Translate

Wednesday, February 12, 2014

የአዲሲቱ ኢትዩዽያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ

የሺሀረግ በቀለ (ኖርዌ)

Obang Metho in Norway
ተወዳጁ የሰብአዊ መብት ተከራካሪና የአዲሲቱ ኢትዩጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በ8-2-2014 በኖርዌ ኦስሎ በመገኘት ከኢትዩዽያዉያን የስደተኞች ማሕበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር በኖርዌ ስለሚገኘው ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮዽያዊ የሰብ አዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እና ይህ ጥገኝነት ጠያቂ በኖርዌ ምን ያህል ተቀባይነት አለው በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ9-2-2014 በሳውድ አረቢያ የተጎዱ ኢትዩጵያውያን ወገኖቻችንን ለመርዳት በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እኛ ስንሰቃይ አሜሪካ ዝም ብላ ይሆናል ፣እኛ ስንሰቃይ የአውሮፓ ሕብረት ምንም አላለ ይሆናል የኢትዩጵያ አምላክ ግን ከኛ ጋር ነው በሚል ልብ የሚንካ ነገር ተናግረዋል።
በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ10-2-2014 በኖርዌ ጥገኝነት በጠየቁ ኢትዮዽያዊ ወገኖቻቸው ላይ ስላለው የሰብ አዊ መብት አያያዝ እና ምን ያህል ጉዳያቸው እየታየ ነው የሚለውን በማንሳት ከLandinfo እና NOAS(norsk organisation for asylsøkere) ጋር በሰፊው ውይይት አርገዋል።
በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በሐገራችን ኢትዮዽያ የሰባዊ መብት ረገጣው አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ገልፀው በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንም ይህንን አንባገነን ዘረኛ የወያኔ መንግስት ለመጣል በሚደረገው ትግል ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረጉ ስለሆነ እና ወያኔም ሰላዮቹን አሰማርቶ መረጃ እየሰበሰበ ስለሆነ ቢመለስ አደጋ ይደርስበታል በማልት ገልፀዉላቸዋል።
Obang Metho Solidarity Movement for New Ethiopia (SMNE) chairman in Norway
የመላው ኢትዮዽያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴም የዘረኛው ወያኔ መንግስት ተሰደን ባለንበትም ኖርዌ ሰላዮችን እየላከ መረጃ ይሰበስባል፣ጉዳያችንም በሚገባ ስለማይታ የጤና መታወክ እየደረሰብን ነዉ ከ2 ኔጌቲቭ በላይ አላችሁ እየተባለ ተገቢው የጤና ክትትልም አይደረግልንም በማለት ቅሬታቸውን ከገለፁ በሁዋላ የኑዋስ ተወካይ የሆኑት ጆን ኡላ በኖርዌ ከኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማሕበር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ተገናኝተው በመነጋገር ጉዳዩ ለጀስትስ ሚንስትር የሚቀርብበትን መንገድ ለማመቻቸት ኮሚቴውን ሌላ ስብሰባ እንደሚጠሩ በመግለጽ ስብሰባው አጠናቀዋል።
አቶ ኦባንግም የኖርዌ ቆይታቸውን ጨርሰዉ ተመልሰዋል።
የስደተኛ ማህበሩ ኮሚቴም አቶ ኦባንግ በየጊዜው ለሕዝባቸው መብት መጠበቅ የሚያድርጉትን ትግል በማድነቅ ምስጋና እና አድናቆት ቸረዋቸዋል።
ለተጠናቀረው ሪፖርት የሺሀረግ በቀለ
ከኢትዮጲያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌ

No comments:

Post a Comment