የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው የተጠለፈው አይሮፕላን
-ከ አዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 702 ጄኔቭ ላይ ዛሬ የካቲት 10/2006 ዓም በማዕከላዊ የአውሮፓ ሰዓት ከማለዳው 12 ከ 02 ሲሆን እንዲያርፍ ተገዷል።
- ሁሉም ተሳፋሪዎች እና አይሮፕላኑም በደህና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።
- ለ 2 ሰዓት ከ 45 ደቂቃ ተዘግቶ የነበረው የጀኔቭ አየር ማረፍያ ተመልሶ ተከፍቷል።
- ጠላፊው ረዳት አብራሪው ነው።
- ዋና አብራሪው ወደ ሽንት ቤት ሲሄድ ረዳቱ ሽንትቤቱን ቆለፈበት እና አይሮፕላኑን ጠለፈው።
- አብራሪው ካለ አንዳች ማንገራገር እጁን ለስዊዝ ፖሊስ ሰጥቷል።ጥገኝነት እንዲሰጠውም ይፈልጋል።
- አይሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች 143ቱ ጣልያናውያን ናቸው።
- ''ዘ ሎካል'' የተሰኘው የስዊዝ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው በስዊዘርላንድ ሕግ መሰረት ወንጀሉ እሰከ 20 አመት እስር ሊዳርግ ይችላል።
- ''ዘ ሎካል'' ጋዜጣ አክሎም በድረ-ገፁ ላይ የጠላፊውን ቃል በድምፅ እንዲህ ሲል አሰምቷል '' ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈን የማንሰጥ ለመሆናችን ዋስትና እና ጥገኝነት እንዲሰጠን እንፈልጋለን''
''The local'' Switzerland news paper http://www.thelocal.ch/20140217/ethiopian-plane-lands-in-geneva-after-hijacking
ጉዳያችን
የካቲት 10/2006 ዓም
No comments:
Post a Comment