ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን በመንግስት ደህንነቶች እንደሚመረመሩና እንደሚታሰሩ ተገለጠ
ዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ጋምቤላ ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ተጉዘው የነበሩት ዶ/ር ማኝ አንግ ለኢሳት እንደገለጡት በጋምቤላ በክልሉ ፕሬዚዳንት ተጠርተው ደህንነቶች እንደሚፈልጎቸው ከተነገራቸው በሆላ ለ 2 ሰአት ያህል እንደመረመሮቸው አስታውቀዋል::
ማንኛውም የጋምቤላ ተወላጅ ወደተወለደበት ሀገር ሲሄድ ያሬድ፡ ኤፍሬምና ዳዊት በሚባሉ የመንግስት ደህንነቶች ይመረመራል፤ በጋምቤላ ከሚገኙ የተቃዋሚ መሪዎች፤ ከግምቦት ሰባትና በጋምቤላ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር ስላለው ግንኙነት ይጠየቃል ያሉት ዶ/ር ማኝ አንግ በሳቸው ላይም ተመሳሳይ ምርመራ ከተደረገ በሆላ በነጻ መለቀቃቸውን ተናግረዋል::
ይሁንና በርካታዎቹ በደንነት ከተመረመሩ በሆላ እንደሚታሰሩ የገለጡት ዶ/ር ማኝ አንግ በቅርቡ በቦሌ አየር ማረፊያ የታሰሩና በአሜሪካ ኤምባሲ ጥረት ተፈተው ከቦሌ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ስለተመለሱት ሁለት የአኝዋክ ተወላጆች ተናግረዋል:፡
በተወለዱበትና ባደጉበት ሀገር ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ የሄደ ሰው በመንግስት ደህንነቶች መታደኑ፡ መመርመሩና መታሰሩ በጋምቤላ የተለመደ ነው ያሉት ዶ/ር ማኝ አንግ 20 አመት አሜሪካ ቆይተው በሀገራቸው ስለደረሰባቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸመውን ተግባር ኮንኖል::
No comments:
Post a Comment