“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”። የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ ከተናገረው። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።
ዛሬ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይ የህወሓትን ማስፈራሪያና ዛቻ ከምንም ባለመቁጠር የውቅሮ፣ ዓዲግራት፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደሴና ሌሎች አካባቢዎች ህዝብ “ባለኮከቡን ባንዲራ አይወክለኝም” በማለት ኮከብ አልባውን ሠንቀድ ዓላማ ይዞ በመውጣት እምቢተኝነቱን አድፍረት አሳይቷል።
ሃይለኪሮስ ታፈረ (Hailekiros Tafere) በፌስቡክ ገጹ የዘገበውን አስመልክቶ አምዶን ገብረሥላሴ ይህንን ብሏል፤
“ፖሊስ “ኮከብ የሌለው ባንዴራ ዳሜራ ሸፍናቹሃል” በሚል ሰበብ ዛሬ መስቀል በዓል እያከበረ የነበረው የውቅሮ ከተማ ህዝብ ላይ ድብደባ ፈፅመዋል። የውቅሮ ፖሊስ የመስቀል ዳሜራ በኮከብ የሌለው ባንዴራ ሸፍናቹሃል በማለት በህዝቡ በተለይ በወጣቶችና ህፃናት ላይ ድብደባ ፈፅመዋል። ህወሓት በስመኮከብ ህዝበ ክርስትያን ድብደባ ፈፅማለች።”
በጎንደር፣ በደሴ፣ በመቀሌ፣ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝቡ በተመሳሳይ እምቢተኝነቱን ኮከብ አልባውን ሠንደቅ ይዞ በመውጣት አሳይቷል።
በአዲስ አበባ ከበሮውን በባለኮከቡ ጠቅልለው የወጡትን አስመልክቶ እሸቱ ሆማ ቀኖ Eshetu Homa Keno) ይህንን በማለት ተሳልቋል፤
“የሰንደቅ አላማ አዋጁ አንቀፅ 23(9) ደግሞ ሰንደቅ አላማን የህንፃ ወይም የሌሎች ቁሳቁሶች መሸፈኛ ማድረግ የተከለከለ ነው፣ እስከ 3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ወይም እስከአንድ አመት እስር ያስቀጣል ይላል፤ ያው ለማስታወስ ያህል ነው”
ይህንኑ ፎቶ በቅድሚያ በፌስቡክ ገጹ በመለጠፍ ስዩም ተሾመ (Seyoum Teshome) የሚከተለውን አስፍሯል፤
“እዩ እስኪ፣ #የባንድራው_ኮከብ ካሜራው ውስጥ “ገባ-አልገባ” ብለው የተጨነቁ አይመስልም? ታዲያ በእነዚህ ምዕመናን አዕምሮ ውስጥ እየተመላለሰ ያለው #የአምላክ ሥራ ወይስ #የመለስ ሥራ ነው?”
አፍቃሪ ህወሓት የሆነው የፌስቡክ “አርበኛ” ዳንኤል ብርሃኔ በዛሬ በጎንደርና ደሴ ከተሞች በተካሄደው የመስቀል በዓል አከባበር ላይ ኮከብ የሌለበት ባንዲራ ጥቅም ላይ መዋሉን አስመልክቶ በቀጣይ ቀናት አንዳንድ ውዝግቦች ሊነሱ ስለማለቱ ስዩም ይህንን ምላሽ ሰጥቷል።
“ይህ ባለ ኮከቡ ባንዲራ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንደሆነ የተደነገገው የኢፊድሪ ሕግ-መንግስት ላይ ነው። ነገር ግን፣ ሕገ-መንግስቱን በመጣስ ግንባር ቀደሙ #የኢህአዴግ_መንግስት ራሱ ነው። “ባለቤቱ የናቀው አሞሌን ማንም አይፈልገውም!” እንዲሉ ኢህአዴግ የናቀውን ሕገ-መንግስት #የጎንደርና_ደሴ ህዝብ የሚያከብረው በምን ዕዳው ነው?! ሀገሪቱ እየተመራች ያለው #በፀረ_ሽብር አዋጁ እንጂ በሕገ-መንግስቱ አይደለም። እሱ ደግሞ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላም ላይ ያለው አንባሻ ይሁን ኮኮብ አይደነግግም! ስለዚህ የጎንደርና ደሴ ህዝብ ከፈለገ #የራስተፈራያን ባንዲራ ይዞ መስቀልን ማክበር ይችላል!!!”
ስዩም በጽሁፉ መጨረሻ ላይ ከላይ የጠቀስነውን ሃሳብ ብዚህ መልኩ ደግሞታል፤
“የታፈነ ሕዝብ ያምፃል!” የጎንደር፥ ደሴ፥ ዓዲግራትና ውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች የመስቀል በዓል አከባበርን ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ መጠቀማቸው ከላይ ከጠቀስኩት ጋር ተመሳሳይ ነው። አመፅና ተቃውሞ አደባባይ ወጥቶ ድንጋይ መወርወር ብቻ አይደለም። የመንግስትን ቅቡልነት ሊያሳጣ የሚችል ማንኛውም ዓይነት ነገር መፈፀም ነው።”
የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም በሁሉም አቅጣጫ የህወሓት/ኢህአዴግን አገዛዝ አልቀበልም እያለ በሚያገኘው አጋጣሚ ሁሉ እምቢተኝነቱን እየገለጸ ነው! ትውልድ አምጿል! ሕዝብ እምቢ ብሏል!
No comments:
Post a Comment