Translate

Tuesday, September 26, 2017

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ የቀረበ ክስ

Image may contain: 1 person, standing
(ይህ ክስ በሚገባ ለህዝብ ደርሷል የሚል ግምት የለኝም። ምን አልባት ኮሎኔሉ በፀረ ሽብር አዋጁ ያውም ከ15 አመት እስከ ሞት የሚያስቀጣ አንቀፅ እንደተጠቀሰበትና ስለ ዝርዝሩንም ብዙ ሰው መረጃ ላይኖረው ይችላል። አማራ ክልል (ከጎንደር አልፎ እስከ እንጅባራ) ለነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ ኮሌኔሉን ተጠያቂ አድርገውታል። የክሱ ዝርዝር ኮሎኔሉን ከግለሰብም በላይ አድርጎ አቅርቦታል። በሌሎች ክስ መዝገቦች የተጠቀሱ ጉዳዮችም በኮሎኔሉ ላይ ክስ ሆነው መጥተዋል። ለአብነት ያህል ወደመ የተባለው ንብረት በብዙ መዝገቦች በክስነት ቀርቧል። በሌላ ክስ መዝገብ ተከሳሽ የሆኑት የኮሚቴው ባላት እንደ አባሪ በስፋት ክሱ ላይ ስማቸው ተጠቅሷል። አላስፈላጊ የመሰለኝን የክስ ዝርዝር አላካተትኩትም።)
ለአማራ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ ቤት
ባህርዳር
ቀን 25/02/ 2009 ዓም (ክስ የተመሰረተበት)
የፌ/ጠ/ዐ/ወ/መ/ቁ 157/09
የፌ/ፖ/ ወ/ መ/ቁ 04/09
ከሳሽ_ የፌ/ ጠቅላይ ዐ/ህግ
ተከሳሽ_ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ አየለ፣ እድሜ 45 አመት
አድራሻ _አማራ ክልል ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18፣ የመ•ቀ _አዲስ
1ኛ ክስ
በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀለኛ ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ ፣ ለ ፣ 38 እና በ2001 የወጣውን የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/ 2001 አንቀፅ 3(1)፣(2)፣(4) እና (6) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ፣

የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በቀጥታ እንዲሁም በሙላ ሀሳቡ ወንጀል ድርጊቱና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል የማፍረስ ዓላማ ይዞ ዓላማውን ለማስፈፀም እና መንግስት ላይ ተፅዕኖ በማሳደር ህብረተሰቡን ለማስፈራራት የሀገሪቱን መሰረታዊ ፣ፖለቲካዊ፣ ህገ መንግስታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይንም ማህበራዊ ተቋማትን ለማናጋት እና ለማፈራረስ ከሚንቀሳቀሰው ራሱን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ብሎ የሚጠራውን የሽብር ቡድን የሽብር ተልዕኮ ለማስፈፀም እራሱን የወልቃይት ህዝብ የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ በሚል አቋቁሞ የኮሚቴው ፕሮፖጋንዳ ሀላፊ በመሆን ከሌሎች የኮሚቴው አባላት ከሆኑት መብራህቱ ጌታሁን፣ ጌታቸው አደመ እና አታላይ ዛፉ ጋር በመሆን የማንነት ጥያቄውን ሽፋን በማድረግ ከሽብር ቡድኑ አመራሮች ጋር በቀጥታ ግንኙነት በመፍጠር በትግራይ ክልላዊ መንግስት እና በወልቃይት መስተዳደሮች ላይ የግድያና የአፈና እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለወጣቶች ጦር መሳሪያ አስታጥቀው በማስፈራራት፣ ዳንሻ ከተማ ግለሰቦች እንዲገደሉ በማድረግ፣ በቃፍታ ወረዳ መስተዳደሮች ላይ የግድያ ሙከራ በማድረግ፣ በዳንሻና ሰሮቃ መንገድ እንዲዘጋ በማድረግ የወልቃይት ህዝብ ለአመፅ እንዲነሳ በማድረግ እና የመንግስትን መዋቅር ለማፈራረስ በመንቀሳቀስ፣
………………
………………
……………
(መሃል ላይ የታለፈ ዝባዝንኬ ክስ አለ)
……………
…………
………………
ተከሳሽ የኮሚቴ አመራሮች ጋር በመሆን ከአርበኞች ግንቦት ሰባት የሽብር ቡድን ኤርትራ ከሚገኘው ሠረበ ጥሩነህ እና ሀገር ውስጥ ካለው የሽብር ቡድን ( አባል ) ደጀኔ ማሩ ግንኙነት በማድረግ የማንነት ጥያቄ እንደሽፍን በመጠቀም ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የግንቦት ሰባት ታጣቂዎች እና የጦር መሳሪያ (ይዘው) እንዲገቡ በማድረግ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን ፀገዴ ወረዳዎች በተለያዩ አካባቢዎች መንገድ በመዝጋት የመንግስት መስተዳደሮች ላይ ግድያ እንዲፈፀም ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አባላትን በመመልመል እና መሳሪያ በማስታጠቅ በመንቀሳቀስ ላይ ሳሉ የፀጥታ ሀይሎች ያንን ድርጊት ለማስቆም በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ የ(በ)ፍ/ቤት የመያዣ ትዕዛዝ በ05/ 11/ 2008 ዓም ተከሳሽ እጅ እንዲሰጥ ሲጠየቅ ያልተያዙ ግብረ አበሮቹን በመጥራት በፀጥታ ሀይሎች ላይ ተኩስ በመክፈት እና ቦንብ በመወርወር ፣
1ኛ) ኮማንደር ሃለፎም አዳነ
2ኛ) ረ/ ኢን/ር አህመድ ሁሴን
3ኛ) ረ/ኢን/ር አደን አብዱላሂ
4ኛ)ብርሃኑ ሲሊቶ
5ኛ) ኮ/ል ኤቢሳ ኢታና
6ኛ) ም/ ሣጅን አብዲ አለሙ
7ኛ) ም/ ሣጅን አለሙ መላኩ
8ኛ) ሣጅን ናስር መሽሮ
9ኛ) ሣጅን አትሎግ አሰፋ
10ኛ) ም/ አስር አለቃ ሄኖክ ስጦታውን በጥይትና በቦንብ ጥቃት በመፈፀም ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረገ ሲሆን
1ኛ) ሀሰን አብዲ የግራ እግሩ ከጉልበት በታች እንዲሰበር
2ኛ) ም/ ሣጅን ሳተናው ጅፋር የግራ ክርኑ ጡንቻ እና ነርብ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የጣቶቹ ሁኔታ በእጅጉ እንዲጎዳ በማድረግ፣
3ኛ) መካሻው አህመድ ጉልበቱ ላይ ስብራት እንዲደርስ ማድረግ፣
4ኛ) አስር አለቃ ኢብራሂም አብዱ በሁለት እግር ላይ ከሁለት ታፋና ከጉልበቱ በታች ከፍተኛ ጉዳት፣
5ኛ) አስር አለቃ ሀይለኛው አሰፋ ከጉልበቱ በታች ሁለቱ እግሮቹ እና የእጁ ክንድ ከፍተኛ ጉዳት
6ኛ) አስር አለቃ ሙሉቀን አሰፋ በቀኝ እግሩ ታፋ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ
7ኛ) ዋ/ ኢ/ር ከፍ ያለው ጀምበሩ በእግሩ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት በማድረስ እንዲሁም ያልተያዙ የሽብር ቡድኑ አባላት ከሽብር ቡድኑ አመራሮች የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት በማሰብ ሀምሌ 5 ቀን 2008 ዓም እስከ ነሃሴ 25 ቀን 2008 ዓም በተለያዩ ቀናት በሰሜን ጎንደር፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በደባርቅ፣ በወረታ፣ ደንቢያ፣ ወገራ፣ በምዕራብ አርማጭሆ፣ በመተማ ዮሃንስ፣ በመተማ ዙሪያ፣ ባስነሱት አመፅ በመንግስት ( እና) ህዝብ ተወቋማት፣ በግለሰብ መኖሪያ ቤት፣ በድርጅት፣ በመንግስትና በግለሰብ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲሁም ኮድ 61630 ኢት ሰላም ባስ በማቃጠል 95, 345,363,56 (ከዘጠና አምስት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አምስት ሺህ መቶ ስድሳ ሶስት) ብር በላይ የሚገመት ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ ተሳታፊ ሆነዋል።
በአጠቃላይ ተከሳሽ ከልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የወልቃይት አማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ሽፋን በማድረግ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ተግባር ሲፈፅም ቆይቶ ይህን ድርጊት ለማስቆም የፀጥታ ሀይሎች የፍ/ ቤት መያዣ ትዕዛዝ በመያዝ ለህግ እጁን እንዲሰጥ ሲጠየቅ ግብረ አበሮቹን በመጥራት ተኩስ በመክፈትና ቦንብ በመወርወር 10 የፀጥታ ሀይሎች ህይወታቸው እንዲያልፍ፣ በ7 የፀጥታ ሀይሎች ላይ የከባድ አካል ጉዳት እንዲደርስ እንዲሁም በመንግስት እና ህዝብ ተቋማት፣ በድርጅቶች ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ የሆነ ንብረት እንዲወድም ያደረገ በመሆኑ በፈፀመው የሽብርተኝነት ድርጊቶችን መፈፀም ወንጀል ተከሷል።
2ኛ ክስ
በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 256/ ለ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ፣
ተከሳሽ በህገ መንግስቱና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ በሀይል፣ በአመፅ እና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ለማፈራረስ በማሰብ በቀን 06/11/ 2008 ዓም በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ
1ኛ) አንድ እግር ክላሽ
2ኛ) አንድ ማካሮቭ ሽጉጥ
3ኛ) አንድ ኤፍዋን ቦንብ
4ኛ) ሁለት የጭስ ቦንብ የጦር መሳሪያዎች አከማችቶ የተገኘ በመሆኑ የተንኮል ድርጊቶችን ግዙፍ በሆነ አይነት መሰናዳት ወንጀል ተከሷል።
ብርሃኑ ወንድማአገኝ*
መኩሪያ አለሙ*
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
*የሁለቱ ዐ ቃቤ ህጎች የማይነበብ ፊርማ አለበት

No comments:

Post a Comment