Translate

Sunday, October 25, 2015

“ዘመድነህ ንጋቱ የኩባንያው ሳይሆን የህወሃት አገልጋይ ናቸው”

ዓለምአቀፉ ኧርነስትና ያንግ ኩባንያ ጉዳዩን እንዲመረምር ተጠየቀ

E&Y


የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ስም የኧርነስትና ያንግ የተሰኘውን የንግድ ሒሳብና ኦዲት ሥራ የሚያከናውን ኩባንያ ከፍተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ዘመድነህ ንጋቱ በኦባንግ ሜቶ ለዓምአቀፉ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች አቤቱታ ቀረበባቸው፡፡

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለዓለምአቀፉ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያ ዋና የሥራ ኃላፊዎች ማርክ ዋይንበርገር እና ሮጀር ደንባር ጥቅምት 9፤2008 ዓም (October 20, 2015) በጻፉት ደብዳቤ የኩባንያው ሸሪክ አስተዳዳሪ አቶ ዘመድነህ ንጋቱ ኩባንያው ከቆመለት ዓላማ ውጪ በመንቀሳቀስ ከህወሃት ጋር በማበር ከሙያው ሥነምግባር ያፈነገጠ አካሄድ በመሄድ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየበደሉ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡
“ላለፉት 14 ዓመታት” ይላል ደብዳቤው “በገሃድ ከሚታየው እውነታ በራቀ መልኩ አቶ ዘመድነህ ሚዛኑን ያልጠበቀና የሃሰት መረጃ በማቅረብ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥሩ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዳለ ሲሰብኩ ቆይተዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካና የገበያ አደጋ ዝቅ አድርጎ እንዲታይ አድርገዋል ብለን እናምናለን፡፡ ስለሆነም አቶ ዘመድነህ የዓለምአቀፉን ኩባንያ የሥነምግባር መመሪያ በመጣስ የድርጅቱን ስም በማጉደፍ ኩባንያውንና የኩባንያውን ደምበኞች ፍላጎት አደጋ ላይ ጥለዋል ብለን እናምናለን” ብሏል፡፡
ደብዳቤው ሲቀጥልም አቶ ዘመድነህ ህወሃት የሚገዛትን ኢትዮጵያ በመወከል በተለያዩ መድረኮች በመገኘት በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስትመንት እንዲካሄድ የሚያደርጉትን ቅስቀሳ ወቅሷል፡፡ እጅግ በርካታ የሆኑ ህወሃት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የተቆጣጠራቸውን ኩባንያዎች በመወከል እንዲሁም በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ በመቀስቀስ አቶ ዘመድነህ የሚያደርጉት ተግባር ከኩባንያው የሥነምግባር አሠራር ጋር የሚጋጭና ኩባንያውንም አደጋ ላይ የሚጥል ብቻ ሳይሆን ሕገወጥ አሠራርም መሆኑን “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ ለበላይ ኃላፊዎቹ አስረድተዋል፡፡
በተለያዩ ዓምአቀፋዊ የሙስና መለኪያዎች መሠረት በኢትዮጵያ የሚገኘው የሙስና አሠራር አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለ መሆኑ እየታወቀ እንደ ባለሙያ ይህንን እውነታ በማሳየት ኢንቨስት የሚያደርጉ ሁሉ ጥንቃቄ እንዲወስዱ ከመምከር ይልቅ ዘመድነህ ንጋቱ ህወሃት በሚገዛት ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር ለኢንቨስትመንት የተመቻቸ መሆኑን በየመድረኩ መስበካቸው ከሥርዓቱ ጋር የተቆራኙ ከመሆናቸው ጋር የተያያዘ ለመሆኑ ደብዳቤው ማስረጃዎችን ጠቅሷል፡፡ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያ ከመመሥረቱ አንስቶ ቢሮውን በአዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ላይ በሚገኘው ሜጋ ሕንጻ ላይ ማድረጉ ከህወሃት ጋር ያለውን ትስስር ገና ከጅምሩ ያደረገ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
በመሆኑም ደብዳቤው ለዓለምአቀፉ የበላይ ኃላፊዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቅርቧል፡-
  • To conduct a thorough assessment/investigation of these concerns in regards to Mr. Zemedeneh Negatu and EY’s East Africa Managing Office, currently under his leadership
  • To appoint an independent body to examine East African Managing Partner’s books and Mr. Negatu’s business activities on the ground in Ethiopia, in the Middle East, Asia and in the US
  • To also require a disclosure of his associations with all the ruling party-owned and regime-affiliated corporations on the ground in Ethiopia, as well as in the US, Europe, Middle East, Asia and other locations.
  • To require that Mr. Negatu and/or his emissaries cease from promoting all FDI in Ethiopia where such promotion favors or is in collusion with the ruling party-owned and affiliated corporations, although few other options exist.
  • To stop Mr. Negatu from using EY’s brand in association with his role as a representative of the Ethiopian government’s foreign investment promotion effort; in particular, where it is used to mislead investors to the reality of the economy. TheVideo presentation at the Turkey-Ethiopia Business Forum on 27 April 2015, in Istanbul, Turkey is the latest example.
  • To require that Mr. Negatu disclose his personal business activities and his association with Fairfax Africa Fund LLC, established in McLean, Virginia and led by the former EY East Africa Managing Partner employee in Addis Ababa, Yared Berhane, regarding the investment of millions of dollars in Ethiopia and East African countries.
  • According to the news, the latest investment offer of Fairfax Africa Fund was the Ethiopian Crown Cork & Can Manufacturing Industry S.C. (ECCCMI), from the government’s Privatization & Public Enterprise Supervising Agency. David Johns, Director of Fairfax is a newly hired US national who may be a front to make it appear that the fund is an American investment, when in actuality; it is believed to be a ruling party-affiliated business. The website, All Africa, reported that Mr. Negatu was the principle representative of the fund in the purchases of ECCCMI. Interestingly, he was invited to speak at the Fairfax Africa Fund’s organized event: “Collaborative Investing by the Ethiopian Diaspora in the U.S” on at least two occasions in California in February of 2012.
በተለይ በመጨረሻው ላይ ዘመድነህ ንጋቱ እና በአሜሪካ አገር በቨርጂኒያ ጠቅላይ ግዛት የሚገኘው Fairfax Africa Fund LLCየተባለው ድርጅት ያላቸው ግንኙነት እንዲመረመር የተጠየቀው የአቶ ዘመድነህን ከህወሃት ጋር ያላቸውን ድብቅ ግንኙነት የሚያጋልጥ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ Fairfax Africa Fund LLC ዴቪድ ጆንስ የተባለ አሜሪካዊ የሚመራው ድርጅት ሆኖ ለይስሙላ በግምባር የተቀመጠ ቢሆንም ድርጅቱን ከኋላ የሚመራው የቀድሞ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያው ሠራተኛ የሆነው ያሬድ ብርሃኔ መሆኑ አቶ ዘመድነህ ከህወሃት ጋር የተጠላለፈ ንግድ የሚፈጽሙ የሥርዓቱ ደጋፊ መሆናቸውን ያጎላ ሆኗል፡፡ ያሬድ ብርሃኔ የሚመራው የውጭ ኩባንያ ተብሎ የተሰጠቀሰው ድርጅት የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ለሽያጭ የሚያቀርባቸውን ድርጅቶች እያመቻቸ እና እያስማማ የሚያሸጥ የህወሃት ውክልና ያለው እንደሆነ ተግባሩ እንደሚመሰክር ከደብዳቤው ላይ የተገኘው መረጃ አስረድቷል፡፡ በመሆኑም ይህንን መሰል አሠራር ውስጥ የሚገኙት ዘመድነህ ንጋቱ በአለቆቻቸው እንዲጠየቁና ሕገወጥ ከሆነው እና በግፍ ኢትዮጵያን እየገዛ ካለው ሥርዓት ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዲመረመር አቶ ኦባንግ በደብዳቤያቸው ጠይቀዋል፡፡
ይህ ደብዳቤ ለዓለምአቀፉ ድርጅት የሥራ አመራሮች መድረሱን በተመለከተ ጎልጉል መረጃ የደረሰው ሲሆን ጉዳዩ በይፋ የወጣና ለዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ላይ እንዲያውቁት የተላከ በመሆኑ የኩባንያው አመራሮች ይፋዊ ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቶ ኦባንግ የጻፉት ደብዳቤ ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡-

No comments:

Post a Comment