Translate

Thursday, September 7, 2017

ዜና ጎንደር – ህዝቡ የአፀፋ እርምጃ እየወሰደ ነው

አስናቀው አበበ – ጳጉሜ 2 2009
ጳጉሜ 1 2009 እለት ጎንደር በአድዛ እና ሎዛ ቀበሌወች የወያኔ በአርራና ቅማንት ስም የተደገሰ ህዝብ ከፍፋይ ምርጫ ምዝገባውን ለማስፈፀም የሄዱ ሆምዳ ባለስልጣናት ላይ ህዝቡ የቅጣት እርምጃ ወስዶባውልዋ። ባንዳወቹ ተደብድበው መኪናቸው ተሰባብሯል። ከተመቱት ውስጥ ፖሊስ እና ከጎንደር የሄደች አቃቢ ህግ እንደምትገኝበት ታውቋል።
ትናንት ከሰሜን ጎንደር ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ስለምርጫው ለመዘገብ እና ሁኔታውን ለማየት ሄደው ነበር። አጋጣሚ ለቅሶ ስለነበር ከደንቢያ ጭልጋ እና ላይ አርማጭሆ የመጡ ሰወች ነበሩ። በምርጫው እጅግ ተበሳጭተው ስለነበር መኪናው ላይ ጥቃት አድርሰዋል። የመኪናው መስታውት ሙሉ ተሰባብሯል። የሄዱትም ተላላኪ ተሿሚወች ተደብድበዋል። የቀበሌው ሰወች የተበሳጩበት ምክኒያት ምርጫ የሚካሄዱበት ቦታወች አማራ የሚኖርበት ከመሆኑ አልፎ ለምን ህዝቡን ሊከፋፈሉ መጡ በማለት ነው።
አማራውን በማፅዳት የቅማንት የራስ አስተዳደርን ለማስፈን ወያኔ የያዘውን የመለያየት ተንኮል የተረዱና የተቃወሙ የብአዴን የአካባቢው ባለስልጣን የነበሩ ከአመራርነት እየተነሱ መሆናቸው ታውቋል።

ይህ በዚህ እንዳለ በምርውጫ አስፈላጊነትና ፍትሃዊነት ህዝቡ ባያምንበትም የነጋዴ ባህር ህዝብ እና የመተማ ህዝብ በነቂስ ለምርጫው እየተሳተፈ መሆኑን ተረድተናል። ለሌላውም ቀበሌዎች በነቂስ ወጥቶ እንዲመርጥ ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ቅስቀሳ እየተደራረገ ይገልኛ። ገሃድ የወጣውን አማራን እናፅዳ የሚለውን የቅማንት ኮሚቴ ዶክመንት ህዝቡ እጅ ስለገባ ትልቅ ቁጣ ፈጥልሯ። ኮሚቴውም ከዚህ በላይ እንደሚያደርጉ ነግሮኛል።
በነዚህ 12 ቀበሌወች የሚገውኘ አብዛኛው ነዋሪ አማራ በመሆኑ ምርጫው ከመጀመሪያው መደረግ እንዳልነበረበት ነገርግን በትክክል ከተደረገ ግን ውጤቱ ግልፅ ነው። ነገር ግን ወያኔ 5400 በላይ ቅየንማት መውቅቂያ የታደላቸው በየቀልሌወቹ በተመደበላቸው መኪና እየተዘዋወሩ ድምፅ የሚያስገቡ አዘጋጅቷል ይህም ካልተሳካ ኮሮጆ ለቅቀየር ወያኔ እንደተዘጋጀ ያፈተለከው ማስረጃ ሰነድ አጋልጧል።
ከቦታው መረጃውን የላኩት ወገኖች መታወቂያ እየተሰጣቸው ከሌላ ቦታ ለመምረጥ የሚመጡትን ህዝቡ መከላከል እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋል። በነጋዴ ባህር እና በመተማ ጨምሮ ብዙ ቦታ ላይ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።

No comments:

Post a Comment