቱን ጄኔራሎች ጨምሮ ሰባት ከፍተኛ የቀድሞ የህውሀት አባላት ጄኔራሎች እንዲባረሩ ተደረገ።
በሌላም በኩል የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሀላፊ ወ/ስላሴ ለረጅም ወራት ታግዶ ከቆየ በሁዋላ ወደቦታው እንዲመለስ ተደረገ። የታገደው የስብሀት ነጋ ደጋፊ ነው ተብሎ ነበር። ብዙዎቹ በዚህና በአንጃ ደጋፊነት እየተፈረጁ ሲያበቁ እግዱ ተነስቶላቸው የሚመለሱበት፣ በሁዋላም ጠቅልለው የሚወጡበት አካሄድ ለፓርቲው ቅርብ ለሆኑ አባላት ጭምር ግራ ያጋባ እንቆቅልሽ እንደነበር ይጠቁማሉ። አዜብ ብዙ ርቀት ለመጝዋዝ የጣሩት የስብሀትን አካሄድ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር። ነገርግን ያሰቡትእቅድ ሙሉ ለሙሉ ሳይሳካ የአሁኑ ጠንካራ ፍልሚያ ላይ ደርሰዋል።ስብሀት ከፓርቲው ሲለቁ «የእኔ» የሚሉአቸውን ሰዎች ቁልፍ ቁልፍ ቦታ እንዲጨብጡ አድርገዋል።
የህወሀት ማ/ኮሚቴ ውስጥ የስብሀት ሁለት እህቶች አሉ።የፌደራል ደህንነት ቢሮ የሚመራው በጸጋዬ በርሄ (ሀለቃ)ሲሆን፣ የጸጋዬ ባለቤት ቅዱሳን ነጋ፣ የስብሀት ነጋ ታናሽ እህት ናት። ስብሀት በአዜብና በረከት ላይ ለከፈቱት የውስጥ ዘመቻ ከጎን ካሰለፉት አንዱ አርከበ እቁባይ ይገኙበታል።አርከበ ከአዜብ በተደጋጋሚ የደረሰባቸው ጥቃት ለመጠጥ ሱሰኝነትና ብስጭትዳርጎአችው ቆይቶአል። የእግዜር ሰላምታ መለዋወጥ ካቆሙ ክርመዋል። ስብሀት አርከበን ከጎን ሲያሰልፉ ሌላም አላማ አንግበው ነው።
ይኽውም የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነቱን ስልጣን ይረከባል ተብሎ የሚጠበቀው አቶ ብርሀነ ገ/ክርስቶስ ታናሽ እህት ንግስቲ ገ/ክርስቶስ የአርከበ ባለቤት ናት። ብርሀነ የነበረው ወዳጅነትና ታማኝነት ከመለስ ጋር አብሮ ምእራፉ ተዘግቶአል። የፍጥጫው አንዱ አካል የሆነው የመከላከያ ጄነራሎች ሹመት ይገኝበታል። በአንዳንድ ወገኖች የሚሰነዘር ተገቢ ጥያቄ አለ።«የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠ/ሚ/ር በሌለበት እንዴትና በማን ሹመቱ ተሰጠ? ጸደቀ?» የሚል ሲሆን፣ ለዚህ ደግሞ ከመንግስት አፈ ቀላጤዎች የሚስጠው ምላሽ ሹመቱ ቀደም ሲል በአቶ መለስ የጸደቀ እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ይህ ግን ውሀ የማይቕጥር ነው ሲሉ የመከላከያ ምንጮች ማስተባበያውን ያጣጥላሉ። ምክንያቱንም ሲያስረዱ ከተሾሙት ጄነራሎች መካከል በአንጃነት ተፈርጀው የቆዩ፣ በመለስ በጥሩ አይን የማይታዩና ለረጅም አመት ለእስር የተዳረጉ እንዳሉም ይገልጻሉ። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ መለስ እነዚህን ይሾማሉ ብሎ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ ነው ሲሉ ያክላሉ። እርከን ጠብቀው የተሾሙ እንዳሉም ይጠቁማሉ። ቢሆንም ግን ህገ መንግስቱን ያልተከተለና ተገቢውን መንገድ የልተከናወነ ሹመት እንደሆነ አልሽሽጉም።
የብ/ጄኔራል ሹመት ከሰጣቸው አንዱ ኮ/ል አታክልቲ በርሄ ይገኝበታል። ከዚህም ቀደም ባቀረብኩት መጣጥፌ «መለስ ካጠፋቸው የፓርቲው አባላት»ይኸው ኮ/ል እንደሚገኝበት ጠቅሼ ነበር። በተሰነይ ግንባር ከፍተኛ ጀግንነት የፈጸመው ኮ/ል አታክልቲ ከጦርነቱበሁዋላ መለስን ሀይለ-ቃል በመናገሩና በማውገዙ እስር ቤት ወርዶ ለረጅም አመት ድምጹ ጠፍቶ ቆይቶአል።በ 2000 አ.ም ከእስር ተለቆ እንደቆየና በቅርቡ የብ/ጀነራልነት ሹመት አግኝቶ በተሻለ ሀላፊነት ላይ መቀመጡ ታውቆአል።
ሌላዋ የሴት ጄነራል ተሿሚ አስካለ ብርሀኔ ትባላለች። ህወሀትን የተቀላቀለችው ከበርካታ ታዳጊ እኩዮችዋ ጋር ሲሆን ጊዜው ደግሞ ግንቦት 1970 አ.ም ነበር። አብረዋት ጫካ ከገቡት ሴቶች ሁሉም ማለት ይቻላል በነመለስ ተገፍተው ሜዳ ተጥለዋል። ጀነራል አስካለ ይህን ሹመት ማግኘትዋ አስገራሚ የሚያደርገው ነጥብ አለ። የቀድሞ አየር ሀይል አዛዥ ጀ/ል አበበ (ጆቤ)ባለቤት ስትሆን ፣ጆቤን ጨምሮ የጦር አዛዦችና ከፍተወታደራዊ መኮንኖች እንዲባረሩ የተደረገው በመለስ ህገወጥ ውሳኔና ፊርማ እንደነበር ምንጮቹ ያስታውሳሉ።
የጄ/ል አስካለ ባለቤት- እህት ከተባረሩትና ከተንገላቱት መካከል ይጠቀሳሉ። የህወሀት ፖሊት ቢሮ አመራር የነበሩት አለምሰገድ ገ/አምላክ ባለቤት ሀመልማል ተ/ሀይማኖት ስትሆን ጋዜጠኛ ሀመልማል የጄ/ል አበበ ተክለሀይማኖት እህት ናት። ከራዲዮ ፋና እና ከፓርቲው እንድትባረር የተደረገው ባለቤትዋ ከመለስ ጋር በመለያየታቸው እንዲሁም ወንድሟ በመባረሩ ነበር።
በሌላም በኩል በአንጃ ደጋፊነት ተፈርጀው ከቆዩትና በመለስ በጥሩ አይን ከማይታዩት መካከል ፍስሀ በየነ፣አብርሀም አረጋይ፣የማነ ሙሉ፣ማአሹ ሀጎስ፣ግኡሽ ጽጌና ገብሩ ገ/ሚካኤል የብ/ጀነራልነት ሹመት ካገኙት ይጠቀሳሉ።አብዛኞቹ በሎጀስቲክ መምሪያ ሲሰሩ የቆዩ ናቸው። ከዚሁሉ ጀርባ እጃቸውን አርዝመው የሹመቱን ሚና የከወኑት ስብሀት ነጋ እንደሆኑ ሲታወቅ በሁለቱ ባላንጣዎች ላይ (አዜብና በረከት)የጥፋት ሴራ ማዘጋጀቱን ገፍተውበታል።
በደብረ ዘይት የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ሹም ጄ/ል ወዲ ዳኘው በሚመራው መንግስታዊ ተቛም አቶ ቢተው በላይ ስራ መጀመራቸው ታውቛል። በመለስ ታግደውና ታስረው የነበሩት ቢተው ቁልፍ በሆነ ቢሮ መመደባቸው ሚስጥሩ ስብሀት ነጋ እንደሆኑ ተጠቁሟል። የሜ/ጄነራልነት ሹመት ካገኙት አንዱ መሀሪ ዘውዴ ሲጠቀሱ የፓርቲው አባላት «ወዲ ዘውዴ» እያሉ የሚጠሩአቸው እኚህ ጄ/ል ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የሳሞራ ቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሎአል።
በመጨረሻም በመከላከያ ቢሮ የምስራቅ እዝ ዋና እዛዥ ሆነው የቆዩት ጄ/ል ባጫ ደበሌ ባለፈው አመት በእረፍት ሰበብ ከሀላፊነት እርቀው እንዲቆዩ ከተደረገ በሁዋላ በዛው እንደተባረሩ ተገልጾላቸዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እንዳሉ ሲታወቅ የት ከተማ እንዳሉና ለምን እንደመጡ ማወቅ አልተቻልም።
No comments:
Post a Comment