Translate

Thursday, January 31, 2013

Indian, Ethiopian activists against land grabbing meet in New Delhi


Indian, Ethiopian activists against land grabbing meet in New Delhi

Lagos, Nigeria – The Indian Social Action Forum (INSAF) and the Oakland Institute in the US will convene a day-longEthiopian Govt Sells Off Arable Land While People Starve summit on 6 February at the India International Centre, New Delhi, bringing together activists resisting land grabs across India and Ethiopia.
In a press statement, received here Thursday by PANA, organizers said the meeting will be a ground-breaking opportunity for dialogue between Ethiopian small farmers and land rights activists and their Indian counterparts, providing space for those directly affected by land grabs to share their experiences, suffering, and collectively strategise to challenge institutional and corporate land grabbers.

የኢትዮጵያዊነት ልዩ ውበትና አንድነት እስከ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ የመብት ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች የተንጸባረቁበት 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ


Sports had the power “to change the world … to inspire … to unite people.”
Nelson Mandela
በፍቅር ለይኩን
Ethiopian footballer adane girma
የ1998ቱ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ስፖርት ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለአንድነት… ወዘተ ያለው አዎንታዊ ፋይዳ በግልፅ የታየበት መድረክ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡

ነፃ የወጣው የኦሮሞ ነፃ አውጪ


ነፃ የወጣው የኦሮሞ ነፃ አውጪ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
ቀስ በቀስ ደረጃ በደረጃ የሰከነ የሃሳብ እድገት፣ ብስለትና መረዳት ከዘመናት ለውጥ ጋር መሻሻልን መፍጠሩ እውነት ነው። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማኖር፣ ይልቁንም ደግሞ በነፃነት ለመኖር ከወራሪዎች ጋር በተደረገ ትግል ሁሉ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተንቀሳቅሰዋል። ለዚህ ታሪክ ሥሪት የኦሮሞ ልጆች ያልከፈሉት መስዋዕትነት አልነበረም። ኢትዮጵያን ግብርና መራሽ ኢኮኖሚ እስከዛሬ ካቆያት ደግሞ ያለ ኦሮሞ ኢትዮጵያ የለችም። የዚያኑ ያህል ኢትዮጵያ ምሉዕ የምትሆነው ከየትኛውም ዘር ይፈጠር ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ክብር፣ እኩል መብትና ነፃነት ሲኖረው ነው።
በአንድ የዘመን ቅንፍ ውስጥ የተፈጠሩ የስህተት መንገድን እውነት ብለው የተቀበሉ የኩረጃ ትውልዶች ስለነጻነት ያነበቡትና ስለመገንጠል ተገነዘብን ያሉትን አምጥተው የሀገራቸውን አመሰራረትና ታሪክ ሳይሆን የአውሮፓ ታሪክን ባዩበት ዐይን እንደ ሰው ያስከበራቸውን ኢትዮጵያዊነት ኮንነዋል።

Wednesday, January 30, 2013

“የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው”


“የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው”

ሻዕቢያው በረከት ህወሃትን ሊነዱት ይሆን?
bereket vs sebhat


የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ መውጣቱን የሚያመላክት መረጃ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በህወሃት መንደር ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት ልዩነቱን ለማርገብ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም።

Tuesday, January 29, 2013

የጎልጉል ቅምሻ


የጎልጉል ቅምሻ

(ከዚህም ከዚያም)
lisa


“የድመት ጸጉር የመብላት ሱሰኛ ነኝ”
የሱሰኛነት ነገር ሲነሳ ሰሞኑን ከወደ ሚሽጋን ጠቅላይግዛት የተሰማው ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ የ43ዓመቷ ሊሳ በቀን ሦስት ሩብ መጠን ያለው የድመት ጸጉርጥቅል እንደምትበላ ተናግራለች፡፡

ለ “የጣመ ውይይት” ምላሽ


ለ “የጣመ ውይይት” ምላሽ

ማስታወሻ፥ ከግብጽ ወጣቶች ምን እንማራለን
tahrir_sq_protest_BBC
እኛ የመጨረሻዎቹ የሚል አንድ ጽሁፍ በድረ ገጾች የሚሽከረከር አይቼ፣ እውን እንዴት ቀን ቀንን ዓመት ዓመትን እየተካው ዓለም ምንኛ በተጨባጭ በግብርም፣ በሃሳብ በመንፈስም እንደተሽከረከረች እንደገና ልብ ብዬ ነበር። እኔም የትላንት ሰው ስለሆንኩ።

እግርኳሳችን የራሷን ሙሴ ትፈልጋለች


እግርኳሳችን የራሷን ሙሴ ትፈልጋለች

game
ስሜት ጎርፍ ነው፤ ያውም ደራሽ ጎርፍ፤ ብሄራዊ ቡድናችንን ስንደግፍም ሆነ ስናወድስ እንዲሁም ስንወቅስ በዚሁ ደራሽ ጎርፍ መወሰዳችን ይታያል። ይሄ ችግር ግን እንደ ሃገርም ችግራችን እየሆነ የመጣ ነገር ነው በስሜት መደገፍ በስሜት መቃወም፤ ዛሬ ያወደሱትን ነገ መርግም ሁሉንም ነገር በዘላቂ ጥቅም፤ በዘላቂ ስራ እና በዕውቀት መመዘን እያቃተን ነው። ከዚያም ዐልፎ ስሜታችን ጫፍ ላይ በሚደርስበት ጊዜ ሰከን ብሎ የሚያስብ ሰው ሲያጋጥመን እንደጭራቅ እንመለከተዋለን። ከእኛ በሓሳብ የተለየ አስተያየት የሰጠ እንደሆነማ በቃ ቤተክርስቲያን ውስጥ የገባ ውሻ እናደርገዋለን።…

ሒትለርና አይሁድ፤ መለስ ስብሀትና አማራ


ሉሉ ከበደ

ውድ አንባቢያን “ዘራፊ ሚሊየነሮች” ለሚለው ጽሁፍ ካደረሳችሁኝ መልሶች አጠር ያለውን አንዱን እንመልከትና ወደሚቀጥለው ጉዳይ እናመራለን።
ወዳጄ ስለነዚህ እርጉም ሰዎች የጻፍከዉን ከማህደሬ አዉጥቼ ዛሬ አነበብኩት። እግዜር ይስጥህ። ምን እላለሁ። አፍዝ አደንግዝ እንደተደረገብን ሁሉ ዝም ብሎ ማየት ሁኗል ።ጉርሻ በሚሸጥበት አገር ሰዉ በቁንጣን አለቀ ሲሉን ለማመን ይዳዳናል። ምን አይነት እርጉም ወራዳ ትዉልድ እንደሆንን ነዉ የሚያሳየዉ።  የትግሬ እና የሻቢያ ምሁራን ቀጥፈዉ ዋሽተዉ በድፍረት የሌለ ታሪክ ታሪክ አድርገዉ ተከታዮቻቸዉን እያሳመኑ ነዉ። የእኛ ምሁራን ደግሞ ሲሞዳሞዱ ጥቅም አይቅርብን ብለዉ ሲልከሰከሱ ስለኢትዮጵያ ከሞላ ጎደለ የሚጽፈዉ ያዘነልን ነጭ ሁኗል።  ቢያስቡት ቢያስቡት መልስ የሌለዉ ነገር ነዉ። ነገር ግን ትግሬን ምን አደረግነዉ? ትግሬ ከሌሎች ወገኖች በላይ የደረሰበት በደል ምንድነዉ? ኢትዮጵያን ሊያጠፋ የተነሳበት ምክንያት ምንድነዉ? የሚለዉ ነገር ሁልጊዜ ጥያቄ ዉስጥ ይከተኛል።

ሕወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ


ከኢየሩሳሌም አርአያ

ዛሬ በመቀሌ ለአባላ ትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩTigray People Liberation Front Split በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ» ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤
«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤
«ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።

Monday, January 28, 2013

Genocide Watch President Speaks out on TPLF/EPRDF Terrorism (video)


Genocide Watch President Speaks out on TPLF/EPRDF Terrorism (video)

Genocide Watch exists to predict, prevent, stop, and punish genocide. Prof. Gregory Stanton is president of Genocide Watch.
Related story:

Ethiopian Regime Expands its State Sponsored Terrorism to the United States

Amnesty International, Human Rights Watch, the UN, the U.S. Department of State, Genocide Watch, and Committee to Protect Journalists (CPJ) have documented many of these human rights violations committed by the incumbent criminal regime in Ethiopia.Read more…

ስልጣንና ንግድ በህውሃት መንደር


27/01/13

Author and writer Tesfaye Zenebe from Norway
ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)
አመልና ልማድ የትም ቢሆን አይለቅምና  ከሃገርና ከህዝብ መዝረፍ የለመደው የወያኔ ህውሃት ቡድን ድንበር ተሻግሮ በኢትዮጲያ  ቴሌቪዥን አማካኝነት ያልከፈለበትን የ29ኛው የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ማስተላለፉ ከነሱ አልፎ ቤሄራዊ ክብራችንን የሚነካ የወረደ ተግባር መሆኑ አስረጂ አያስፈልገውም፡፡ ስለሆነም  በካፍ መግለጫ መሰረት የኢትዮጲያ ቴሌቪዥን በዚህ ሳይከፍል ሰርቆ ባስተላለፈው ስርጭት ላይ የሃገር ውስጥ እስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶችን እየጠራ ተጨማሪ ገቢ ማግኘቱ ሌላው አሳፋሪ ተግባሩ  ነው፡፡ የኢትዮጲያ እግር ኳስ ቡድን ከ31 ዐመታት በሗላ ለዚህ መድረሱ ህዝቡን ቢያሰደስተውም  ጫወታውን በቀጥታ ለማስተላለፍ ግን የወያኔ መንግስት  አቅም የለኝም ማለቱ ጫወታውን በጉጉት ለሚጠባበቀው ህዝብ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ 18 ሚሊዮን ብር እንኳን በዘረፋ ለደለበ የወያኔ ቡድን ቀርቶ ስርዓቱ ላፈራቸው ህገወጥ ባለሃብቶች በጣም ቀላል እንደ ሆነ ብዙዎች ይሰማማሉ፡፡ሆኖም ምኑም ባለየለት ምክንያት  ህገወጥ ስርጭት በማስተላለፍ ቤሄራዊ ክብርን  ማስነካት ይቅር የማይባል በደል መሆኑን ልብ ሊባል የገባዋል፡፡

Sunday, January 27, 2013

« ፍቅረኛሞቹ» አዜብና ብርሃነ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


አዜብ መስፍንን ከሱዳን አምጥቶ ሕወሓትን እንዲቀላቀሉ ያደረገ ነው። የፍቅር ግንኙነትም ነበራቸው። ይህ ሰው ብርሃነ ኪዳነማርያም (በቅፅል ስሙ ብርሃነ-ማረት) ነው። አዜብና ብርሃነ ድርጅቱን ሲቀላቀሉ የተቀበሏቸው አቶ አስገደ ገ/ስላሴ (አሁን የአረና አባል) ነበሩ። ጥቂት የበላይ አመራሮች በሁለቱ የፍቅር ግንኙነት ዙሪያ መከሩ። ከዛም የብርሃነና የአዜብ ግንኙነት እንዲቋረጥ በማድረግ ከለያዩዋቸው በኋላ ከመለስ ዜናዊ ጋር አዜብ እንዲጠቃለሉ ሆነ። (በነገራችን ላይ አንዳንድ ወገኖች አዜብና ሟቹ ክንፈ ገ/መድህን በጫካ ግንኙነት እንደነበራቸው ተደርጎ የሚነገረው ከእውነት የራቀ እንደሆነ የቅርብ ታማኝ ምንጮች ይገልፃሉ፤)

ወደ ዋናው ርዕሰ ጉዳይ እናምራ፥ በሕወሓት ውስጥ አድፍጠው መሰሪ ተግባር ከሚፈፅሙት አንዱ ነው ተብሎ በፓርቲው ወገኖች የሚፈረጀው ብርሃነ ኪ/ማርያም (ብርሃነ-ማረት) ማንነትና አደገኛ አካሄድ ምን እንደሚመስል ከላይ የተገለፀውን መንደርደሪያ ያስቀደሙ ታማኝ ምንጮች ተከታዩን ይላሉ።

ሰራዊታችን ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ፡ ብዛት ያላቸው ሴት ታጋዮችም ግንባሩን ተቀላቀሉ!


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ነበልባል ጦር ጥር 17-2005 ዓ.ም በወልቃይት ጎብለል በተሰኘ የወያኔው መከላከያ ካምፕ ላይ በወሰደው ድንገተኛ ማጥቃት በካምፑ የሚገኙ የመከላከያ አባላትን ደምስሷል። በውጤቱም 25 ሙት 36 ቁስለኛ እንዲሁም  20 ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ ፣ 4 የእጅ ቦንብና 1 ስናይፕር ጠብመንጃ ከነ ሙሉ ትጥቁ በመማረክ በማግስቱ ማለትም በትናንተናው እለት በቀጠለው የነበልባል ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት በወልቃይት ጠበቆ በተባለ ቦታ 24 የአገዛዙ ታጣቂዎች ሙትና 29 ቁስለኛ ሆኗል። በድምሩ በሁለት ቀናት ውጊያ በጠቅላላው 49 ሙት 65 ቁስለኛ ሲሆን፦ የአምባገነኑ አገዛዝ ሰራዊት የአርበኛውን ጡጫ መቋቋም ተስኖት እግሬ አውጭኝ ብሎ ከመፈርጠጡም ባሻገር የውጊያ ሞራሉ ክፉኛ በመዳከሙ ምክንያት በአድጎሹ ፣ አደባይ፣ሁመራና እድሪስ አካባቢ የሚገኙ የጦር አመራሮች በመሰባሰብ የመልሶ መቋቋም እንቅስቃሴ ላይ እንደተወጠሩ ታውቋል።

Saturday, January 26, 2013

ከአሜሪካ የህወሓት ሰላዮች ዛቻ


ከኢየሩሳሌም አርአያ


አሜሪካ የመሸጉ የሕወሐት ሰላዮች ዛቻና ማስፈራሪያ መሰንዘር ጀምረዋል። አልፈው ተርፈው «ክስ» እንመሰርታለን ብለዋል። ለማስፈራሪያቸው የሚበረግግ ባይኖርም – ነገር ግን ነፃነት ባለበት አሜሪካ ያሉ የፍትህ አካላት በብርሃነ፣ ስብሃት፣ በረከት፣ አዜብ አሊያም ሽመልስ….የሚሽከረከሩ መስሎዋቸው ያለሃፍረት አንደበታቸውን ሞልተው ሲደነፉና ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ መታየታቸው …ምን ያክል የሞራል ድቀት እንደተጠናወታቸው ያሳያል። ባለፉት ወራት ከተሰነዘሩ ተራ ስድቦችና ዛቻዎች የትላንቱ ለየት የሚያደርገው ነጥብ ስላለ ነው፥ ይህችን መልክት ለመፃፍ የተገደድኩት። እነዚህ ሰዎች አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የመሸጉ የሕወሐት ሰላዮች እንደሆኑ ላሰምርበት እወዳለሁ። ከጀርባቸው ብርሃነ እንዳለ በግልፅ በአንደበታቸው አረጋግጠውልኛል። ዋናው አላማቸው ደግሞ « ሳንጋለጥ..ቀድመን እናሸማቅ፤..» ከሚል ከንቱ አስተሳሰባቸው የመነጨ ነው።
እናንተ በንፁሃን ደም የታጠባቹ ወንጀለኛ የብርሃነ ጀሌዎች፥ የፈለጋችሁትን ብትደረድሩ እናንተን ከማጋለጥ ወደኋላ የሚያፈገፍግ ብዕር የለም!! በአሜሪካ ተቀምጣችሁ ከምትፈፅሙት የስለላ ወንጀል ባሻገር ያለው የጀርባ ጉድፍ ታሪካችሁ ገና አልተነካም። ከአገራችን ባህል ውጭ በሚያሳፍር ፀያፍ ተግባር ተዘፍቃችሁ … በሴት እህቶቻችን ላይ ስትፈፅሙ የነበረው የቡድንና የተናጠል…የአመንዝራ -ሴሰኛ ድርጊታችሁ የማይታወቅ መስሎዋችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል።

በደል እንዴት ይራሳል?



(ክፍል 1)
የኢትዮጵያ ህዝብ መስከረምን ከጥቅምት ወይም ታህሳስን ከጥር ጋር አወዳድሮ ይህ ወር ከዚህ ወር ይበልጣል ወይም ይሻላል ብሎ የሚያምንበት ልዩ ምክንያት ባይኖረዉም እያንዳንዱ ወር በመጣ ቁጥር ግን ይዞት የሚመጣዉ የራሱ የሆኑ ታሪካዊ፤ ባህላዊና ፖለቲካዊ ትዝታዎች አሉት። የቅርቡንም ሆነ ቆየት ያለዉን ታሪካችንን ወደ ኋላ ዞር ብለን ስንመለከት ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀልንና የዚያኑ ያክል ተስፋችንን አጨልሞ ጽልመት ዉስጥ የከተተን ወር ቢኖር ወርሃ ግንቦት ነዉ። አዎ ! . . .  ግንቦት የፖለቲካና የባህል ቁመናችንን የዳሰሱ አያሌ ክስተቶችን ያስተናገደ ጉደኛ ወር ነዉ።  . . .  ግንቦት ልደታ፤ ግንቦት 8፤ ግንቦት 20ና ግንቦት ሰባት በየአመቱ የግንቦት ወር በመጣ ቁጥር የምንዘክራቸዉ አገራዊ ትዝታዎቻችን ናቸዉ። ግንቦትንና እነዚህን ትዝታዎች የብዕር ሰዎቻችን በየዘመኑ ያነሷቸዋል፤ የኪነት ሰዎቻችን ቅኔ ይቃኙላቸዋል የየዘመኑ የታሪክ ድርሳኖቻችንም ይዘግቧቸዋል።
ግንቦት 7 1997 በኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ ትግል ታሪክ ዉስጥ ልዩ ቀን ናት። ግንቦት ሰባት አንድ ትዉልድ ብቻ ሳይሆን ሁለትና ሦስት ትውልድ የደም ላብ አልቦና የህይወት ግብር ከፍሎ በረጂም ዘመን የትግል ታሪከችን መዝገብ ዉስጥ የጫራት አብሪ ኮከብ ናት። አዎ! ግንቦት ሰባት የዲሞክራሲ ትግላችን  የከተባት ግዙፍ ክታብ ናት። ግንቦት ሰባት የ1940ዎቹ ትዉልድ አስቧት፤የ1950ዎቹና 60ዎቹ ትዉልድ አርግዟት የ1970ዎቹና 80ዎቹ ትዉልድ አምጧት የ1990ዎቹ ትዉልድ በጣር የወለዳት የኢትዮጵያ ህዝብ የበኩር ልጅ ናት። የኢትዮጵያ ሀዝብ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ያደረገዉ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ የዘመናት የነፃነትና የዲሞክራሲ ረሀቡ ዉጤት፤የአርቆ ማስተዋሉ ምልክት፤ወይም ከዉስጥ ሆዱ የመነጨ የፍትህ፤ የነፃነትና የእኩልነት ፍላጎት ዉጤት ነዉ እንጂ የመላምት ታሪክ ቱልቱላዎች ሹክ ሊሉን እንደሚፈልጉት የወያኔ በጎ ፈቃድ ገጸበረከት አይደለም። ግንቦት ሰባት የአዋቂዉ መሳሳብ፤ የሀፃናት መተሳሰብ፤የምሁሩ መናበብና የወጣቱ መተሳሰብ “ቱሉፎርሳ” ብሎ ከዘረኞች ጓዳ በገመድ ጎትቶ እዉን ያደረጋት የዲሞክራሲ ትግላችን ተምሳሌት የሆነች ቀን ናት።

የሃይማኖት መብቶች እንዲከበሩ ለሁሉም መብቶች የመታገያ ግዜው አሁን ነው!



ፍትህ፣ ነጻነት፣ እኩልነትና አንድነት የብዙ ሃይማኖቶች መሰረታዊ መርህ  እሴቶች ናቸው። እነዚህ ቲውፊቶች ለአለፉት 20 አመታት በዘረኛው ወያኔ እየተሸረሸሩና እየመነመኑ ዛሬ ከእነ አካቴው በሀገራችን ኢትዮጵያ ስለመሰረታዊ የሰው ልጆች መብት ነጻነት እንዳይወራ፤ ወያኔ የጥይት አፈ ሙዞች በእያንዳንዱ የህዝብ አገልግሎት ተቋማት ላይ በመደቀን የአምልኮ ቦታዎችን ሳይቀር በመዳፈር ህዝበ ምእመናኑ የእኔ የራሴ የሚለው የአምልኮት ቦታ እና ህግ እንዲያጣና እንዳይኖረው እያደረገ ነው።
በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቀን ወደቀን እየተባባሰ የመጣው የእምነት ነጻነት እጦት ሁላችንንም ሊያሳስበን እና ሊያስተሳስረን የሚገባበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። በተለይም በታሪካችን፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በእምነት፣ በዘር፣ በፖለቲካ እስከ ቅርብ ጊዚያት ድረስ ሳይለያይ ተከባብሮና ተሳስቦ የሚኖር ህዝብ እንደሆነ የማይካድ ሃቅ ነው።
ይሁን እንጅ ከቅርብ ግዜ ወዲህ አምባገነኖች በፈጠሩት ህገ- አራዊት በሆነው የከፋፍለህ ግዛ እና የአንድ ዘር የበላይነት ፖሊሲ አማካኝነት የምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ አበው ለአንድነቷ፣ ለህልውናዋ የሞቱላት፣ ዘውግ፣ ቋንቋና የሃይማኖት ልዩነት ሳያግዳቸው የገነቧት እማማ ኢትዮጵያ፤ የልጆቿ የኤሎሄ ማሰሚያ ስፍራዎች፣ ተቋማትና የገዳማት አባቶች በህወሃት የጥፋት አለንጋ እየተገረፉ ናቸው።

በዳውሮ ዞን የህዝቡን ተቃውሞ መርተዋል የተባሉ ሰዎች ታሰሩ


ኢሳት ዜና:-በዳውሮ ዞን በማረቃ ወረዳ ከወረዳ እና ከሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ግጭት መርተዋል ከተባሉት መካከል አቶ ዱባለ ገበየሁ፣ አቶ ጎሳሁን ዶሳ ዶሻና አቶ ግዛቸው ታደሰ ከበደ በትናትናው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

በዞኑ የሚታየው አለመረጋጋት ያሳሰበው መንግስት ግለሰቦቹ በአካባቢው የሚደረገውን ተቃዎሞ በማደራጀት በኩል እጃቸው አለበት በሚል እንዳሰራቸው፣ ቤቱ ለፍተሻ በሄደበት ወቅት ያነጋገርነው በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኘው፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች ድርጅት የደቡብ ክልል ዋና አደራጅ አቶ ዱባለ ገበየሁ ገልጸዋል።
አቶ ዱባለ በክልሉ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር እርሳቸው የኢህአዴግ አባል በነበሩበት ጊዜ በተለይም የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የደኢህዴግ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ አሰፋ ቤተሰቦቹን እያሾመ ነው በማለት ገምግመዋቸው እንደነበርና አሁን የሚደርስባቸው ነገርም የዚያ በቀል መሆኑን ገልጸዋል
በአሁኑ ጊዜ ከአቶ ዱባለ ጋር በእስር ላይ የሚገኙት የማረቃ ወረዳ አቃቢ ህጎች መሆናቸውን አቶ ዱባለ ገልጸዋል
በማረቃ ወረዳ በማሪ አካባቢ ሰሞኑን በተነሳው የሕዝብ አመጽ ሕዝቡ በፖሊስ ላይ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።  ሻለቃ በዛብህ ገዝሙ የተባሉ የዞኑ ፖሊስ ከፍተኛ አመራርና አንድ ወታደር በድንጋይ ተደብድበዋል።  አንድ የመንግሥት መኪና ተሰባብሮ ከጥቅም ውጪ መሆኑና የመኪና መንገድ በመቆፈር ግንኙነት እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወሳል።

ድምጻችን ይሰማ የሚል ቲ-ሸርት ያደረጉ ሙስሊሞች ከስታዲየም ተባረሩ


ድምጻችን ይሰማ የሚል ቲ-ሸርት ያደረጉ ሙስሊሞች ከስታዲየም ተባረሩ


በትላንትናው ጨዋታ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ለመደገፍ የታደሙት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት የሙስሊሙ ማህበረሰቦች ድምጻችን ይሰማ እና እንዲሁም መሪዎቻችን ይለቀቁ የሚሉ ቲሸርቶችን ለብሰው በመታየታቸው በሰኩሪቲ ፖሊስ እየተለቀሙ ከስታዲየም ግቢ እንዲወጠ ተደርገዋል ። አብዛኞቹን ለጥያቄ እንፈልጋችኋለን በማለት የወሰዷቸው ሲሆን ሌሎቹን ደግሞ ይህንን ለብሳችሁ እዚግ ስታዲየም ውስጥ መቆም አትችሉም በማለት አስረግጠው ነግረረዋቸዋል ።ከደቡብ አፍሪካ የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ እንደአቀረበው ሪፖርት ከሆነ ማንኛውም የተቃውሞ የሚያሰሙ ነገሮችን በመንግስት ሃይሎች እና በኢትዮጵያ ኤምባሲ ትብብር ህብረተሰቡን ለመቆጣጠር እና መብቱ እንደተጋፉት ገልጾአል ።

ብስጭት በጨዋታ “…ቡርኪናፋሶ አበዛብኝ ለቅሶ!”


ብስጭት በጨዋታ “…ቡርኪናፋሶ አበዛብኝ ለቅሶ!”

ABE TOKCHAW
እንደምን አደራችሁ ብስጭት እናስነብባለን በመጀመሪያም አርዕስተ ብስጭት።
በትላንትናው ዕለት ብሄራዊ ቡድናችን ላይ በደረሰበት መጠነ ሰፊ ጥቃት በርካቶች መበሳጨታቸው ተሰማ።
በቅድሚያ፤
ብሄራዊ ቡድናችን፤ በደቡብ አፍሪካ ያለ ኮከብ በሚያበራው የኢትዮጵያ ባንዲራ፤ በባለ አንበሳው ሞአንበሳ ባንዲራ በባለኮከቡ የፌደራሉ ባንዲራ እንዲሁም በባለ ዋርካው የኦነግ ባንዲራ ምን እርሱ ብቻ በባለ ቀንበጡ የኤርትራ ባንዲራ ሁሉ ሲደገፍ ተመልክተን እማማ ኢትዮጵያ ብዙ ልጆች እንዳሏት አየን ደስም አለን!

ለላሊበላስ ማን ይድረስ?



የአማራ ሰማዕታት ሐውልት፤ ባህርዳር


የላሊበላ ውቅር አብያተ ከርስቲያናት የመፍረስ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ መነገር የጀመረው ዛሬ አይደለም። ቢያንስ ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት ያካባቢው ነዋሪዎች፣ በወፍ ዘራሽ ወደዚያ ያቀኑ ጋዜጠኞችና ለልቦናቸው የቀረቡ የገዳማቱ አገልጋዮች አስጠንቅቀዋል። ማስጠንቀቂያው ግዙፍና ዕረፍት የሚከለክል ቢሆንም ተግቶ ምላሽ የሰጠ አካል ባለመኖሩ፣ ጉዳዩን በመያዝ የተከራከረና ገዢውን ፓርቲ ያስጨነቀ የህዝብና የቅርስ ጠበቃ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ባለመገኘቱ “ለላሊበላ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች አንድ ናቸው” የሚል አስተያየት እየሰጡ ነው።

Thursday, January 24, 2013

የዋልድባ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለክልሉ መንግሥት አቀረቡ



ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ  ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ።  የሚደርስባቸውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በደብዳቤ የዘረዘሩት መነኮሳቱ ፤መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትንም ዝርዝር አቅርበዋል።
 <<መብታችን እየተጣሰ ስለሆነ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድልን ስለመጠየቅ>>በሚል ርዕስ ለክልሉ መንግስት ለሰብዓዊ መብት ኮሞሽን በጻፉት ሰፊ ደብዳቤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋልድባ የሚለውን ስም መጥራት ሁሉ የተለየ ይዘት እየተሰጠው  ይህን ስም የሚጠሩ መነኮሳት ሁሉ እየታሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል።
 መንፈሳዊ ቦታ ማንም  ያለ ዘር መድሎ የሚገለገልበት መሆን እንዳለበት ግልፅ ነው ያሉት መነኮሳቱ፤ በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻህፍት የተፃፉትን ለጊዜው ትተን የሀራችንን ሕገ-መንግሥትና ሌሎች የመንግሥት ሕግጋትን ብንመለከት  ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈለገበት የሀገሪቱ አካባቢ የመኖርና መብቱ እንዲጠበቅለት የመጠየቅ ሰብዓዊ መብት እንዳለው ተደንግጓል ብለዋል።

የህሊና እስረኞችን ለማነጋገር ወደ ቃሊቲ የተጓዘው የሽማግሌዎች ቡድን በተቃውሞ ተመለሰ



ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማስታወሻው ላይ እንዳሰፈረው ወደ ቃሊቲ በማምራት ርዕዮት አለሙን ያነጋገሩት ፓስተር ዳንኤል ‹‹የእስከዛሬው ተግባርህ የሚያስረዳው የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚክንፍመሆንህን ነው፡፡ ስለዚህም በምንም አይነት ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ አይደለሁም›› የሚልያልጠበቁትን መልስ በማግኘታቸው የይቅርታ አጀንዳውን ሳያነሱ ተመልሰዋል፡፡ የሙስሊሙማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በበኩላቸው ለፓስተር ዳንኤል እና ለፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ  ፦‹‹ያቀረባችሁትን የይቅርታ መጠየቅ ሀሳብ  በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነንም አንልም፣ አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› የሚል መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡
ከርዕዮትና ከሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ያልጠበቁትን መልስ ያጘኙት  የሽማግሌዎቹ ልዑካን፤ እስክንድር ነጋን ሳያነጋግሩተመልሰዋል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በግል የፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ሀሙስ ጥር 2 ቀን 2005 ዓ.ም በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ይመሩ ከነበሩት ሽማግሌዎችውስጥ የተዘጋጀ ሶስት ሰዎች ያሉት አንድ ቡድን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝቶ ነበር፡፡

Occupy Eritrean Embassy London

ልማታዊው ኪስ አውላቂ (ክንፉ አሰፋ)


ማስታወሻ፡  ባለፉት ጊዚያት በጫጫርኳቸው አጫጭር ጽሁፎቼ፤ ገንቢ ትችቶች ለላካችሁልኝ አንባብያን ሁሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው። በአንጻሩ አፍራሽ ትችቶች በስማችሁ ጽፋችሁ የላካችሁልኝ ወገኖችንም አደንቃለሁ። ነገር ግን በብእር ስም ራሳችሁን በመደበቅ፤ ነውር እና አሳፋሪ የሆነ የፈጠራ ስራ ለምትሰሩ ደግሞ፡ ልቦና ይስጣችሁ ከማለት ውጭ የምለው የለም። ሰውን ዘልፎ ለመጻፍ እንቅልፋቸውን የሚያጡ ሰዎችን ፈረንጆቹ ‘ባለ ትንሽ ጭንቅላቶች’ ይሏቸዋል። ችግሩ ከአስተዳደግ ጉድለት፣ ከአስተሳሰብ ድህነት እና በራስ ካለመተማመን የሚመጣ የስነልቦና በሽታ ነው።
ክንፉ አሰፋ

የ ‘ህዳሴው ቦንድ’ ግዢ ግርግር ሞቅ ብሎ በነበረበት ሰሞን ይነገር የነበረ አነድ ቀልድ አለ። የ‘ማረሚያ’ ቤት ፖሊሶች እና ታጋዮች 500 ብር በሰረቀ ሌባ ላይ ውይይት ያደርሉ። ተከሳሹ ብሩን ያላግባብ ይስረቅ እንጂ በገንዘቡ የህዳሴውን ቦንድ መግዛቱ ነው ጉዳዩን ለውይይት የዳረገው።  ይህ ሌባ መታሰር የለበትም የሚሉት ታጋዮች፡ ለፖሊሶቹ ያቀረቡት መከራከሪያ ነጥብ ልማታዊ ሃሳብ ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት፡ ‘ይህ ልማታዊ ኪስ አውላቂ ነው። እንዲያውም እንደዚህ አይነቶቹን ሌቦች የበለጠ እንዲሰሩ ማበረታታት ነው ያለብን።…’  ሁሉም በዚህ ሃሳብ ተስማሙና ሌባውን በያዘው ልማታዊ ተግባር የበለጠ እንዲሰራበት መክረው ለቀቁት።

አባ ሕዝቅኤል ለምን ስብሰባ ረግጠው ወጡ?


“የማንም አሿሿሚ አልሆንም የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም”በማለት አራት ወራት የቀረውን የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነታቸውን የሚለቁ መሆናቸውን በደብዳቤ ገለጡ እየተባለ ሰሞኑን

ethiopian orthodox church in Addis Ababa የሚወራላቸው አባ ሕዝቅኤል  ቀደም ሲልም ስብሰባ ረግጠው ቢወጡ የፈረሰው ቀኖና ይመለስ ብለው እንዳልሆነ መታወቅ አለበት
አባ ሕዝቅኤልና በአዲስ አበባ የሚገኙት የሲኖዶስ አባለት ለእርቅና ለሰላም እንዲሁም ለሀያ ዓመታት የዘለቀውን የቤተ ክርስቲያን መለያየት ወደ አንድነት ለማምጣት በቅንነት እና ግልጽ በሆነ መንገድ ቢጓዙ ኖሮ ለዚህ ለከፋ መከፋፈል እንዲሁም ለመንግሥት ጣልቃ ገብነት ባልተዳረጉ ነበር ይልቁንም አባ ሕዝቅኤል  የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አለ መባሉ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነና ቅዱስ ሲኖዶስ ለምርጫ የሚያስፈልጉ ደንቦችን ከማውጣት በቀር መንግሥት ጣልቃ አልገባም በማለት በአደባባይ ተናግረው ጸሐይ የሞቀውን እውነት የካዱ አባት ናቸው አቡነ ገብርኤልም ይሕንኑ ሀቅ ክደው በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በሰጡት ቃል የአባ ሕዝቅኤልን ውሸት ደግመውታል

ተከደነ ብቃት በዓለም አደባባይ ሲውል


“Eine große Überraschung”  EuroSprt

“አንድ አዲስ ያልተጠበቀ ብርቅዬ ነገር”

ከዛሬ የከሰዓት በኋላ ኢሮ ስፖርት ትንተና የተወሰደ
ከሥርጉተ ሥላሴ 22.01.2013
መቼም ፍቅር ከነተፈጥሮው የሚገኝበት ሚስጢር ከእናትና ከማልያ ላይ ብቻ ነው። የማልያ ፍቅር ተጫዋቹን ብቻ ሳይሆን ታዳሚውንም በሙሉ ፈቃደኝነት የሚሰደምም  … ዕጹብSouth Africa Ethiopian fans ድንቅ ጥበብ ነው። የበቃ!
እግር ኳስ የዓለምን ህዝብ በፍቅር ክንፍ የሚያደርግ ጨዋታ ነው። ሌላው ቀርቶ የእግር ኳስ ህግጋትን በሚመለከትም ከዳኞች ባላነሰ ታደሚዊቹ በቂ ዕውቀት እንዳላቸው እገምታለሁ። ስለምን? በእግር ኳስ ጨዋታ ታዳሚው በባለቤትነት ስሜት መንፈሱንና አካሉን በፈቃዱ ለድንቡልቡሏ ውብ ተዋናይ በውዴታ ስለገበረ፤ ሰለለገሰ በቀላሉ ሜዳ ላይ ባለው ትዕይንት ብቻ መማር ስለሚቻል።
የተቀባው እግር ኳስ ዕልፍ አዕላፋትን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በፍቅር ብቻ ቤተኛ

የጣመው ውይይት ፍሬያማ እንዲሆን ምን ይደረግ?


(ጋሻው አለሙ)

what to do
በእኔና በአቶ አንዱ አለም ተፈራ መካከል እየተደረገ ያለው ውይይት እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል::  እየተወያየን ያለንው የጋራ ስለሆነችው አገራችን የወደፊት የፖለቲካ ዕድገትና ሁለንተናዊ ለውጥ መምጣት ስለምንችልበትና አሁን ላሉብን ፖለቲካዊ ችግሮች ሊፈቱበት ስለሚገባቸው አግባብ ዙሪያ ነው:: ይህም፣ የተለያዩ ሃሳቦች መንሸራሸርንና ጠንካራ የሃሳብ ፍጭትን የሚጠይቅ ነው:: ለዚህም፣ የሌሎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው::

Wednesday, January 23, 2013

ESAT Yesamintu engeda Martin and Yohann part II Ethiopia


ESAT Yesamintu EngIda Martin and Yohann part I Ethiopia


ኢትዮጵያ ፣ የ ጋዜጠኞቹ ገጠመኝና ዓላማ


ማርቲንና ዮሃን ቃልቲ ሳሉ ሌሎች እስረኞች «የስዊድን ኤምባሲ» የሚል ስያሜ ወደተሰጠው መኝታ ስፍራቸው ይመጡ እንደ ነበር በፈገግታ ያስታውሳሉ።

ወ/ሮ አዜብ የመለስ ፋውንዴሽንን በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል


ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፓርላማ  ባለፈው ሳምንት ሐሙስ  ዕለት  ያጸደቀውና  በቢሊየን  ብር  የሚቆጠር  ዓመታዊ በጀት ይኖረዋል ተብሎየሚገመተው የመለስ ፋውንዴሽንን ወ/ሮ አዜብ  መስፍን  በፕሬዚዳትነት ይመሩታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለጉዳዩ ቅርበት  ያላቸው  ምንጮች አመለከቱ፡፡ ባለቤታቸውን  በድንገት በነሐሴ ወር 2004 አጋማሽ በሞት ካጡ በኋላ  ከአራት ወራት በላይ በተመረጡበት የፓርላማ ወንበር ላይ ተቀምጠው ያልታዩት ወ/ሮ አዜብ  መስፍን  ይኸን  ሃላፊነት   እንዲረከቡ  የተፈለገው ከአቶ መለስ ጋር  የተያያዙ ብዙ ሥራዎች  የቤተሰባቸውን  ዕውቅናና ፈቃድ  የሚፈልጉ  በመሆናቸው   ነው  ተብሎአል፡፡ በዚሁ መሰረት ወ/ሮ አዜብ  ፋውንዴሽኑን  እንዲመሩ አስቀድሞ የማግባባት ሥራ መጀመሩን  ምንጫችን አመልክቷል፡፡


በጸደቀው አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው ፋውንዴሽን ጠቅላላ ጉባዔ፣ቦርድ፣ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት
ይኖሩታል፡፡ ከ13  ተቋማት 45 ያህል የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ያሉት ሲሆን በውክልና ደረጃ ከአቶ መለስ ቤተሰብ
አራት ያህል ተወካዮች በጠቅላላ ጉባዔ ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡በተጨማሪም ከመከላከያ ሶስት፣ከገንዘብና
ኢኮኖሚ ልማት ፣ከውጪ ጉዳይ ፣ከትምህርት፣ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር መ/ቤቶች፣ከመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት፣ከቅርስ
ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ከወጣቶች እና ሴቶች ማህበራት  ከእያንዳንዳቸው አንድ ከፍተኛ አመራር አባል የጠቅላላው
ጉባዔ አባላት ሲሆኑ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አምስት፣ከእያንዳንዱ ክልል አምስት ተወካዮች ይኖሩታል፡፡
በአዋጁ መሰረት የፋውንዴሽኑን ሰባት አባላት በጠቅላላ ጉባዔ ለአራት ዓመታት  የሚመረጡ ሲሆን የአቶ መለስ ዜናዊ
አራት የቤተሰብ አባላት ግን በቀጥታ ያለምርጫ ቦርዱ ውስጥ እንዲገቡ አዋጁ ይፈቅዳል፡፡ ቦርዱ ደግሞ የፋውንዴሽኑን
ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት መርጦ ይሾማል፡፡በዚሁ መሰረት በፋውንዴሽኑ ቦርድ ውስጥ ወደ ግማሽ የሚጠጋ ድምጽ
የያዘው የአቶ መለስ ቤተሰብና ወዳጆቻቸው ወ/ሮ አዜብን በፕሬዚዳንትነት ይመርጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡

በጥምቀት በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሸጡ የነበሩ ሰዎች ታሰሩ


ኢሳት ዜና:-ብዙውን ጊዜ በጥምቀት በዓል ጊዜ የሚጠቀሰውንና ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ ያሰፈረውን ፦“አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት” የሚል  የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተፃፈበት ቆብ  የጥምቀት ዕለት ለሰንበት ት/ቤታቸው ገቢ ማስገኛነት በመሸጥ ላይ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ታፍሰው ታሰሩ።

እንደ ደጀ ሰላም ዘገባ፤ ጥር 11/2005 ዓ.ም ታቦተ ሕጉን ተከትለው በሞቀና በደመቀ ሃይማኖታዊ መንፈስ በማክበር ላይ እያሉ በፖሊስ የታሠሩት ስድስት ወጣቶች ሲሆኑ ፤ጥቅሱ የተጻፈበትን ቆብ ይሸጡ የነበሩት  ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ገቢ ለማስገኘት  እንደሆነ ተገልጿል።
 ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር  በአንድ ወቅት ወጣቶችን ሰብስበው ስለሀይማኖቶች ባደረጉት ገለፃ ፦ ተመሳሳይ ጥቅስ የተፃፈበትን ቲሸርት የለበሱ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን ፦<<አንዲት ሀይማኖት የሚሉ አክራሪዎች>>በማለት እንደዘለፏቸው ይታወሳል።

አቶ ጁነይዲን ሳዶ ሂስ በማውረድ ጥፋታቸውን አመኑ፤ ወ/ሮ አስቴር ማሞ ከፌዴራል ኃላፊነታቸው ይነሳሉ


አለም ተራ ነው ይባል የለ እንግዲህ መቻል ነው:: ዶ/ርመረራ ያኔ ፓርላማ ውስጥ “የእስረኞ አያያዝ ጥሩ አይደለም እስር ቤቱ እንደ አዲስ መገንባት አለበት ንጽህና ይጎለዋል አንድ ቀን ለናንተም ሊሆን ይችላል እና ከወዲሁ ቢታሰብ በት ጥሩ ይመስለኛል” ብለው ነበር::
ረሱት እንዴ አቶ ጁነዲን አለም ተራ ናት
አቶ ጁነይዲን ሳዶ ሂስ በማውረድ ጥፋታቸውን አመኑ፤ ወ/ሮ አስቴር ማሞ ከፌዴራል ኃላፊነታቸው ይነሳሉ
አቶ ጁነይዲን ሳዶ ሂስ በማውረድ ጥፋታቸውን አመኑ፤ ወ/ሮ አስቴር ማሞ ከፌዴራል ኃላፊነታቸው ይነሳሉ | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider
የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ሰሞኑን በአዳማ ሲያካሂደ click here to read http://www.zehabesha.com/archives/11187
source zehabesha.com

ዳዊት ከበደ እየበራ ነው እየጠፋ!?


ABE TOKCHAW

የቀድሞው አለቃዬ እና የአሁን ወዳጄ ዳዊት ከበደ ሰሞኑን አወዛጋቢ ሆኖ ሰንብቷል። ለምን አወዛገበ? ምን አወዛገበ? እንዴት አወዛገበ? ማንን አወዛገበ…? ወዘተ የሚሉትን ሁሉንም ዘርዝሬ መዝለቄን እንጃ ግን እስቲ ትንሽ ነካ ነካ ላድረግማ፤
ባለፈው ጊዜ ዳዊት ከበደ ስለ ኢትዮ ሚዲያው አበርሃ የፃፈውን ወቀሳ በአውራምባ ታይምስ ድረ ገፅ ላይ አንብቤ ነበር። በኢትዮ ሚዲያ ላይ ስለ ዳዊት ከበደ የወጣውን ፅሁፍ አላየሁትም። የዳዊትን ምላሽ ግን አልወደድኩትም። ይህንን ለዳዊትም ነግሬዋለሁ። ሳስበው ዳዊት ያንን ፅሁፍ ሲፅፍ ክፉኛ ተበሳጭቶ እንደሆነ እገምታለሁ። ምን መገመት ብቻ በደንብ አውቂያለሁ እንጂ…
በተናደድን ጊዜ የምንወስናቸው ውሳኔዎች ብዙ ግዜ መልከ መልካም አይሆኑም። ወይም ውጤታቸው አያምርም። በብስጭት ሲወሰን እንኳን ሌላው ቀርቶ ራስን ማጥፋት እንኳ አይሳካም። ለሁሉም ነገር ስክነት ያስፈልጋል። በስክነት ውስጥ ብስለት አለ። በጥድፊያ ውስጥ ግን ያለው ጥፊያ ነው መጥፋት እና ማጥፋት።

Ethiopia’s resettlement scheme leaves lives shattered and UK facing questions



MDG : Ethiopia : landgrab in Gambella : Resettling rural population
Mr O twists his beaded keyring between his long fingers as he explains why hestarted legal action against Britain’s international development department over its aid funding to Ethiopia. Three other refugees from the Gambella region listen as he speaks in a stifling room in north-eastern Kenya. All have a story to tell.

Tuesday, January 22, 2013

TPLF and the Culture of Violence


by Yilma Bekele

According to ESAT the FBI has foiled an attempt by the Ethiopian government to assassinate Ato Abebe Gelaw. GooshAccording to ESAT the FBI has foiled an attempt by the Ethiopian government to assassinate Ato Abebe Gellaw. Abera and his accomplices are under custody. Please note here I said the Ethiopian government since there seems to be no thin line between the TPLF party and the government. Why am I not surprised? I am not surprised because for the TPLF violence is sanctioned by the party leaders as a legitimate tool to achieve political, economic and military dominance.

በኤርትራ መንግሥት አልተገለበጠም

አሜሪካ ለዜጎቿ መመሪያ ሰጠች
isayas afewerqi1


“ኩዴታ ሲደረግ በቅድሚያ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚገባው የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያ ነው። በአስመራ  ይህ ስለመሆኑ የተባለ ነገር የለም። ታዲያ እንዴት ነው ኩዴታ ተከናውኗል ሊባል የሚችለው? በርግጥ ገለልተኛና ነጻ የውጪ ሚዲያዎች አለመኖራቸው የመረጃውን መጠንና ጥራት ቢገድበውም እስካሁን የሚወጡት መረጃዎች እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ እንጂ የማስገደድ አይመስልም። በዚህ መነሻ ኢሳያስ ሙሉ በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው ማለት አይቻልም። ግን የመደራደር ነገር ሊኖር ይችላል” አውሮፓ የሚኖር ኤርትራዊ ለጎልጉል የተናገው ነው።

Monday, January 21, 2013

የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሲ ትግርኛ የማይናገሩ ኢትዮጵያዉያንን የበይ ተመልካች እያደረገ መሆኑን የግንቦት 7 ጥናታዊ ሪፖረት አጋለጠ



ባለፈዉ ሳምንት ኢትዮ ተሌኮም ዉስጥ ስር እየሰደደ የመጣዉን የወያኔ ዘረኝነት በመረጃ በተደገፈ ጥናታዊ ዘገባ ለህዝብ ይፋ ያደረገዉ የግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍበዛሬዉ ዕለት ደግሞ በተመሳሳይ ደረጃ አደረጃጀቱን፤ አወቃቀሩንና የሰዉ ኃይል አመዳደቡን ለአንድ አመት ሙሉ በቅርበት የተከታተለዉን የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺንን ጥናታዊ ዘገባ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ አድርጓል። ለኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ግንባታ መሠረት ለመጣልና በአገሪቱ ኮንስትራክሺን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ታስቦ የተዋቀረዉ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን የኢትዮጵያ መሆኑ ቀርቶ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪ የህወሀት መኮንኖች እጅ መግባቱን ያጋለጠዉ የኸዉ የግንቦት 7 ጥናት ኮርፖሬሺኑ ከዋና ዳይረክተር እስከ ተራ ቴክኒሺያኖች ስረስ የህወሀት አባል በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ስር ወድቋል ብሏል። የጥናቱ ሙሉ ዘገባ እንደሚገተለው ቀርቧል።

መነቀል ያለበት ስር የሰደደ የወያኔ ዘረኝነት  (ሙሉ ጥናቱን በPDF ከዚህ ላይ ዳውሎድ ማድረግ ይቻላል)

(በግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ የተጠናና የተዘጋጀ)

“ዝም በል ዳያስፖራ” – አዋጅ፦ ከቤተ መንግሥት እስከ ቤተ እምነት


ኤፍሬም እሸቴ/Adebabay

ምን ይሆን ሚሰጥሩ ስንጥቅ የሚያረገኝ፡በዚህ ሰሞን መቼም ከእግር ኳስ ውጪ ማውራት በሕማማት ስለ ቁርጥና ጥብስ እንደማውራት ሳይቆጠር አይቀርም። እኔም ብሆን ስለ እግር ኳሱ ማውራቱን መች ጠልቼው። በርግጥ ይኼ ሁሉ ወፈ ሰማይ የስፖርት ተንታኝ በየኤፍ.ኤሙ ሲተችበት በሚውለው የተጫዋቾቻችን ብቃት፣ ጥራት፣ የኳስ ጥበብ፣ የሽልማት ዓይነት፤ የተጋጣሚዎቻችን ሁኔታ፣ የተጫዋቾቻቸው ዝና፣ ማን ከየትና ከየትኛው ክለብ እንደመጣ፣ አሰላለፋቸው እና ከኢትዮጵያ ጋር ሲገጥሙ ሊኖራቸው ስለሚችለው አያያዝ ለመተንተን ሙያውም መረጃውም የለኝም። (“ችሎታ የለኝም” አለማለቴ ይሰመርበት። ማን ይሞታል። መቸም “አልችልም” ማለት ጎጂ ባህል ሆኗል።) ቢያንስ የእንጀራ አገሮቻችን አሜሪካ እና ስዊዲን ስላፈሯቸው እና ለእናት አገራችን ኢትዮጵያ ስላበረከቷቸው ተጫዋቾቻችን መወያየት ይቻላል።

ማፈራረስ ማተራመስ ማሸበር- የወያኔ ታላቁ ራዕይ


ከይኸነው አንተሁነኝ

ጥር 19 2013

“መካብ ሲያቅት ማፍረስ ሥራ ይሆናል” ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም

ወያኔ ላለፉት 21 ዓመታት የሀገራችንን ታሪክ ለማፈራረስና ለመቀየር የቻለውን ሁሉ ሞክሯል። የሕዝባችንን የአልደፈርም ባይነት ወኔ ለመስለብና ለማኮላሸት ያልቆፈረው ጉድጋድ አልነበረም። ሃይማኖታዊ ስርአታችንንና ወጋችንን ለመናድ ብዙ መንገድ በመጓዝ ደክሟል። አብሮ በመቻቻል የመኖር ወጥ ባህላችንን ለመጨፈላለቅና ለማጥፋት ሞክሯል። በኢኮኖሚ የወያኔ ጥገኛ እንድንሆንና የመብት ጥያቄ እንዳናነሳ ፀጥ ብለን እንድንገዛ ለማድረግ ሲጥር ከርሟል። ለወገናችን ጠብ ባላለው ልማት ስም ስንቶችን ከመኖሪያ ቤታቸው ከእርሻ ማሳቸው አፈናቅሏል። አሻፈረኝ ያሉትንም አስሯል ገድሏል። ራሱ የማያከብረውን የይስሙላ ህግም አስከብራለሁ እያለ የስንቶችን መብት ረግጧል። ወያኔ ከሳምንት እስከ ሳምንት ስገቴ ናቸው የሚላቸውንና ያላማሩትን ሁሉ አቅሙ እስከ ቻለ ተጉዞ በስደት ዓለምም ቢሆን ያፈናና የግድያ ሙከራ ከማድረግ ቦዝኖ አያውቅም። በዚህ የክፋት ድርጊቱም ጥቂት የማይባሉ ወገኖቻችን ላይመለሱ ክቡር ሂዎታቸውን ገብረዋል። ወያኔ ዛሬም ቢሆን በዓለም ዙሪያ እኩይ ስራውን አላቆመም።

ከእሁድ እስከ እሁድ


ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
oil


በደቡብ ኦሞ የነዳጅ ፍለጋ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጀመረ
በደቡብ ኦሞ ጨው ባህር አካባቢ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ በማካሄድ ላይ የሚገኘው ታሎው ኦይል የተሰኘው የእንግሊዝ ኩባንያ የመጀመሪያው የሆነውን የፍለጋ ጉድጓድ ቁፋሮ ከትናንት በስቲያ ጀመረ፡፡ ቁፋሮው የተካሄደው በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ ከኦሞራቴ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው፡፡

Sunday, January 20, 2013

የበረከት-አዜብና የስብሃት ፍጥጫ (ከእየሩሳሌም አርአያ)


የበረከት-አዜብና የስብሃት ፍጥጫ (ከእየሩሳሌም አርአያ)

በሽማግሌው ስብሀት ነጋና በረከት ስምኦን መካከል ስር ሰዶ የቆየው የውስጥ ሽኩቻ እየከረረ ሔዶአል ።አዜብ መስፍን ከበረከት ጎንተሰልፈዋል። አዜብ ለፓርቲው ሊቀምንበርነት «ይመጥናሉ» ያሉዋቸውንና «መለስን ይተካሉ» ሲሉ በድፍረት የተሟገቱላቸው ሁለት አመራር አባላት ተቀባይነት አለማግኘታቸው አበስጭቶአቸዋል አዜብ የጠ/ሚ/ር እንዲሆኑ የተሟገቱላቸው  ቴዎድሮስ አድሀኖም ከእጩነት ራሳቸውን በማግለል ኩም አድርገዋቸዋል።


ሕወሀትን ከጀርባ በማሽከርከር የሚታወቁት ስብሀት ነጋ ለቀጣዩ ፍልሚያ ሀይል እያደራጁ ነው። ለበረከት ያላቸው ጥላቻ-ንቀት ጭምር የተላበሰ ነው። አዜብን ለመበቀል ግዜው አሁን እንደሆነ አረጋግጠዋል።የስብሀትና አዜብ ቁርሾ የተጠነሰሰው ከአምስት አመት በፊት ነበር። በወቅቱ የተወሰኑ የህውሀት ማ/ኮሚቴ አመራሮችን የሰበሰቡት አዜብ«ስብሀት ከኤፈርት ሃላፊነቱ መነሳት አለበት » ይላሉ። ትእዛዙንየተቀበሉት እነቴዎድሮስ ሀጎስ መልእክቱን ለሽማግሌው ያደርስሉ። 

እንደ መከላከያ ሁሉ ኢትዮ ቴሌኮምም



እንደ መከላከያ ሁሉ ኢትዮ ቴሌኮምም

ዘረኛው የወያኔ መንግስት ዘረኝነቱን በሚያጠናክርለት ና የራሱን ጀሌዎች ብቻ የስርአቱ ተጠቃሚ በማድረግ የአንድ ብሄር የበላይነቱን ይዞ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን የሚያሳይ ሌላ መረጃ ሰሙኑን የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የጥናት ክፍል ይፋ አድርጓል ። ቀደም ሲልም  በየካቲት 2002 በመከላከያ ሰራዊት በአዛዥነት ቦታዎች ያለውን የብሄር ተዋጽኦ ማጋለጣችን ይታወሳል።
ወያኔ በኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ ለረጅም ግዜ በየዘርፉ ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች አባሮና አፈናቅሎ ታማኝ ያላቸውን የህወሃት ታጋዮችን “ከሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ያስመረታቸውን ምርቶች እና ከመቀሌ ኢንስቲዩት ቴክኖሎጅ ” በአብዛኛው ከአንድ ዘር በማምጣት መድቦ ኮርፕሬሽኑ የጀሮ መጥቢያ የስላላ ተቋምና የፓርቲው መሳሪያ በማድረግ የዜጎችን ሉዓላዊነት በመዳፈር ሀገራችንን በዚህ ዘመን የመረጃ ርሃብተኛ አድርጓታል።
በዚሁ ጥናት ሌላው አሳዛኙ ጉዳይ ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 194 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያላቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም።

Saturday, January 19, 2013

አሜሪካ በአፍሪካ ወታደራዊ የበላይነቷን ልታረጋግጥ ነው!


ፕሮግራሙን ለማስፈጸም 35 አገሮች ተመርጠዋል

africom 1
አዲስ በተያዘው የአውጳውያን ዓመት አሜሪካ በአፍሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ የበላይነትን ሊያረጋግጥላት የሚችል ፕሮግራም ነድፋለች፡፡ ከሦስት ሳምንታት በፊት ይፋ የሆነውን ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ላይ የተነደፈውን ዕቅድ የሚያስፈጽሙ 35 የአፍሪካ አገሮችም ተመርጠዋል፡፡

ኢሳት እና ግንቦት 7


ኢሳት እና ግንቦት 7

እታለማሁ ማንደፍሮ
በአጭር ጊዜ ተጠንስሰው፣ በአጭር ጊዜ ተወልደው፣ በአጭር ጊዜ ያደጉ ድርጅቶች እንደ ኢሳትና እንደ ግንቦት7 አላየሁም ፣ ከቅንጅት በስተቀር። ኢሳትና ግንቦት 7 ስማቸው በፌስቡክ፣ በኢቲቪ፣ በዌብሳይትና በየሰዎች ቤት ይነሳል። የድርጅቶቹ ጠላቶችም ወዳጆችም ስሁለቱ ድርጅቶች ሳይናገሩ መሽቶ አይነጋላቸውም። እውን ድርጅቶቹ እንደስማቸው የገዘፉ ናቸው? የውስጣቸውን ጥንካሬ ራሳቸው ናቸው የሚያውቁት። እኔ ግን የታዘብኩትን ልናገር፣ ድርጅቶቹ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት ውስጥ ገብተዋል። በውጭ አይደለም ፣ በኢትዮጵያ። ይቀጥላል…