Translate
Monday, December 31, 2012
ከዚህም ከዚያም
ፍቅር ቁመት አይወስነውም
የዓለማችን ረጅም ወጣት የከንፈር ወዳጅ የሆነው የ22ዓመቱ ብራዚላዊ ከፍቅረኛው ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ አስደሳች እንደሆነ ገለጸ፡፡ ዕድሜዋ 17ዓመትና ቁመትዋ 6ጫማ ከ8ኢንች (2.1ሜትር) የምትረዝመው ኤሊሳኒ ሲልቫ ዕድገቷን የሚቆጣጠረው ዕጢ ላይ ባጋጠማት ችግር ምክንያት እንደዚህ ቁመቷ ሊረዝም እንደቻለና በሽታዋ ከታወቀ በኋላ ሐኪሞች ዕብጠቱን እንዳስወገዱት ተገልጾዋል፡፡
ከእሁድ እስከ እሁድ
(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
ጁነዲንና ኢህአዴግ ፊርማቸውን ቀደዱ
ከሚኒስትርነታቸውና ከኦህዴድ ስራ አስፈጻሚነታቸው በግምገማ እንዲነሱ የተደረጉት አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ሰንደቅ ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል። ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው ለማንሳት ፓርላማው በዝግጅት ላይ መሆኑን ይፋ የምክር ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ አስታውቋል።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከአገር መባረር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከአገር መባረር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው
ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከብፁዓን አበው ጋር |
- ሊቀ ካህናት ለጉባኤው መግለጫ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለሰዓታት ጫና ተደርጎባቸዋል
- ‹‹አጀንዳዬ ሃይማኖታዊ ነው፤ የሠራኹት ስሕተት ይኹን የምጠይቀው ይቅርታ የለም !!››
- የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ እንደሚያወጣ ይጠበቃል
- መንግሥት በወሰደው ርምጃ የመንበረ ፕትርክና ዓላሚዎቹ ጳጳሳት እጅ እንዳለበት ታምኖበታል
በተወሰኑ ጳጳሳት ግፊትና በመንግሥት የደኅንነት ኀይሎች ርምጃ ትላንት ምሽት ከኢትዮጵያ ተገደው እንዲወጡ የተደረጉት ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከጥቂት ሰዓታት በፊት አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ደርሰዋል፤ በሰላምና አንድነት ጉባኤው አባልም አቀባበል እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡
Sunday, December 30, 2012
ሰንበት ምሳ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው!?
ABE TOKCHAW
ዛሬም “ለአዲስ ታይምስ” (ፍትህ) አዲሳባ ተልካ የነበረችቱን ወግ ለሰንበት ምሳ እዚህ ተለጥፋለች፤ ይቋደሱልኝ እውነት ግን የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው!?
የመንገድ ቁፋሮው ነገር እንዴት አድርጎታል? በአሁኑ ሰዓት አዲሳባ ውስጥ ትራንስፖርት ከማግኘት “ፖርት” ማግኘት ይቀላል ሲሉ የሚያሽሟጥጡ ሰዎች መበራከታቸውን እየሰማን ነው።
ኧረ “ፖርት” ብል ጊዜ ምን ትዝ አለኝ፤ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ አዲስ ወደብ ግንባታ እያደረገችላት መሆኑን ሰምተን ደስታችን ጨምሯል። እሰይ እንዲህ ነው እንጂ ልግስና! በዚሁ አይነት ፤ ሌሎቹ ጎረቤቶቻችንም እንዳይቀየሙ ብንገነባላቸው ምን አለበት…? ለነ ሱዳን ፤ለነ ሱማሌ ኤርትራዬ እና ኬኒያስ ቢሆኑ ካለኛ ማን አላቸው…? እና ይታሰብበት… “ያስቀኛል ገንፎ ከራቴ ላይ ተርፎ” አሉ አበው!
“[ሻዕቢያ] በየቀኑ እየሞተ ነው”
ፕሬዚዳንቱ ግን "በልማት" ተግባራት ተጠምጃለሁ ይላሉ
ኤርትራ ከውጪና ከውስጥ ተዥጎርጉራለች። ከውጪ ደግሞ “በየቀኑ ትንሽ ትንሽ እየሞተች ነው፤ በቅርቡም የሚፈነዳ ነገር አለ” በሚል ግምት ከየአካባቢው እየተሰጠ ነው። ከውስጥ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የኢንቨስትመንት ጥያቄና ግብዣ ላይ ናቸው። የተበላሸባቸውን ዲፕሎማሲ ለማቃናት ላይ ታች እያሉ ነው።
ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው
በዮሐንስ አንበርብር
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱትን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡
የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ጁነዲን በፓርላማ የሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት ሊጠየቁበት የሚችል የሕግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል፣ በምክር ቤት አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ምክር ቤቱ እንዲያነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ በመንግሥት ቀርቧል፡፡ ጥያቄው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ወይም በፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በኩል መቅረብ ያለበት መሆኑን የምክር ቤቱ ደንብ ያዛል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች፣ ጥያቄው በየትኛው አካል መቅረቡን ለመረዳት እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡
ባለፈው ሐሙስ የዓመቱን ዘጠነኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ፕሮግራም ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በአራቱ ላይ ብቻ ተወያይቶ የቀረውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡
ባለፈው ሐሙስ የዓመቱን ዘጠነኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ፕሮግራም ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በአራቱ ላይ ብቻ ተወያይቶ የቀረውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡
የመለስ ራዕይ የሚባል ነገር የለም ሲል ስብሐት ነጋ ተናገረ፣ በአዲስ አበባ መለስን የሚያወድሱ ፖስተሮች እየተነሱ መሆናቸው ታወቀ
ስብሐት ነጋ እሱ እራሱ በፈጠረዉ ህወሀት ዉስጥ ይህ ነዉ ተብሎ የሚነገር ስልጣን ባይኖረዉም ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ግን ህወሀት ዉስት በተፈጠረዉ የመሪ እጦትና አለመተማማን የተነሳ ተደማጭነቱ እየጎላ መጥቷል። በቅርቡ በየመገናኛ አዉታሩ አንደተስተዋለዉ ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በነበሩት ሁለትና ሦስት ወራት ከፍተኛ ተሰሚነት ነበረዉ በረከት ስምኦን ድምጹ እየጠፋ ስብሐት ነጋ የኮከብ ተዋናይነቱን ቦታ እየያዘ መምጣቱ ይታወቃል።
አንጋፋዉ የህወሀት አባል ስብሐት ነጋ ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮችን መሾም ሕገ-መንግስቱን አይጥስም ወይ ተብሎ የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመለስ. . . . የሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሾም ያስፈለገው ክፍት የአመራር ቦታ ስለነበር እንደሆነ ተናግሮ ሹመቱ መደረግ የነበረበት ነገር ነዉ ካለ በኋላ መልሱን በመቀጠል እኔ የማውቀው ነገር የለም ሆኖም ሕገ-መንግስቱ ተጥሷል ከተባለ ያለው አማራጩ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ወይንም ሌላ አማራጭ መፈለግ ነዉ እንጂ አዲሱ አደረጃጀት መቀጠል አለበት የሚልና የህወሀትን ህገወጥነትና ጋጠወጥነት በግልጽ የሚያሳይ አስነዋሪ መልስ ሰጥቷል። ስብሐት ነጋም ሀነ ሦስቱን ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች የሾሙት የህወሀት አንጋፋዉ የህወሀት መስራችና መሪ ስብሐት ነጋ የመለስ ራዕይ የሚባለው ነገር ትክክል እንዳልሆነና የወያኔ ራዕይ የጋራ ራዕይ መሆኑን በያዝነዉ ሳምንት አጋማሽ አዲስ አበባ ዉስጥ ለንባብ ለበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጠዉ ቃለ ምልልስ መናገሩን የአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ። ስብሐት ነጋ ይህንን የተናገረዉ ብዙዎችን ግራ ያጋባዉንና በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔ አገዛዝ የሰጠዉን የሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት አስመልከቶ የቀረበለተን ጥያቄ ሲመልስ ነዉ።ባለስልጣኖች አሁን ተፈጠረ የተባለዉ የአመራር ክፍተት አንዴት በመለስ ዜናዊ የሃያ አንድ የልጣን ዘመን እንዳልተፈጠረ ከህዝብ የቀረበላቸዉን ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የትግል ሜዳ መሃል አገርን ጨምሮ ወያኔ ባለበት ሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች መሆኑ ተዘገበ
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል በሚል ስያሜ መመስረቱን ድርጂቱ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ያሳወቀ ሲሆን ይህን መግለጫ ተከትሎም በርካታ የዜና አውታሮች ሲዘግቡት መቆያታቸው ይታወሳል። ከዚሁ ዘገባ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት በትናንትናው እለት ስርጪቱ ከግንቦት 7 ሃይል ቃል አቀባይ ታጋይ ዜና ጉታ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ ቃል አቀባዩ እንደገለጹት የዝባዊ ሃይሉ ራእይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ጠንካራ ኢትዮጵያን እውን ሆና ማየት ነው ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት የንቅናቄው ስም ግንቦት ሰባት የተባለበት ዋነኛ ምክንያት በ1997 ምርጫ ወቅት ግንቦት ሰባት ቀን የኢትዮጵያዊያን ድምጽ ባደባባይ በጉልበት የተነጠቀበት በመሆኑ፣ ቀኑ በኢትዮጵያዊያን ልዩ ቦታ የሚሰጠውና እለቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ዘረኛውን የወያኔ አገኣዛዝ ፍጹም እንደማይፈልግ የገለጸበት እንዲሁም ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ዝግጁነቱን ያረጋገጠበት ቀን በመሆኑ ነው ብለዋል።
የግንቦት ሰባት ሃይልን አሁን መመስረት ለምን አስፈለገ በሚል የኢሳት ጋዜጠኛ ለታጋይ ዜና ጉታ ላቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል።
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ታጋይ ዜና ጉታ ወያኔን በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በምድር ላይ እየተንቀአሳቀሱ ካሉ ሃይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆኑንና፣ ከነኝሁ ሃይሎች ጋር በጋራ ለመስራት አስፈላጊዉን ቅድመ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን እንዲሁም የዚህ ሃይል የትግል ሜዳ መሃል አገርን ጨምሮ ወያኔ ባለበት ሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ነው በማለት፣ በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ አብራርተዋል።
ህወሃትን ፈጣሪም ሰውም ተፀይፎታል !
ህወሃት ጭካኔውን እንደ ጀግንነት፤ ድንቁርናውን እንደ እውቀት ቆጥሮት እኔ ብቻ ጀግና! እኔ ብቻ አዋቂ! ብሎ በትዕቢት አብጦ በማን አለበኝነት ታብዮ የኖረ ዘረኛ ቡድን ነው። የዚህ ቡድን ትዕቢት ልክና ወሰን የለውም። የትዕቢታቸው መገለጫም ብዙ ነው።”እኛ ከሌለን ኢትዮጵያን እንበትናታለን” ብለው የሚዘባትሉትን ማስታወስ ብቻ በቂ ነው። ይሄ የጨካኞች መገለጫ እንጂ የጀግና ጠባይ አይደለም። ጀግና አገር ይገነባል እንጂ አገር አይበትንም። ጀግና ለአገሩ አንድነትና ለህዝቡ ክብር ይዋደቃል እንጂ እኔ ከሌለው አገሪቷን አፈርሳታለው ብሎ አይዘባትልም። ህወሃቶች ከትእቢታቻው ላይ በወንድማማቾች መካከል ጥላቻን የመዝራት የረከሰ ስብዕናቸው ታክሎበት በሰውና በፈጣሪ ፊት የተጠሉ እንዲሆኑ ሁነዋል።መጽሃፍ ቅዱስም “እግዚአብሄር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ፤በወንድማማቾች መካከል ጥላቻ የሚዘራውንም ነፍሱ አጥብቃ ትፀየፈዋለች” ይላል። ህወሃቶች የሚገለጹት በዚህ መልኩ ነው።ከዚህ ሌላ መልክ የላቸውም።
በእነዚህ በሰውና በፈጣሪ ፊት በተናቁና በተጠሉ ቡድኖች አማካኝነት በኢትዮጵያችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም። አዎን በደል አይረሳም። በህወቶች የተፈፀመው በደል የማንረሳው የታሪካችን ህያው አካል ነው።ህወሃቶች በአገራችን ላይ የፈፀሙትን በደል ያላካተተ የኢትዮጵያ ታሪክ ጎዶሎ ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ መጥፎ ገጽታዋ መገለጫ ነው።
የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ! አገራችን እንዲህ ያለ መከራ ውስጥ የገባችው በህወሃቶች ክፋት ብቻ አይደለም፤ የእነርሱን ክፋት እያዩ ዝም በሚሉ ቅን ዜጎችም ጭምር ነው። ከሃያ ዓመት በላይ ፈረጀ ብዙ የሆኑ ግፎችን ተሸክመን ዝም በማለታችን “አህያ” ተብለን ተሰደብን እንጂ ያተርፍነው በጎ ነገር የለም።
ብሶት የወለደኝ እያለ የሚመጻደቀው ወያኔ ብሶተኞችን እየፈለፈለ ነው
በአገራችን ውስጥ የነበረው ብልሹ አስተዳደር በፈጠረው ኢፍትሃዊነት ብሶት አርግዞ ለድል ያበቃውን ጠመንጃ እንደመዘዘ በኩራት የሚደሰኩረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፡ የመንግሥት ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ሰቆቃ ተማርረው በተራቸው ብሶት አርግዘው ጠመንጃ ለማንሳት የሚገደዱ ሃይሎችን በየቀኑ እየፈለፈለ መሆኑ በተግባር እየታየ ነው።
ወያኔ የድጋፍ መሠረቴ ነው ከሚለው የትግራይ ክልል ውስጥ የወጣው “የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት” ወይምዴሚት በሚል ምህጻረ ቃል ከሚጠራውና በርካታ የትግራይ ወጣቶችን ማሰባሰብ ከቻለ ድርጅት ጀምሮ “በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የብሄር እኩልነት ካባ አከናንቤያችኃለሁ” ብሎ ወያኔ ከሚመጻደቅባቸው ህዝቦች አብራክ የወጡ የኦሮሞ፣ የኦጋዴን፣የቤነሻንጉል፣ የጋምቤላ፣ የአፋርና የደቡብ ህዝቦች የዚህን ዘረኛ ሥርዓት እብሪትና ጥጋብ አስተንፍሰው የተዋረደውን ክብራቸውን ለማስመለስ መሳሪያ አንስተው መፋለም ከጀመሩ ውለው አድረዋል።
በወያኔ የዘር ፖለቲካ ከማለዳው ጀምሮ የጥቃት ሰለባ የሆነውና እንደ ባዕድ ወራሪ በሰላም ከየሚኖርባቸው ክልሎች ታድኖ የሚባረረው አማራም “በዘር መደራጀት ከጥቃት የሚያድን” ከሆነ በሚል ቁጭት ተደራጅቶ የትጥቅ ትግሉን ጎራ መቀላቀሉን አስታዉቋል። በብሄር እኩልነት ስም በየክልሉ ለተሾሙ ምስለኔዎች በታኮነት የተመደቡ ዘረኞች በህዝባችን ስም እየማሉና እየተገዘቱ የሚያደርሱት ግፍ አስመርሯቸው ጠመንጃ ካነሱ ከነዚህ የብሄር ድርጅቶች በተጨማሪ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ላለፉት 12 አመታት ከወያኔ ጋር የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርም የተፈጠረው ወያኔ በህዝባችንና በአገራችን ላይ በሚፈጽማቸው ወንጀሎች ብሶት ባረገዙ ዜጎች መሆኑን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ የለም።
Saturday, December 29, 2012
ሰበር ዜናሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል::
ሰበር ዜናሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል::
በኢሳት እርዳታ ሳጅን ሽታየ ወርቁ ራሱን ከማጥፋት ተቆጠበ
ኢሳት ዜና:-ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ክልል በዳዉሮ ዞን በሎማ ወረዳ ገሣ ከተማ ላይ ይደረግ በነበረዉና የሎማ ዲሣ ህዝብ የአዲስ ወረዳ አግባብነት ስብሰባ ላይ የግል አስያየቱን የሰጠዉ የፖሊስ ባልደረባ ሳጅን ሽታየ ወርቁ እራሱን ከምግብ እና ከውሀ ለ24 ሰዓታት ከልክሎ በወጣበት ዛፍ ላይ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ከኢሳት ጋር ተገናኝቶ አላማውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመፈለጉ የኢሳት ባልደረቦች በስልክ አግኝተው ራሱን እንዳያጠፋ በመምከራቸው፣ ከድርጊቱ ታቅቦ በፖሊስ ታጅቦ ወደ እስር ቤት ተጉዟል።
ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ ከሁለት ቀናት በፊት “ወረዳ አያስፈልም ካላችሁ ለምን ድሮ ለሲዳማ 9 ለወላይታ 5 እያለችሁ ሸንሽናችሁ ሰጣችሁ በማለት” በስብሰባ ላይ በሰጠዉ አስተያየት ምክንያት በዕለቱ ለስብሳበ የወጡ የወረዳዉ የመንግሥት ሠራተኞች የእርሱን ሀሳብ በመደገፍ ስብሰባዉን አቋርጠዉ በመዉጣታቸዉ ምክንያት ከትላንቱ ስብሰባ የወረዳዉ ፖሊስ አባላት በሙሉ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
Friday, December 28, 2012
መንግሰት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ
ኢሳት ዜና:-አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና
ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡
ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት
አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገር
ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም
የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች
ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት
አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገር
ግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም
የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች
ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ
ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።
40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።
በኦሮሚያ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ስራቸውን እየለቀቁ ነው
ኢሳት ዜና:-
ከአንድ ወር በፊት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ታደለ ነጊሾና አቶ ሰይድ ጁንዲን ስልጣናቸውን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲለቁ ከተደረጉ በሁዋላ፣ ችግሩ መባባሱ ተገልጾአል።
ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች አሁን ባለው የፌደራል ስርአትና በክልሉ መንግስት ላይ አመኔታ ስለሌላቸው ከስልጣን እንዲለቁ መደረጋቸውን ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ዳኞች ለኢሳት ተናግረዋል።
ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች አሁን ባለው የፌደራል ስርአትና በክልሉ መንግስት ላይ አመኔታ ስለሌላቸው ከስልጣን እንዲለቁ መደረጋቸውን ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ዳኞች ለኢሳት ተናግረዋል።
በኩዌት በሳዑዲ ዓረቢያና ጅዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰው ኃይልን በርካሽ ዋጋ ሊያቀርብ እንደሚችል በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያው እያስነገረ ነው፡፡
ሰው በፈለገበት ቦታና አገር የመዘዋወር መብቱ በሕገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በኮንትራት በቤት ሠራተኝነት ወደ አረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይሰማል። ኢትዮጵያውያኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እየደረሰ ነው። ለዚህም በዋነኛነት ማሳያ የሚሆነው በተለያዩ የዓረብ አገሮች በቤት ሠራተኛነት በሚሄዱት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የመደፈርና ያለደመወዝ ማባረር ጥቂቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት እንኳን ከዓለም ደቻሳ ጀምሮ በድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የተዳረጉትን የተደፈሩትን ከፎቅ የተወረወሩትን ለአእምሮ መቃወስ የተዳረጉት የትየለሌ ናቸው ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪወቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ በዝርዝር እየዘገቡት ነው፡፡
የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው
ሰነዱን ምዕራባውያን፣ የስለላና የመብት ተቋማት ተርጉመውታል
“አዲሱ ቴሌ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ኢንሳ” በሚል ርዕስ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት የታላላቅ አገር የስለላ ተቋማት፣ ለጉዳዩ አግባብ ያላቸው መምሪያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትኩረት መሳቡ ታወቀ። ሪፖርቱን አገራቱ በራሳቸው ቋንቋ በመተርጎም የህወሃት/ኢህአዴግን የስለላ መረብ ከተለያየ አቅጣጫ እየመረመሩት ነው።
Thursday, December 27, 2012
“ይቅርታ የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም” ቴሌኮም ቀመስ ልቦለድ!
ABE TOKCHAW
ናፍቃው ናፍቃው አሁንም ናፍቃው ደወለችለት።
ነግሯታል። በእርሱ ውስጥ የተሾመች ባለስልጣን እርሷ ነች። ና ስትለው ይመጣል ሂድ ስትለው ይሄዳል። ግባ ስትለው ይገባል ውጣ ስትለው ይወጣል።
ለዚህም ነው የወደደችው ታዛዥነቱን ትህትናውን “ጠብ እርግፍ” ማለቱን አይታ ነው በፍቅሩ “ጠብ እርግፍ” ያለችው።
ናፍቃው ናፍቃው አሁንም ናፍቃው ደወለችለት።
“ይቅርታ የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይሉም!” በተስረቅራቂ ድምፅ ከወዲያኛው መስመር የሆነች ሴትዮ መለሰችላት። ቅናት አይሉት አንዳች ሰይጣናዊ ስሜት ሲሰማት ታወቃት። ሰውነቷ በበስጭት ጋለ። ከዛም ምን ነካኝ… ብላ በሀፍረት ሳቅ ብላ…
ደግማ ደወለች…
ናፍቃው ናፍቃው አሁንም ናፍቃው ደወለችለት።
ነግሯታል። በእርሱ ውስጥ የተሾመች ባለስልጣን እርሷ ነች። ና ስትለው ይመጣል ሂድ ስትለው ይሄዳል። ግባ ስትለው ይገባል ውጣ ስትለው ይወጣል።
ለዚህም ነው የወደደችው ታዛዥነቱን ትህትናውን “ጠብ እርግፍ” ማለቱን አይታ ነው በፍቅሩ “ጠብ እርግፍ” ያለችው።
ናፍቃው ናፍቃው አሁንም ናፍቃው ደወለችለት።
“ይቅርታ የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይሉም!” በተስረቅራቂ ድምፅ ከወዲያኛው መስመር የሆነች ሴትዮ መለሰችላት። ቅናት አይሉት አንዳች ሰይጣናዊ ስሜት ሲሰማት ታወቃት። ሰውነቷ በበስጭት ጋለ። ከዛም ምን ነካኝ… ብላ በሀፍረት ሳቅ ብላ…
ደግማ ደወለች…
Wednesday, December 26, 2012
የሚያስቅና የሚያሳቅቅ የፍርድ ቤት ውሎ
ዕለቱ “በእነ ኤልያስ ክፍሌ የፍርድ መዝገብ” ምስክርነት ይሰጣል የተባለበት ዕለት ነበር። በዚህ መዝገብ ውብሸት ታዬ፣ አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር፣ ሂሩት ክፍሌ እና ርዮት አለሙ ክስ ተመስርቶባቸዋል።
የደሞዝ Vs. የጠብሽ* ሰሞን
የደሞዝ Vs. የጠብሽ* ሰሞን
(ማሕሌት ፋንታሁን)
የዘወትር የድረገጻችን ተሳታፊ የሆኑ ይህንን ጽሁፍ እንድናነበውና እንድናትመው በላኩልን መሠረት እነሆ ለአንባቢዎቻችን አቅርበነዋል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ለጸሐፊዋ ማሕሌት ፋንታሁን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
የደሞዝ Vs. የጠብሽ* ሰሞን
አነጋገራችንን፣ አካሄዳችንን፣ አበላላችንን፣ አስተያየታችንን ባጠቃላይ የምናደርገውን ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ ቀጥጠኛ አስተዋፅኦ ካላቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛው በኪሳችን ያለው ገንዘብ ዋነኛው ነው፡፡ ገንዘብ ከምናገኝባቸው አንዱ መንገድ ደግሞ ተቀጥሮ መሥራትና ወር ሲያልቅ የሠራንበትን ክፍያ/ደሞዝ ማግኘት ይገኝበታል፡፡ አብዛኛው በከተማ አካባቢ የምንኖር በዚህ መስመር ውስጥ እንገኛለን፡፡
ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል
“[ሙስና] የስርዓቱ አደጋ ነው” ርምጃ ግን የለም!!
ሙስና በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ኢህአዴግ አይክድም። ኢህአዴግ ባለስልጣኖቹ በሙስና ስለመዘፈቃቸው ማመኑን የገለጸው “የመንግስት ሌቦች አስቸገሩኝ” በሚል ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ “በሙስና የተለከፉ ዋጋቸውን ያገኛሉ” ሲሉ ስልጣን በያዙ ማግስት መዛታቸውን የሚያስታውሱ በስተመጨረሻ “ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል” የሚል ድምዳሜ ላይ ነው።Monday, December 24, 2012
ከእሁድ እስከ እሁድ (የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
ከእሁድ እስከ እሁድ
(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
ኢህአዴግን በኃይል ለማስወገድ ጥሪ ቀረበ
በኢትዮጵያ ያለውን አገዛዝ ለመጣል ይቻል ዘንድ ለቀድሞው ሰራዊት፣ አሁን በስራ ላይ ላሉት የመከላከያ አባላትና በአገር ውስጥና በውጪ ስደት ላይ ላሉ ዜጎች ሁሉ የትግል ጥሪ ቀረበ። “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” በሚል ስያሜ ጥሪውን ያስተላለፈው ክፍል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሚመሩት ድርጅት ጋር ግንኙነት እንዳለው ለማጣራት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ኢሳት ዘወትር እሁድ በሚያቀርበው የሳምንቱ ዜናዎች ላይ አስታውቋል።
Sunday, December 23, 2012
የባህርዳር ሹማምንት በከፍተኛ ሙስና ተዘፍቀዋል ተባለ
ኢሳት ዜና:-ለአቶ በረከት ስምኦን የተጻፈ ሚስጢራዊ ደብዳቤ እንዳመለከተው በባህርዳር ከተማ ከንቲባ በአቶ ፋንታ ደጀን አማካኝነት በርካታ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ናቸው።
ደብዳቤው በብአዴን ውስጥ ሁለት በጥቅም የተሳሰሩ ቡድኖች መፈጠራቸውን ያመለክታል። አንደኛው ቡድን ደጀኔ ሽባባው በተባለው የብአዴን ጽሀፈት ቤት ሀላፊ የሚመራ ሲሆን በዚህ ቡድን ውስጥ የገቢዎች ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆነው ክብረት ሙሀመድ፣ የከተማ አግልገሎት የቴክኒክ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅር መኮንን፣ የቤቶች ልማት ስራአስኪያጅ አቶ ክንድይሁን እገዘው፣ የንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መንግስቴ አምሳሉ እና የጥቃቅን ምክትል ሀላፊ አቶ ሙላቱ ጸጋየ ይገኙበታል።
አቶ ስማቸው ወንድማገኘሁ በተባለው ሰው በሚመራው ቡድን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ቢያድግልኝ አድምጠው፣ የጥቃቅን ጽህፈት ቤት ሃለፊ አቶ ንበረት ታፈረ፣ የገንዘብ ጽ/ቤት ሃለፊ አቶ ፍትሀነገስት በዛብህ፣ የከተማ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሲል ሙሉ፣ የትምህርት ጽ/ቤት ሃለፊ አቶ ሙሉቀን አየሁ፣ የፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ነጋ ተመስገን፣ የከንቲባ ጽ/ቤት ሃለፊ አቶ አላዩ መኮንን፣ የጤና ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ወርቅነህ ማሞ፣ የትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ሃለፊውን አቶ ሙለጌታ ካሳ እና የከተማዋ ም/ቤት ም/ል አፈ ጉባኤዋ ወ/ሮ አበባ ካህሊው ይገኙበታል።
Saturday, December 22, 2012
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ተመሰረተ
www.ginbot7pf.org በሚል ድረ ገጽ ላይ የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የሚባል ድርጅት መመስረቱ ተገለጸ ። መግለጫውን ያወጣው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል እንዳብራራው ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓም ” የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ “የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል” የሚል ስያሜ የሰጠነውን፣ በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና ዜጎች የተሞላውን ድርጅት መመሥረታችን በዛሬው እለት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እናበስራልን” ብሎአል።
“የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የዜጎች መብቶች፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆኖ የማየትን ራዕይ የሰነቀ ድርጅት መሆኑን” የገለጸው ህዝባዊ ሀይሉ፣ መንግስትን በኃይል የማስወገድ፤ ሰላማዊና ዲሞክራሲ የሥልጣን ሽግግር በሃገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛዉም የፓለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነፃ፣ ጠንካራና ብቃት ያላቸው ህገ-መንግሥታዊ የመከላከያ፣ የፓሊስና የደህንነት ተቋማት እንዲኖሩ አስተዋጽዖ የማድረግ ተልዕኮ” ይዞ መነሳቱን ገልጿል።
መንግስት የለም ወይ? መንግስት የለም ወይ? (ህዝብ)
ዘረኛው ህወሃት የኢትዮጵያ መንግስት እኔ ነኝ ይላል።ህዝቡ ግን መንግስት የለም ወይ እያለ መጠየቁን አላቆመም። ህወሃት የመንግስት ቅርፅና መልክ የሌለው ቡድን ስለሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አለ ለማለት አይቻልም። ህወሃት መንግስት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ብርቱ የሆነ የአቅም ችግር አለበት። ይሄን ደካማነቱን የተመለከተ ህዝብ ነው ድምጹን ከፍ አድርጎ መንግስት የለም ወይ ? መንግስት የለም ወይ? ብሎ የጠየቀው።ህወሃት የመንግስትነት ባህሪይ ቢኖረው ኑሮ ይሄን ድምጽ ማድመጥ በቻለ ነበር። እንዲህ ያለውን ድምጽ አሁን በዚህ ዘመን ያለ ይቅርና በዚያ በጨለማ ዘመን እግዚአብሄር ሾመን የሚሉ ነገስታት እንኳ ቢሆኑ ያደምጡት ነበር።ህወሃት ከጨለማው ዘመን ነግስታት እንኳ የማይሻል እጅግ ኋላ ቀር መሆኑን ከሚያሳዩን ድርጊቶቹ መካከል አንዱ ይሄው የህዝቡን ድምጽ መስማት አለመቻሉ ነው።
አንዳንድ ሰዎች ህወሃት የህዝቡን ድምፅ ለመስማት ፍላጎት እንዳይኖረው ያደረገው ምንድ ነው ብለው ይጠይቃሉ። መልሱ ተፈጥሮው ነው የሚል ነው። የህወሃት ተፈጥሮው የሚገለፀው በትእቢት እና በወንጀል ነው። ትዕቢቱና ሲፈፀመው የኖረው ወንጀሉ ደግሞ ከህዝብ ጋር አብሮ እንዳይኖር አድርገውታል። ህወሃት ራሱን “እኔ አውራ ነኝ ፤እኔ ከሌለው አገሪቷ ትፈርሳለች” እያለ በአደባባይ ሲፎክር መኖሩን እናውቃለን። ”እኔ ከሌለው አገር ትፈርሳለች” የሚለው አባባል አንደኛ የትዕቢቱ ማሳያ ሁለተኛ ደግሞ ለአገሪቷም ሆነ ለህዝቧ ምንም ኃላፊነት እንደማይሰማው የሚያስረግጥ አባባል ነው። በአጠቃላይ ህወሃት ራሱን አለማወቁና ወሰን ያጣው ትዕቢቱ የህዝብን ድምፅ እንዳይሰማ አግደውታል። ከዚህ ትዕቢቱ መላቀቅ ባለመቻሉም የህዝብድ ድምጽ አድምጦ ከህዝብ ጋር የመኖርን ጥበብ ሊያገኛት አልቻለም።
ወያኔን ማስገደድ ወይም ማስወገድ የሞራልና ተፈጥሮዓዊ ግዴታ
ወያኔ/ኢህአዴግ የሰላማዊ በሮችን ሁሉ በመዝጋት በሀይል እየገፋና እየደፈጠጠ ስለ ሰላም የሚያወሩትን፣ ነጻነት የሚጠይቁትን፣ እንደወንጀለኛና ሽብርተኛ ታርጋ እየሰጠ ዴሞክራሲን ማፈኑ፣ ነጻነታችንን መግፈፉና የፖለቲካውን ምህዳር ማጥበቡ፤ የሀገራችን ህዝብ ሆ! ብሎ የተዘጋውን የሰላም በር ለማስከፈትና እንደ አረቡ አለም ጸደይ አቢዎት ተባብረን ስርአቱን የምናስወግድበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
ሰሞኑንንም በኢትዮጵያ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይኼው የሰላሙ ትግል ተዳፍኖባቸው ለቀበሌና ለወረዳ ማሟያ በሚደረገው ምርጫ አንሳተፍም ብለዋል። ወያኔ ለዚህ ሁሉ ህዝብን ወደ አላስፈላጊ አማራጭ መግፋቱ አሁንም በታሪክ ተጠያቂ ያደርገዋል። በእኛ እምነት በሰላማዊ መንገድ የሚፈታ ማናቸውንም አማራጭ ሀሳቦችን ወደ ጠረንጴዛ በማምጣት መወያየት ስልጡን የሆነ፣ ስልጣን የህዝብና በህዝብ የሚመጣ መሆኑን ማረጋገጫ ስለመሆኑ አሁንም ደግመን ደጋግመን እንናገራለን።
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኖቭል የሰላም ሽልማት ሲቀበሉ ሰላማዊ የትግል አማራጭ ከወታደራዊ መፍትሄ እጅግ የተሻለ ስለመሆኑ የማያከራክር ቢሆንም በሰላማዊ መንገድ ብቻ ተጉዞ ሰላምን ማምጣት የማይቻልበት ሁኔታ መኖሩ፤ በዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ኃይልን መጠቀም ግዴታ ብቻ ሳይሆን ከሞራል አንፃር ተገቢ ስለመሆኑ ያብራሩበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአንዳንድ የዓለም ክፍሎችና ሁኔታዎች የኃይል አማራጭ ተገቢነት እየጨመረ መምጣቱን እና ለሰላም ሲባል ደም አፍሳሽ ጦርነት ውስጥ እንኳን ሊገባ እንደሚችል ማስረጃዎችን በመጥቀስ ያስገነዘቡበት ነው:: ወያኔ/ኢህአዴግ ደግሞ ለዚህ ትልቅ ምሳሌ ነው።
ከሶማሊያውያን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን ተሰደዋል
ኦሮሞ፣ ኦጋዴን፣ አማራና ትግራይ በደረጃ ተቀምጠዋል
የአራት ዓመት ማነጻጸሪያ የቀረበበትን የሪፖርቱ አንያንዳንዱ ክፍል ያስገርማል። የማነጻጸሪያው ማሳረጊያ አስደንጋጭ ነው። መረጃው በአሃዝ፣ በኩኔታ፣ በባህሪው ስደትን ይገልጻል። ትንታኔው በካርታ፣ በስደቱ መነሻና መድረሻ መካከል፣ እንዲሁም በስደት መዳረሻ ላይ የሚያጋጥመውን አፈና፣ ቶርቸር፣ አስገድዶ መደፈር፣ ስቃይ፣ የባህር ሲሳይ የሆኑ ወገኖችን ይጠቅሳል።
Friday, December 21, 2012
ታላቅ የህወሃት የንግድ ግዛት ኤፈርት ምስጢር!!!
effort2“የሙስና መርከብ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አሉ። ከተቋቋመ ጀምሮ አንድም ቀን ስለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተገልጾ አያውቅም። ከአገሪቱ ባንኮች ትልቁ ተበዳሪ ነው።የወጋጋን ባንክ ትልቁ ባለድርሻ ነው። በአንዳንድ ከፍተኛ የንግድ ተቋማት ውስጥ የንግድ ሽርክና እንዳለው ይታማል። የወርቅ ማዕድን ፍለጋው ሰምሮለታል። የግል አስመጪዎችን በመፈታተን አነካክቶ ጥሏቸዋል። አገሪቱ ላይ የገነባው የንግድ ኢምፓየር በበርካቶች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ የተቋቋሙትን የንግድ ተቋማት በመደፍጠጥ በፖለቲካው የበላይነቱ ሳቢያ ልዩ ተጠቃሚ በመሆኑ አይወደድም። ይህ ታላቅ የህወሃት የንግድ ግዛት ኤፈርት ነው።
የትግራይ ህዝብ “ያንተ ነው” ስለሚባለው ታላቅ የንግድ ኢምፓየር የሚያውቀው ነገር እምብዛም የለም። አስራ ሶስት ሰፋፊና ስትራቴጂክ ኩባንያዎችን ያቀፈው ኤፈርት በቅርቡ የእህት ኩባንያዎቹን ቁጥር እንደሚጨምር ምልክቶች አሉ። ኤፈርት ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ በስፋት ይነገርበታል። ከዚሁ ከሚታማበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ ወ/ሮ አዜብ በድንገት ይፋ ያደረጉት ምስጢር አነጋጋሪ ሆኗል።
Thursday, December 20, 2012
በ 21.12.12 ዓለም የምትጠፋበትን ቀን እና ጥፋት ተንባዮችዋ
ስለ ዓለም ኅልፈት የተነገረዉን ትንቢት ይዘን በፊስ ቡክ አስተያየታቸዉን እንዲያካፍሉን የጠየቅናቸዉ ታዳሚዎች አብዛኞቹ ከፈጣሪ በቀር ይህን የሚያዉቅ የለም ወግዱ በሏቸዉ ሲሉ ሃሳባቸዉን ፅፈዋል። አንዳዶች ደግሞ ብቻችንን መቅረታችን ነዉ ያሉንም አሉ።
የጎርጎረሳዉያኑን ቀመር የሚከተሉ በሂሳብም ሆነ በስነ-ፈለግ እንዲሁም በፒራሚድ ሥራዎቻቸዉ የሚደነቁትና ሥልጣኔን ለዓለም አበርክተዉ ያለፉት ማዕከላዊ አሜሪካ ይኖሩ የነበሩት ጥንታዊያኑ፤ የማያ ጎሳዎች የዘመን ቀመር በመጠናቀቁ ዓለም የምትጠፋበትን ቀን ተንብየዋል።
የጎርጎረሳዉያኑን ቀመር የሚከተሉ በሂሳብም ሆነ በስነ-ፈለግ እንዲሁም በፒራሚድ ሥራዎቻቸዉ የሚደነቁትና ሥልጣኔን ለዓለም አበርክተዉ ያለፉት ማዕከላዊ አሜሪካ ይኖሩ የነበሩት ጥንታዊያኑ፤ የማያ ጎሳዎች የዘመን ቀመር በመጠናቀቁ ዓለም የምትጠፋበትን ቀን ተንብየዋል።
በትንበያቸዉ መሰረት ይህ ቀን አርብ በ 21.12.12 ይዉላል ነዉ የተባለዉ። በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ የተለያዩ የብዙሃን መገናኛዎች በጉዳዩ ሰምዎኑን የመዝናኛ ርዕሳቸዉ አድርገዉት ሰንብተዋል። እኛም ይህን ሃሳብ ይዘን በፊስ ቡክ ገፃችን አስተያየታቸዉን እንዲያካፍሉን የጠየቅናቸዉ የዶቸ ቬለ ታዳሚዎች አብዛኞቹ ከፈጣሪ በቀር ይህን የሚያዉቅ የለም ወግዱ በሏቸዉ ሲሉ፤ ሌሎች ተገላገልን ነበር ከማይረባዉ ዓለም ሲሉ የተለያየ ሃሳባቸዉን አካፍለዉናል።
ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ በላይ ኢህአዴግ ሆኖብናል ሲሉ ተቃዋሚዎች ገለጹ
ታህሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-መጪው የአካባቢና የአዲስ አበባ ምርጫ ፍትሀዊ መሆን አለበት በማለት ፔትሺን ተፈራርመው ያስገቡት 33 የፖለቲካ ድርጅቶች ዛሬ በመኢአድ ጽህፈት ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ ምርጫ ቦርድ ለጥያቄያቸው መልስ አለመስጠቱን ገልጸው፣ በንባብ የሰጡዋቸውን ምላሽ እንደ አንድ ትልቅ መንግስታዊ ተቋም በደብዳቤ ለመግለጽ እንኳን ፈቃደኛ አልሆኑም ፣ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ በላይ ኢህአዴግ ሆኖብናል ብለዋል።
የፓርቲዎች ጥምረት ኮሚቴ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳስታወቀው ምርጫ ቦርድ ለገዢው ፓርቲ በግልጽ ወገናዊነቱን አሳይቷል ብሎአል። ያቀረቡትን የውይይት ሀሳቦች ቦርዱ አለመቀበሉን ያሳወቁት ፓርቲዎች ፣ ምርጫው ላይ ለመሳተፍ እና ላለመሳተፍ ገና አለመወሰናቸውን ገልጸዋል።
የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወ/ሮ የሺ ፈቃደ በምርጫ 1997 ዓም ኢህአዴግን ወክለው ለምርጫ የተወዳደሩ ሲሆን ፣ በ80 ድምጽ ብቻ በማግኘት ተሸንፈው ሲወድቁ የምርጫ ቦርድ ኤክስፐርት ተብለው በህዝብ ግንኙነት ባለሙያነት ተሹመው የፓርቲውን ስራ ያስፈጽማሉ ብለዋል።
የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወ/ሮ የሺ ፈቃደ በምርጫ 1997 ዓም ኢህአዴግን ወክለው ለምርጫ የተወዳደሩ ሲሆን ፣ በ80 ድምጽ ብቻ በማግኘት ተሸንፈው ሲወድቁ የምርጫ ቦርድ ኤክስፐርት ተብለው በህዝብ ግንኙነት ባለሙያነት ተሹመው የፓርቲውን ስራ ያስፈጽማሉ ብለዋል።
ስዊስ ባንክ በታምራት ላይኔ ስም የተቀመጠ ስምንት ሚሊዮን ዶላር መለሰ
አቶ ታምራት ላይኔ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከመቋቋሙ በፊት ሥልጣንን አለአግባብ በመጠቀም ሦስት ክሶች ተመሥርቶባቸው ነበር፡፡ ከእነዚህ ክሶች በተጨማሪም መንግሥትን ወክለው ከሼክ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ 16 ሚሊዮን ዶላር ለቡና ግዥ ተበድረዋል መባሉ ይታወሳል፡፡ ይህ ገንዘብ ስዊስ ባንክ ውስጥ ይገኛል የሚል መረጃ የደረሰው መንግሥት በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል ገንዘቡን ለማስመለስ ጥረት አድርጓል፡፡
ከ16 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ስምንት ሚሊዮን ዶላር በስዊስ ባንክ እንደሚገኝ በመረጋገጡ፣ መንግሥት ገንዘቡ እንዲመለስለት ለስዊስ ፍርድ ቤት ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የስዊስ ፍርድ ቤት ገንዘቡ የኢትዮጵያ መንግሥት አይደለም በሚል ለሌላ ግለሰብ እንዲመለስ ወስኗል፡፡
አቶ ዓሊ የተጠቀሰው ገንዘብ ለኢትዮጵያ እንዳልተመለሰ ገልጸው፣ ገንዘቡ የተመለሰለትን ግለሰብ ስም ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደሚገልጹት ከሆነ ግን ገንዘቡ የተመለሰው ለሼክ አል አሙዲ ነው፡፡
ጠቅላይ ፍርድቤት የእነ አቶ አንዱዓለምን ይግባኝ አዳመጠ
ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ጠቅላይ ፍርደ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝግብ በሥር ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ጥፋተኝነት የተፈረደባቸውን የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ክርክር አድምጧል፡፡
ከቃሊቲ እና ቂሊንጦ እስር ቤቶች የቀረቡት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አንዷለም አራጌ፣ የፓርቲው አመራር አባልና የወጣቶች አደራጅ ኃላፊ ናትናኤል መኮንን፣ የመኢዴፓ ፓርቲ ኃላፊ ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)፣ የቀድሞው የፓርላማ አባል አቶ አንዷለም አያሌው ናቸው፡፡
የአንዷለም አራጌ፣ የናትናኤል መኮንን እና የክንፈሚካኤል ደበበ ተከላካይ ጠበቃ አቶ ደርበው ተመስገን መከራከሪያቸውን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ “የሥር ፍርድ ቤት (ከፍተኛው ፍርድ ቤት) በደበኞቻቸው ላይ ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት ሳይኖር በሕጋዊ መንገድ በሚንቀሳቀሱበት ፓርቲዎችና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው ብቻ ጨካኝ እና ከባድ ፍርድ ሳያገናዝብ እንደፈረደባቸው 5 ዋና ዋና ነጥቦችን አቅርበው አስረድተዋል፡፡ አንድ ነገር ወንጀል የሚባለው ህጋዊ ግዙፋዊ እና ሞራላዊ ሁኔታዎች በአንድ ላይ ሲኖሩ ነው፤ ይህ ባሌለበት ነው ፍርድ የተሰጠው” በማለት ጠበቃው ተከራክረዋል።
መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ የ2.6 ቢሊዮን ብር ኮንትራት ተሰጠው
ኢሳት ዜና:-ባለቤትነቱ የሕወሀት የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ከሶስት የስኳር ፋብሪካዎች የ2.6 ቢሊዮን ብር ኮንትራት እንደወሰደ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘገበ።
ከተቋቋመ 19 አመት የሞላውና የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዳውመንት ፈንድ የተሰኘው ግዙፍ ድርጅት አካል የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገነቡ 3 ስኳር ፋብሪካዎች የሚሆኑ የማፍሊያ ቤቶችን (ቦይሊንግ ሀውሶች) ለመገንባት ነው የ2.6 ቢሊዮን ብሩን ኮንትራት የወሰደው።
የመስፍን ኢንጂነሪንግ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ገብረኪዳን ለኢቲቪ እንደገለጹት፤ ፋብሪካው ከ2 ዓመት በሁዋላ አመታዊ ትርፉን ወደ 600 ሚሊዮን ብር ለማሳደግ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ መስፍን ኢንጂነሪንግ በቦሌ ዞን በ35 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ይገነባል የተባለውን የኢንዱስትሪ ዞን ኮንትራት ወስዶ እየገነባ እንደሆነ ዜናው ጠቁሟል።
Wednesday, December 19, 2012
ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ መገንባት ጀመረች
"... ህወሓት በሽርክና የሚያስገነባው ቢሆንስ?"
በጅቡቲ አዲስ የሚገነባው ወደብ ወጪ በኢትዮጵያ እንደሚሸፈን ተገለጸ። ወደቡ በቀጥታ ከትግራይ ከሚነሳው አዲሱ የባቡር መስመር ጋር እንደሚገናኝም ታውቋል። እያደር ይፋ በመሆን ላይ ያሉት ፕሮጀክቶች አቶ ሃይለማርያም አስመራ ድረስ ለመሄድያሳዩትን ፈቃደኛነት “ለኢሳያስ የቀረበ የፖለቲካ አይስክሬም” በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ፡፡
Tuesday, December 18, 2012
ህወሓት የብረት መዳፍ
(ተመስገን ደሳለኝ)
የድህረ-መለስ ዝግመተኛውና መቋጫ ያጣው የፖለቲካ ማዕበል፣ አሁንም አዳዲስ ክስተቶችን ማሳየቱን አላቋረጠም፡፡ ዝነኛው ‹‹የመለራዕይ›› መፈክርም ግንባሩን የታሰበውን ያህል ወደ አንድ ለማሰባሰብ አቅም ያጠረው ይመስላል፡፡ ጥገናዊ ለውጦቹም እንዲሁ አትራፊመሆን አልቻሉም፡፡ መሀል አራት ኪሎ በሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ግድግዳ ላይ የተሰቀለው የመለስ ፎቶም ‹‹ሸምጋይ››አልሆናቸውም፡፡ በብሄር ተኮር ፍላጎት የሚወዛወዘው የኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስትም ለሁለት ወር ከአስር ቀን ያህል ያለ ሚንስትሮችምክር ቤት (ካቢኒ) ስልጣን ላይ የቆየ ቢሆንም፣ ህዳር 20/2005 ዓ.ም. ካቢኔውን ሲያቋቁም ሁለት ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይሚኒስትሮች እና ሶስት ሚኒስትሮችን ለፓርላማው በማቅረብ እንዲሾሙ አድርጓል፡፡ በዚህ ፅሁፍም የሁለቱን ምክትል ጠቅላይሚንስትሮች ሹመት ከህገ-መንግስቱ አኳያ ያለውን ህጋዊነት እና ከሹመቱ ጀርባ ያሉ ፖለቲካዊ መግፍኤዎችን እንዳስሳለን፡፡ስንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች?
ምንም የሚያስፈራን ነገር የለም፤ ሞትም ቢሆን! የተበዳይ ኮሙዩኒኬተሮች ሕብረት አንድነት ጉባኤ
ይድረስ ለክቡር አቶ በረከት ስምዖን
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ (ሚኒስትር)
ከእንጀራ ልጆችዎ
ክቡር ሚኒስትር አቶ በረከት ሆይ!እባክዎትን ልብ ብለው ይስሙን፡፡ እባክዎትን አንድ ጊዜ ጆሮዎትን ያውሱን፡፡ ምነው ልብዎት በእኛ ጨከነሳ? ይህ የእንጀራ ልጅን የማግለል ሥራ ውጤቱ ጥሩ የሚሆን ይመስልዎታልን? እንዴት ነው ነገሩ?
ክቡር አቶ በረከት፡- እኛ ለእርስዎ ልዩ ክብርና አድናቆት አለን፡፡ የኮሙዩኒኬሽን ድ/ቤትን መምራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በዋናነት በእርስዎ አመንጭነትና አስፈፃሚነት የተወሰዱ የተለያዩ እርምጃዎች በአገራችን ለዘመናት የነበረውን የኮሙዩኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ሥራ ለማሻሻል ጥሩና አበረታች ጅምር ያሳዩ ናቸው፡፡ ይህን እናምናለን፡፡
ጂጂና ቴዲ፣ እንደ ቦብ ማርሊ እንደ ፌላ ኩቲ
ጃማይካዊውን የጥበብ ሰው ጋሪሰን ሃውክን በመንተራስ አርቲስት ጂጂ እና ቴዲ አፍሮ ሰሞኑን የለቀቁት 'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'´ ነጠላ ዜማ በብዙዎች አድናቆትን እየተቻረ ይገኛል። ብዙዎችንም አነቀቅቷል። ሙዚቃው የተለየ ነው፣ የሚያበረታታ እና የሚያነቃቃም ነው።
"ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!"
ብዙውን ግዜ በጦር ጀብዱ የፈጸመን ወይንም ድል ያደረገን ሰው ጅግና ብለን እንጠራዋለን።
ጀግንነትን በዚህ መስፈርት ብቻ ከለካነው - ይህ ቀላሉ ጀግንነት ሊሆን ይችላል። ከባዱ እና እውነተኛው ጀግንነት ግን ጦርነትን ሳይሆን ሰላምን ማሸነፍ መቻል ነው።
ምንም አይነት ጅብዱ ቢፈጽም ራእይ ግን የሌለው ሰው ጀግና ሊሆን አይችልም። ህይወት ካለ ተስፋ አለ። ተስፋ ካለ ህልም አለ። ህልም ካለ ራዕይ አለ። ራእይ ያለው ሰው ነው ጀግና። 'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!
ብዙውን ግዜ በጦር ጀብዱ የፈጸመን ወይንም ድል ያደረገን ሰው ጅግና ብለን እንጠራዋለን።
ጀግንነትን በዚህ መስፈርት ብቻ ከለካነው - ይህ ቀላሉ ጀግንነት ሊሆን ይችላል። ከባዱ እና እውነተኛው ጀግንነት ግን ጦርነትን ሳይሆን ሰላምን ማሸነፍ መቻል ነው።
ምንም አይነት ጅብዱ ቢፈጽም ራእይ ግን የሌለው ሰው ጀግና ሊሆን አይችልም። ህይወት ካለ ተስፋ አለ። ተስፋ ካለ ህልም አለ። ህልም ካለ ራዕይ አለ። ራእይ ያለው ሰው ነው ጀግና። 'ጀግና አይፈራም … ተስፋ አይቆርጥም'!
“በኢትዮጵያ አስደንጋጩ የግብረሰዶማዊያን መደራጀት ና መስፋፋት!
ታዋቂው ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አርአያ በኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ ድረገጽ ላይ “በኢትዮጵያ አስደንጋጩ የባሕል ወረርሽኝ” በሚል ርዕስ ለሕዝብ ያስነበበውን የግብረ ሰዶም መከሰት በኢትዮጵያ መለስ ዜናዊ እና ስርዓቱ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንዳደረገ በሰፊው እንዳስነበበን ታስታውሳላችሁ። ከ10 እና 12 ዕደሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሃያ (20) ታዳጊ ሕፃናት በውጭ አገር ሰዎች እንደተደፈሩና ደፋሪውም ወደ አገሩ እስኪመለስ ደረስ ሆን ተብሎ መንግስት ቸል እንዳለው ዘገባዎች አመልክተዋል። ችግሩ ጠለቅ ብልን እንድንረዳው ጋዜጠኛ እየሩሳሌም ግበረሰዶማዉያን በደብቅ ሳይሆን በቡድን ወደ መደራጀት ደረጃ እንደደረሱ ሁኔታውን እንዲህ ይገልጸዋል፤-
“ግብረሰዶማዊያን ማሕበር (ቡድን) እስከ መደራጀት ደርሰዋል።ከላይ እንደጠቀስኩት የመለስ አስተዳደር ምን አቋም እንዳለዉናእንደሚከተል ጠንቅቀዉ የተረዱ ግብረሰዶማዊያን የ2000ዓ.ም.ሚሊኒየም በማስታከክ “ሕጋዊ ዕውቅና ይሰጠን” እስከማለትናየመለስ ዜናዊን በቀጥታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል።ስለዚሁ ጉዳይ ወይም ጥያቄ “ሪፖርተር” ጋዜጣ የዜና ሽፋን በወቅቱ ሰጥቶታል።” ይላል ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋማርያም (እየሩሳሌም አርአያ)።
ዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ስርአት መለወጥ አለበት አለ
ኢሳት ዜና:-የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ስርአት ካልተለወጠ፤ የኢትዮጵያ እድገት ግቡን መምታቱ አጠራጣሪ ነው ሲል የዓለም ባንክ አስጠነቀቀ።የዓለም ባንክ ባለፈው ሳምንት በሂልተን ሆቴል በለቀቀው፤ “ሁለተኛ ደረጃ ት/ት በኢትዮጵያ፤ እድገትና ለውትን ለማገዝ” (Secondary Education in Ethiopia: Supporting Growth and Transformation ) የተሰኘ ጥናት እንደገለጸው፤ ኢትዮጵያ የጠቅላላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ስርአቷና ካላሻሻለች፤ በ2025 መካከለኛ የምጣኔ ሀብት (ወይም ኢኮኖሚ) ወዳላቸው አገሮች ደረጃ ማደግ መቻሏ የማይታሰብ ነው ነው ሲል አስጠንቅቋል።
ኢትዮጵያ መካከለኛ የኢኮኖሚ እድግት ደረጃ ላይ ለመድረስ የምታደርገው ጥረት አበረታች መሆኑን የጠቀሰው ጥናት፤ ኢትዮጵያ በ2025 ሁለተኛ ደረጃ ት/ትን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ለማድረስ የምታደርገው ጥረት ቢሳካም፤ የትምህርት ስርአቱ ካልተለወጠ በስተቀር፤ አሁን ባለው የትምህርተ ስርአት ወደሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገቡት ተማሪዎች፤ ወደከፍተኛ ት/ት ለመግባት የሚያስችላቸውን የቅድመ ት/ት ዝግጅት ለመወጣት የሚያስችል ብቃት ይዘው አይወጡም ሲል ጥናቱ ስጋቱን ይገልጻል።
ሰበር ዜና....16 የኣውሮፓ ፓርላማ ኣባላት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአፋጣኝ እንዲፈታ የሚል ደብዳቤ ፃፉ!!!
16 Members of the European Parliament Call for the Release of Imprisoned Ethiopian Journalist Eskinder Nega
Washington, D.C.: Today, 16 members of the European Parliament issued a public letter to Ethiopian Prime Minster Hailemariam Desalegn expressing their grave concern regarding the continued detention of imprisoned journalist and blogger Eskinder Nega.
Arrested in 2011 and detained without access to an attorney for nearly two months, Mr. Nega was sentenced to 18 years in prison under the country’s broad 2009 Anti-Terrorism Proclamation on July 13, 2012. Mr. Nega’s arrest and prosecution came after he wrote online articles and spoke publicly about the possibility of an Arab Spring-like movement taking place in Ethiopia. After his sentencing, the government initiated proceedings to seize his assets, including the home still used by his wife and young son. An appeal hearing in the case is scheduled for Wednesday, December 19th.
Washington, D.C.: Today, 16 members of the European Parliament issued a public letter to Ethiopian Prime Minster Hailemariam Desalegn expressing their grave concern regarding the continued detention of imprisoned journalist and blogger Eskinder Nega.
Arrested in 2011 and detained without access to an attorney for nearly two months, Mr. Nega was sentenced to 18 years in prison under the country’s broad 2009 Anti-Terrorism Proclamation on July 13, 2012. Mr. Nega’s arrest and prosecution came after he wrote online articles and spoke publicly about the possibility of an Arab Spring-like movement taking place in Ethiopia. After his sentencing, the government initiated proceedings to seize his assets, including the home still used by his wife and young son. An appeal hearing in the case is scheduled for Wednesday, December 19th.
መስፍን ኢንጂነሪንግ 30ሚሊዮን ዶላር አተርፋለሁ አለ
በአማራ አረም ለማስወገድ የአንድ ለአምስት ጥርነፋ ተደረገ
በኤፈርት ስር ከታቀፉት የህወሃት የንግድ ተቋሞች መካከል አንዱ የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪያል በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ሰላሳ ሚሊዮን ዶላር ለማትረፍ እንደሚሰራ አስታወቀ። ለሶስት ስኳር ፋብሪካዎች የአገዳ መቀቀያ ገንዳ (ቦይሊንግ ሃውስ) ለመስራት የሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ስምምነት አደረገ።
Monday, December 17, 2012
ከፍተኛው ፍርድቤት በሙስሊም መሪዎች ላይ ብይን ሰጠ
ከፍተኛው ፍርድቤት በሙስሊም መሪዎች ላይ ብይን ሰጠ
ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ አቶ አቡበክር የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል በተከሰሱት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ብይን ሰጥተዋል።
ችሎቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ እና ታሳሪዎች ወደ ማረሚያ ቤት እስኪመለሱ ድረስ ከልደታ እሰከ ኮካ ኮላ ድረስ ያለው አካባቢ በመላ በፌደራል ፖሊስ ተወጥሮ ነበር።
ፍርድ ቤቱ ከቀረቡት ክሶች ውስጥ መንግስትን የመገልበጥ ሙከራ የሚለውን ሁለተኛውን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ከአንደኛው ክስ ላይ ደግሞ የሽብር ፈጠራ ከሚለው ላይ ሙከራ ፣ ማነሳሳት የሚለውን አንቀጽ 4 ወጥቶ በአንቀጽ 3 ድርጅቱን በራስ ማድረግ የሚለው ላይ እንዲጠቃለል ወስኗል።
23ኛን ተከሳሽ በሚመለከት የአእምሮ ህመምተኛ በመሆኑ ተነጥሎ እንዲታይ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ አስተላልፎ፣ ከአማኑኤል ሆስፒታል የምርመራ ውጤት እንዲመጣለት አዟል። ነገር ግን ተከሳሹ በዋስትና ወጥቶ እንዲከራከር ጠበቆች ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል።
ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም በቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ኦርቶዶክስ ትክክል ነው የሚል የለም፤›› በማለት ምልአተ ጉባኤውን ተዳፍረዋል .ሚኒስትሩ የቅ/ሲኖዶሱን ትዕግሥት እየተፈታተኑ ነው.
ሚኒስትሩ በቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ኦርቶዶክስ ትክክል ነው የሚል የለም፤›› በማለት ምልአተ ጉባኤውን ተዳፍረዋል
መንግሥት በአክራሪነት ምንነት ላይ ሁሉን የሚያግባባ፣ በጥናት የተደገፈ ትርጓሜ እንዲያስቀምጥ ተጠይቋል
‹‹ሁሉም ሃይማኖቶች እኵል ናቸው ተብሎ ለእኛ [ለቅ/ሲኖዱሱ አባላት] አይነገርም!!›› /ብፁዕ አቡነ አብርሃም/
‹‹መቻቻል እየተበደሉ ነው ወይ? የራስን ሃይማኖት ከጥቃት መከላከልስ አክራሪነት ነው ወይ?›› /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ/
‹‹ወላይታ፣ ጂንካ ስትሄዱ ባለሥልጣኖቻችኹ የፖሊቲካ ሥራ ብቻ አይደለም የሚሠሩት፤ የእምነታቸውንም ሥራ ነው የሚሠሩት›› /ብፁዕ አቡነ ኤልያስ/
‹‹የኦርቶዶክሱና የሙስሊሙ እንጂ የፕሮቴስታንቲዝሙ አክራሪነት እየተሸፋፈነ ነው፡፡ /ታዛቢዎች/
ከወቅቱ ብሔራዊ አደጋዎች (በመንግሥት አነጋገር የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ መሰናክሎች) አንዱ÷ ‹‹የኪራይ ሰብሳቢዎችና የከሰሩ ፖሊቲከኞች መጠጊያና ምሽግ ነው›› የሚባለው ‹‹የሃይማኖት አክራሪነትና ጽንፈኝነት›› እንደኾነ መንግሥት በተለያዩ መድረኰች ይናገራል፡፡
መንግሥት በአክራሪነት ምንነት ላይ ሁሉን የሚያግባባ፣ በጥናት የተደገፈ ትርጓሜ እንዲያስቀምጥ ተጠይቋል
‹‹ሁሉም ሃይማኖቶች እኵል ናቸው ተብሎ ለእኛ [ለቅ/ሲኖዱሱ አባላት] አይነገርም!!›› /ብፁዕ አቡነ አብርሃም/
‹‹መቻቻል እየተበደሉ ነው ወይ? የራስን ሃይማኖት ከጥቃት መከላከልስ አክራሪነት ነው ወይ?›› /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ/
‹‹ወላይታ፣ ጂንካ ስትሄዱ ባለሥልጣኖቻችኹ የፖሊቲካ ሥራ ብቻ አይደለም የሚሠሩት፤ የእምነታቸውንም ሥራ ነው የሚሠሩት›› /ብፁዕ አቡነ ኤልያስ/
‹‹የኦርቶዶክሱና የሙስሊሙ እንጂ የፕሮቴስታንቲዝሙ አክራሪነት እየተሸፋፈነ ነው፡፡ /ታዛቢዎች/
ከወቅቱ ብሔራዊ አደጋዎች (በመንግሥት አነጋገር የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ግንባታ መሰናክሎች) አንዱ÷ ‹‹የኪራይ ሰብሳቢዎችና የከሰሩ ፖሊቲከኞች መጠጊያና ምሽግ ነው›› የሚባለው ‹‹የሃይማኖት አክራሪነትና ጽንፈኝነት›› እንደኾነ መንግሥት በተለያዩ መድረኰች ይናገራል፡፡
በቴዲ አፍሮ ስም የተለቀቀው መዝሙር የዘማሪ ጥላሁን ጎአ መሆኑ ተረጋገጠ
በቴዲ አፍሮ ስም የተለቀቀው መዝሙር የዘማሪ ጥላሁን ጎአ መሆኑ ተረጋገጠ
”ዘ-ሐበሻ) በቴዲ አፍሮ
ስም ተለቆ የነበረውና
ስም ተለቆ የነበረውና
ብዙዎችን ሲያነጋገር
የሰነበተው “በይቅርታ
ተቀበለኝ መዝሙር”
የዘማሪ ጥላሁን ጎአ እንደሆነ ታወቀ።
የሙዚቃው አቀናባሪ ዝናው ሃሳም ይህን አረጋግጧል። በቴዲ አፍሮ ስም ማን እንደለቀቀው ባይታወቅም ብዙዎች ግን
ለዝና ማግኛ ነው ሲሉ አስተያየት ይሰጣሉ።
ዘማሪው ነዋሪነቱ በወላይታ መሆኑም ታውቋል። የበለጠ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።
ለጊዜው በዩቲዩብ የተለቀቀው የዘማሪ ጥላሁን ጎአ መዝሙርን ይመልከቲ።
የሰነበተው “በይቅርታ
ተቀበለኝ መዝሙር”
የዘማሪ ጥላሁን ጎአ እንደሆነ ታወቀ።
የሙዚቃው አቀናባሪ ዝናው ሃሳም ይህን አረጋግጧል። በቴዲ አፍሮ ስም ማን እንደለቀቀው ባይታወቅም ብዙዎች ግን
ለዝና ማግኛ ነው ሲሉ አስተያየት ይሰጣሉ።
ዘማሪው ነዋሪነቱ በወላይታ መሆኑም ታውቋል። የበለጠ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።
ለጊዜው በዩቲዩብ የተለቀቀው የዘማሪ ጥላሁን ጎአ መዝሙርን ይመልከቲ።
“ከኢትዮጵያ ስለመጣችሁ ታሰራችሁ”
የእስራኤል ወገኖች ኦባንግን “ድረሱልን” እያሉ ነው
አገር ቤት ያሉትን ወገኖች ለጊዜው መታደግ ካልተቻለ ቢያንስ ከማንም ተጽዕኖ ወጪ በስደት የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊያኖች ለመርዳት ለሚቀርብ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ የሚያሳዝን እንደሆነ አቶ ሳሙኤል አለባቸው በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር ሊቀመንበር ገለጹ። አቶ ኦባንግ ሜቶን ማህበሩ በተለይ መጋበዙን አስታወቁ።
Friday, December 14, 2012
ሜጀር ጄነራል አብርሀ በኦጋዴን ጦርነት አትራፊ ናቸው ተባለ
በጅጅጋ የሚገኙ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ኦጋዴን ቱዴይ ፕሬስ እንደዘገበው የኦብነግ ተዋጊዎች በደገሀቡር ውስጥ ለቢጋ በተባለ መንደር ባለ የመንግስት የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት ሰንዝረው 30 የሚሆኑ የመንግስት ወታደሮች መግደላቸውን ገልጸዋል።
17 ቆስለው በደገሀቡር ሆስፒታል እንደሚገኙና ከኦብነግ በኩልም 2 ሰዎች መሞታቸውን የኦብነግ አመራር አባል አቶ ሀሰን አብዱላሂ ከአውሮፓ ገልጸዋል።
ከጥቃቱ በሁዋላ የመንግስት ወታደሮች በመንደሩ ላይ ጥቃት ከፍተው የአካባቢውን ሽማግሌዎችና ሴቶች ታጣቂዎቹን ትደብቃላችሁ በሚል ሰበብ አፍነው እንደወሰዷቸውና የደረሱበት እንደማይታወቅ ኦጋዴን ቱዴይ የዘገበ ሲሆን፤ አቶ ሀሰን አብዱላሂም ይሄንኑ አረጋግጠዋል።
ስለውጊያውና በኬንያ ተጀምሮ ስለነበረው የእርቅ ድርድርና ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ሕገመንግስቱን ተቀበሉ ብለው ስላስቀመጡት ቅድመ ሁኔታ የጠየቅናቸው አቶ ሀሰን አብዱላሂ፤ ሕገመንግስቱ ችግራቸው እንዳልሆነ፤ ነገር ግን ጦርነቱ እንዳይቆም የሚፈልጉ የመንግስት የጦር መኮንኖችና የክልሉ ፕሬዚዳንት ለሰላሙ መምጣት እንቅፋት እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
በተለይም የምስራቅ ጦር ዋና አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄኔራል አብርሀ ወልደማሪያም በቅጽል ስማቸው ኳርተር፤ ከነቤተሰቦቻቸው በአካባቢው ላይ ከፍተኛ የንግድና ኮንትሮባንድ ቢዝነስ ስላላቸው፤ እንዲሁም የክልሉ የመንገድ፤ የትምህርት ቤቶች፤ የመንግስት ህንጻዎች ግንባታዎች ኮንትራቶች ለጄኔራል አብርሀ ሚስትና ዘመዶች ስለተሰጡ፤ የጦርነቱን መቀጠል ይፈልጉታል ሲሉ ተናግረዋል።
ከአቶ ሀሰን አብዱላሂ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በኢሳት ሬድዮ ይከታተሉት።
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሳካ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ አካሄደ፣ “አለም አቀፍ ኮሚቴ” የሚባል እንቅሰቃሴ አለመኖሩን ገለጸ
ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጎጠኛው የወያኔው ስርዓት በአገራችንና በህዝባችን ላይ ሲያደርስ የነበረውና እያደረሰ ያለው ግፍ ለስልጣን በበቃበት መንገድ መውረድ አለበት ብሎ ጠብመንጃውን ካነሳና መፋለም ከጀመረ አመታትን አስቆጥሯል።
ሜጀር ጄነራል አብርሀ በኦጋዴን ጦርነት አትራፊ ናቸው ተባለ
ሜጀር ጄነራል አብርሀ በኦጋዴን ጦርነት አትራፊ ናቸው ተባለ
በኦጋዴን ደገሀቡር ውስጥ በመንግስት ወታደሮችና በኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ተዋጊዎች መካከል በተደረገ ውጊያ፤ ከሁለቱም ወገን 32 ሰዎች መገደላቸው ሲገለጽ፤ ጦርነቱን የሚያቀጣጥሉት ከአካባቢው ከሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ ትርፍ የሚያጋብሱ የምስራቅ እዝ የጦር አዛዥ ጄኔራል አብርሀ ወልደማሪያም እና የክልሉ ፕሬዚዳንት ናቸው ሲሉ የኦብነግ አመራር አባል አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት ገለጹ።
በጅጅጋ የሚገኙ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ኦጋዴን ቱዴይ ፕሬስ እንደዘገበው የኦብነግ ተዋጊዎች በደገሀቡር ውስጥ ለቢጋ በተባለ መንደር ባለ የመንግስት የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት ሰንዝረው 30 የሚሆኑ የመንግስት ወታደሮች መግደላቸውን ገልጸዋል።
አፍሮ ሰውየውን ለምን ወደደው?
ቴዲ አፍሮ ሰውየውን ለምን ወደደው?
ድምጻዊ፤ገጣሚና የሙዚቃ ደራሲ የሆነው ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ ለረጅም ጊዜ በተለያየ ምክንያት ከሙዚቃ አልበምና ከመድረክ ስራው ተለይቶ ቆይቶ በቅርቡ #ጥቁር ሰው; በሚለው አዲሱ የሙዚቃ አልበሙ ብቅ በማለት መላውን የሙዚቃ አፍቃሪ በወቅታዊ ብቃቱ መነጋገርያ እስከመሆንና በሙዚቃ አልበሙ ዙርያ የተለያዩ ስሜትና አስተያየቶችን በተለያዩ ጸሃፍትና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች መወያያ ርዕስ ሆኖ መሰንበቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
የዚህ ሙዚቀኛ ጽንፈኛ ደጋፊዎችና በገለልተኛ ሚዛን
ባስቀመጡ አድማጮች መካከል በጋዜጣ፤በመጽሄት፤እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ የመረጃ መረብ በነበረ ፍጭት ግጭትና
ሚዛናዊና ሚዛን አልባ አስተያየቶችን መቋጫ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤት የሆነውን ቴዲ አፍሮ በወረሃ ግንቦት
28/2004ዓም አዲስ አበባ በሚገኘው ሂልተን ሆቴል # የጥቁር ሰው ; አዲሱ አልበም ምርቃ በዓልን ምክንያት
በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችን ይዞ ብቅ ያለው የመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሆነ የሚነገርለት ebs የካሳ ሾው
ፕሮግራም ጋዜጠኛ ጋር እንግዳ በመሆን የነበረውን ቆይታ በተደጋጋሚ መመልከታችን፤ማድመጣችን ይታወቃል፡፡
በኢትዮጵያ በ2003 ዓም ብቻ 100 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ተዘርፎ ወደ ውጭ ባንኮች መግባቱ ታወቀ
ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ጥናቱን ይፋ ያደረገው አለማቀፍ እውቅና ያለው ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ የተባለው ተቋም ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2003 ዓም ብቻ ከኢትዮጵያ በተለያዩ መንገዶች ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ 5 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን 400 ሺ ዶላር ወይም በጊዜው በነበረው ምንዛሬ ወደ 100 ቢሊዮን ብር ነው።
ገንዘቡ የተዘረፈው በአብዛኛው በሙስ እና በታክስ ማጭበርበር ነው። ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እየተዘረፈ ወደ ውጭ ባንኮች ከሚላክባቸው አለም አገሮች መካከል ኢትዮጵያ የ15ኛ ደረጃን ይዛለች። በተጠቀሰው አመት ከቻይና 420 ቢሊዮን፣ ከማሌዢያ 64 ቢሊዮን፣ ከሜክሲኮ51 ቢሊዮን፣ ከሩሲያ 43 ቢሊዮን፣ ከሳውዲ አረቢያ 38 ቢሊዮን፣ ከኢራቅ 22 ቢሊዮን፣ ከናይጀሪያ 19 ቢሊዮን፣ ከኮስታሪካ 17 ቢሊየን፣ ከፊሊፒንስ 16 ቢሊዮን፣ ከታይላንድ 12 ቢሊዮን፣ ከካታር 12 ቢሊየን ፣ ከፖላንድ 10 ቢሊየን፣ ከሱዳን 8 ቢሊየን ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ 7 ቢሊየን እና ከኢትዮጵያ በ ቢሊየን 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ተዘርፏል።
በ2003 ከኢትዮጵያ የተዘረፈው ገንዘብመንግስት በተመሳሳይ አመት ከበጀተው ብሄራዊ በጀት ጋር ተመሳሳይ ነው።
ኢሳት ዜና:-ጥናቱን ይፋ ያደረገው አለማቀፍ እውቅና ያለው ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ የተባለው ተቋም ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2003 ዓም ብቻ ከኢትዮጵያ በተለያዩ መንገዶች ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ 5 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን 400 ሺ ዶላር ወይም በጊዜው በነበረው ምንዛሬ ወደ 100 ቢሊዮን ብር ነው።
ገንዘቡ የተዘረፈው በአብዛኛው በሙስ እና በታክስ ማጭበርበር ነው። ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እየተዘረፈ ወደ ውጭ ባንኮች ከሚላክባቸው አለም አገሮች መካከል ኢትዮጵያ የ15ኛ ደረጃን ይዛለች። በተጠቀሰው አመት ከቻይና 420 ቢሊዮን፣ ከማሌዢያ 64 ቢሊዮን፣ ከሜክሲኮ51 ቢሊዮን፣ ከሩሲያ 43 ቢሊዮን፣ ከሳውዲ አረቢያ 38 ቢሊዮን፣ ከኢራቅ 22 ቢሊዮን፣ ከናይጀሪያ 19 ቢሊዮን፣ ከኮስታሪካ 17 ቢሊየን፣ ከፊሊፒንስ 16 ቢሊዮን፣ ከታይላንድ 12 ቢሊዮን፣ ከካታር 12 ቢሊየን ፣ ከፖላንድ 10 ቢሊየን፣ ከሱዳን 8 ቢሊየን ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ 7 ቢሊየን እና ከኢትዮጵያ በ ቢሊየን 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ተዘርፏል።
በ2003 ከኢትዮጵያ የተዘረፈው ገንዘብመንግስት በተመሳሳይ አመት ከበጀተው ብሄራዊ በጀት ጋር ተመሳሳይ ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)