Translate

Wednesday, February 19, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ ረዳት ካፕቴን መጠለፍ የአገራችንን የአመራር ችግሮችና የሃሣብ ድህነት ክፉኛ አጋልጧል!

በክፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory

የካቲት 17 በጥዋት የጠለፋውን ዜና እንደስማሁ፡ የቅድምያ ተግባሬ ያደረግሁት ለማዘጋጀው ድህረ ገጽ መረጃዎችን ማሰባስብና መረጃዎቹን መመዘን ነበር። ለዚህም ስል: ያሰባስብኩት መረጃ ምን ያህል ለእውነተኝው ሁኒታ ቅርበት አለው የሚለውን በመመዘን ጥቂት ጊዜ አሳለፍሁ።Ethiopian Airlines was absorbed by the TPLF mafia
አንዳንዶቹ ለጊዜው ትክክል ባይሆኑም፡ እንዳለ ማቅረቡ ምክንያታዊ እስከሆኑ ድረስ: ዛሬ ያለውን የመረጃ ጥማት ማርካት ብቻ ስይሆን፡ ለወደፊትም አንድ ሁኔታ በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እንዴት ተዘገበ ለሚለው በምስክርነት ሊረዳ ይችላል።
በወቅቱ በአንድ ጊዜ፡ በተከታታይ በገጼ ላይ እንዳቀረብኩት ሁሉ፡ ብዙ የውጭ ምንጮችን ቃኝሁኝ። ጠቃሚ መረጃዎችንም አገኝሁኝ። በዚያን ወቅት አንድ ነገር ያላድረግሁት ነገር፡ መረጃ ከኢትዮጵያ ለማግኝት መሞከር ነበር። አንደኛ መረጃ ቢኖራቸውም፡ ቀዳሚው መንፈሳቸው የሚቀናው መረጃውን ማፈን ነው!

በሌላ በኩል ደግሞ፡ አውሮፕላኑ ከተጠለፈበት አገር በመጀመርያ ደረጃ መረጃ ማግኘቱ ጠቃሚነቱ ቢታወቅም፡ እንደ ኢትዮጵያ ዐይነት መረጃ መጀመርያ በባልሥልጣኖች መወሰን ባለበት ሃገር ውስጥ፡ ሲተሻሹ ጀምበር ስለሚጠልቅባቸው፡ የሃገር ውስጥ ሚዲያ ዜናውን እንዲያወራ ቢፈቀድለት እንኳ፡ እነርሱም እኛ ገና በማለዳው ያየናቸውን የሮየተርስ፡ ቢቢስ፣ ሲኤኔአንን ወዘተ ነው መልሰው የሚደጋግሙት።
ለማንኛውም፡ አቶ ረድዋን ሁሴን ወደሚዲያ ከቀረቡበት ክረፋዱ በኋላ የነበረው ሁኔታ ግን ክፉኛ ተሳከረ።
አንድኛ፡ ሥዕል ውስጥ ጠላፊው ረዳት ካፒቴን አንድ መሆኑ ቀርቶ ክአንድ በላይ የሆኑ ጠላፊዎች አውሮፕላኑ ውስጥ መግባታቸውን አስሙን።
ሁለተኛ፡ አውሮፕላኑን የጠለፊው ሰው እኔነኝ ብሎ ጠላፌው እጁን ለስዊስ መንግሥት ከሰጠ በኋል: አቶ ረድዋን ጠላፊዎቹ እያሉ በሕዝበ መገናኛ ላይ መንዛታቸውን ቀጠሉ።
ሶስተኛ፡ የዚህ ዐይነት አጣዳፊ ሁኔታ፡ በየፈጣን ደቂቃዎች የሚለዋወጡበት በመሆኑ አስቸጋሪነቱ ግልጽ ነው። ቢሆንም፡ አቶ ረድዋን የተለመደውን የመንግሥታቸውን ቀጣፊነት ባህሪ ማንጸባረቅ ስለነበረባቸው፡ ትኩረታቸው ያረፈው፣ የራሳቸው ዕውነታ (realty) ላይ ሆኖ ዜና ፈጠራ ላይ ነበሩ። ይህም እርሳቸውን እንደግለሰብ ቀባጣሪ ከማድረጉም በላይ፡ ሀገራችንን አሳፋሪ ሁነታ ላይ ጥሏታል።
በእዲህ ያለሁኒታ ውስጥ፡ ማንኛውም ባለሥልጣን ተረት ተረት (fiction) ከመፍጠር ይልቅ፡ በሠለጠነው ዓክም እንድሚደረገው፡ “ለጊዜው መረጃ የለኝም፡ እስካገኝ ጠብቁኝ” ማለቱ ያስከብራል እንጂ አያስንቅም – ባልሥልጣኑ ቃሉን ጠብቆ ያ መረጃ ካለበት ቦታ ቆፍሮ ለጠያቂዎቹ የማቅርብ ቁም ነገርኝነቱን እስካስመስከረ ድረስ!
መንግሥታቸው ለሥልጣኔ አስጊ ናቸው ብሎ የሚጠራጠራቸውን ንጹሃን “አሽባሪዎች” እንደሚላቸው ሁሉ፡ ከዚህ የአውሮፕላን ጠላፍ ጋር በተያያዘ አቶ ረድዋን ዋናዋ ተጠራጣሪ ሱዳን መሆኗን የራሳችውን ውንጀላ ሠነዘሩ።
እኔ የሱዳን ባለሥልጣን ብሆን አንድ ትልቅ የዲፕሎማቲክ የቅሬታ ማስታወሻ (demarche) ለአዲስ አበባ ሳይውል ሳይድር እንዲቀርብ አደርግ ነበር። ለማንኝውም እነዚያም እጆቻቸው ብዙም ጻዳ ባለመሆናቸው፡ ብዙም ላይረበሹ ይችሉ ይሆናል። እንዲያውም፣ የተባበሩት መንግሥታት የራሱንና የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን ስላም አስከባሪ ሃይል ዳርፉር ውስጥ በሥውር በመውጋት ላይ የምተገኘው ራሷ ሱዳን ናት የሚለው የእሁዱ ክስ በቂ ምስክርነት ይሰጣል። (UN report points finger at Sudan over UNAMID attacks)
ሌላው አስገራሚው ነገር፡ የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን ቅጥፈት ነው። የአውሮፕላኑ ጠላፊ ረዳት ካፒቴን “ኃይለመድህን አበራ” (ክአህራም የተገኝ) ክሲቪል አብቭዬሽን ሠራተኞች ጋር ተደጋጋሚ የአየር ላይ ግኑኝነት አድርጎ በመስኮት ወጥቼ መጣለሁ ማለቱን እየስሙና: እጁን በሰላማዊ መንገድ ለስዊስ ፖሊሶች መስጠቱ እየተስማ፡ “ሊያመልጥ ሲል ተይዞ በቁጥጥር ሥር ዋለ” በማለት ያቀረቡት ሀስት ዜ ለአንዴና ለመጭረሻ ጊዜ አገራችን ምን ያህል በወበዴዎች ቁጥጥር ሥር መሆኗን አረጋግጦልኛል።
ይህ ደግሞ የሚመነጨው – በቅርቡ በረከት ስምኦን እንዳለው – ከሕዝብ ንቀት ነው። የፈለግነውን ብንቀባጥርለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያምነናል ከሚል የዋህ አስተሳሰብ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ራስቸውን ብቻ ነው ያዋረዱት!
በራሱ ካፕቴን የተጠለፈው አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ ረዳት ካፕቴን መጠለፍ፡ በዓለም ታሪከ ውስጥ ውሱንና ጥቂት ተጠቃሽ ምሳሌዎች ያሉት ውርደት ነው። በባለሙያ ደረጃ ግለስቡ ደህና ደሞዝ ያገኛል (በአንጻራዊ ደረጃ ከኅብረተስቡ ጋር ሲወዳደር – ከሕወሃት ባልሥላጥኖችና ካድሬዎች ጋር ባይሆንም)። ስለዚህ ይህ ሰው የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው እንዲሰደድ ወይንም አውሮፕላን ጠልፎ ስደት እንዲጠይቅ ያስገደደው ለማለት አይቻልም።
ይህ ሁኔታ ደግሞ አገራችንን ወደተጠናወታት፡ የመብት ረገጣና የስብአዊ መብቶች ገፈፋ እያመለከተ ነው። ጤንነቱን መጠራጥር አይቻልም – የመንግሥት የፕሮፓጋንዳው ሹም፡ ፓይለቱ የወንጀል ሪኮርድ የለበትም፡ ጤንነቱንም በተለመከተ “was medically sane until otherwise proven” ሲሉ መናገራቸውንቢቢሲ ስኞ ከቀትር በኋላ ዘግቦታል
ይህ ደግሞ ወደዋነኛው ሀቅ ይመልስናል – ይህም የኢትዮጵያ ችግር የመንግሥትና የአስተዳደር እንጂ፡ ሌላ እንዳልሆነ ነው!
በሕወሃት አመራር ወዳዘቅቱ
የኢትዮጵያ ችግር ከቀን ወደቀን እየከፋ የመጣው በዘረኛው መንግሥት ፓሊሲዎች ምክንያት ነው። ሲሻው አማራ፡ ኦሮሞ፡ ሶማሌ … ብሎ ከፋፍሎ ሊያባላን የተነሳ መንግስት ነው ያለን። በቅርቡ ሆድ አደር አዝማሪ በፓለቲካ አመራር አማክይነት በብአዴን ድሕፈት ቤት ሃላፊ የተሰነዘረው – በዓለም አቀፍ ሕግ በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጅል ተደርጎ የሚወስደው – ጸረ አማራ ወራዳ የስድብ ጋጋታ ሥርዐቱ ከነሥረ መሠርቱ ያለውን ብልሹነትና ወንጀልኝነት የሚያሳይ ነው።
ባልሥልጣኖቹ ይህን ባስተጋቡ መጠን ተለክቶ የፓሊቲካ ጽዋቸው ይሠፈራል! መዘንጋት የሌለበት፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት በስመ ኦሮሞ ነጻ አውጭ ውንጀላ ፓርላማ ውስጥ ያስሙት/ያሰማው ጸረ-ኦሮሞ አነጋገር፡ በዘፈቀደ የመጣ አይደለም – ሕወሃት ሀገራችን ውስጥ የዘራው ቫይረስ ውጤት ነው!
በቅርቡ የአገሪቱን ዳር ድንበር በመሽረፍ ለሱዳን የአርሻ መሬት ለመስጠት የተደረገው ምሥጢራዊ ስምምነት፡ ለኢትዮጵያም ሆነ ለሕወሃት ትልቅ የጥፋት ምንጭ ይሆናል። ጸጥ በለው ክርመው፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡ ስሞኑን ይህንን ለማስተባበል ሞክሩ። ሆኖም፡ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ጅምረው ባሉት 18 ወራት ግን ሃይማኖታቸው ሃስት መናገርን ሲከለክላቸው አልተመለክትንም።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሸርሸር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኩራታቸን ክሆነባቸው ምክንያቶች አንዱ የፓይለቶቻችንና የመካኒኮቻችን ብቃት፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የኩባንያውያን ኢትዮጵያውያንነት ለማሳደግና ለማበልጸግ ማስቻሉ ነበር።
ዛሬ ግን ኢትዮጵያዊ ፓይለቶች በዘር ልዩነት ምክንያት እየተገፉ፡ የሚወዱትን ኩባንያ እየተዉ ወደመካከለኛው ምሥራቅና በየአህጉሩ እይተበተኑ ናቸው። ዛሬ በጣሊያን አብራሪ የሚመራው አውሮፕላን – ኢትዮጵያዊ ሳይሆን – መጠለፍ፡ በዘረኛው ሕወሃት መዳፍ ሥር አገራችን በየፊናው የምታመራበትን አዘቅት የሚያመላክት ነው!
ኢትዮጵያውያን ለአገራችን ቀናተኞች ነን- አገርን አሳልፎ መሽጥ ባህላችን አይደለም። አልጨበጥ ባይነት፡ ቀባጣሪነትነና በዜጎች ጉስቅልና ላይ የፕሮፓጋንዳ ድራማ መሥራት (ሳኡዲ በነበሩት ላይ እንደተፈጸምው ሁሉ)፡ ኃይልን ተገን አድርጎ መክናፈስ ፍጻሜው መጥፎ ነው – ታሪክ እንደሚያሳየን!
ታዲያ በጥቂቶች ጠባቦችና የሥልጣን ባለጌዎች መጥፎነት ለምን መላው ሃገር ይታመሳል? ህገርስ ዐይናችን እያየ ለምን አገር ወደአዘቅት ታምራ?
ይህንን የመገንዘቡ አዝማሚያ በማይታይበት በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ነው ዜጎች በየቀኑ እየተገፉ እየተረገጡ ሊቀጥሉ የሚችሉት? በመንግሥት ሥልጣን ላይ መንግሥታዊ ባህሪ የሌላቸው ስዎች በመቀመጣችው፡ የባሱ ዜጎችን የሚያሽማቅቁ፡ አገር ሊያውርዱ የሚችሉ፡ ትውልድን የሚያሳፍሩ ገና ብዙ ነግሮች ሊመጡ ይችላሉ – በመንግሥት ላይ የሠፈሩት ሆድ አደሮች ቆም ብለው ከአሁኑ አሳፋሪ ነገር አንዳችም መማር ካልቻሉ።
በነገራችን ላይ፡ ገና ከማለዳው አውሮፕላኑ እንደተጠለፈ የብዙዎቹ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ገለጻ: ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የስብአዊ መብቶች ላይ ማተኮራቻው በቂ ምልክት ተደርጎ ሊወስድ ይገባል!

No comments:

Post a Comment