Abe Tokchaw
ፌሰ ቡክ ምን አለበት what is in your mind? ብሎ ይጠይቃል። ፌስ ቡክዬ… in my mindማ ያለው ምኑ ተነግሮ ምኑ ዝም ይባላል፤ የትኛው ተወግቶ የትኛውስ ይቀራል… for instance last time ‘ታማኙ’ የሀገር ቤት ምንጫችን አዲስ አድማስ ጋዜጣ (ታማሚው አላልኩም አይደል… ጎሽ ተሳስቼ ከደህና ወዳጆቼ እንዳልቀያየም ብቻ!) እና ታማሚው አዲስ አድማስ ጋዜጣ፤ “ኦቦ ሌንጮ ለታ ሀገር ቤት ገቡ!” ብሎ ነግሮን አምነነው የሀገራችን መንግስት እርሳችውን ከተቀበለማ እኛስ እዚህ ሰው ሀገር ቁጭ ብለን ምን እናደርጋለን… እንንካውና ይቀበሉና ብለን ትኬት ልንቆርጥ ስንል አይደል እንዴ እርሳችው በኖርዌይ ቀዝቃዛ ኑሯቸውን እየገፉ መሆኑን ድንግት የሰማነው… (ደግሞ በሌላ እንዳትተርጉሙብኝ ለራሴ ነገር ይገንብኛል፤ ቀዘቃዛ ያልኩት የኖርዌይን ቀዝቃዛ (ቆሪ) አየር ለማለት ነው) እናላችሁ ዜናው ውሽት ሆኖ ቢገኝ ጊዜ አበስ ገበርኩ ብዬ ተደንቅሁ… ይብልጥ የሚገርመኝ ግን አዲስ አድማስ ይህንን ያክል ውሸት ከዋሸን በኋላ በቀጣይ ሳምንታት ምንም ሳይሸማቀቅ መታተሙን ከቀጠለ ነው።
እኛም ከዚህ ሁሉ በኋላ አድማስን ጋዜጣ ብለን ከገዛነው ግርምቴ አስራ አንድ ነጥብ ሁለት በመቶ ይጨምራል።
ኧረ… የእድገታችን ነገር ምን ደረሰ… የቱ እድገት…. እንዳትሉኝ ብቻ… እንድዚህማ አይባልም ወዳጄ…. የትራንስፎርሜሽን እቅዱ አካል የሆነውነ እድገት ነዋ! እንግዲያማ ሌላ ምን ተስፋ አለን… አሃ እቅዱ ሲሳካ እኮ ሀገራችን ከማንም እርዳታ የማትቀበል ሀገር የሚያደርግ ነው።
ሳስብው እንደውም ባለፍው ጊዜ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምስጠውን እርዳታ አስመልክቶ ፍትሻ አደርጋለሁ ያለች ጊዜ መንግስታቸን ብዙ ያልደነግጠው ለዛ ይመስለኛል። ግን አልደነግጠም እንዴ… ካልደነገጠ የምር መንግስታችን ታሟል ማለት ነው። አሜሪካ ግን የምር ልትጨክንብን ነው ማለት ነው… ለነገሩ እንኳን አሜሪካ አባዱላም ጨክነው “ከዚህ በኋላ ኮብራ መኪና መግዛት የለም።” ብለው ባለስልጣኖቻችንን እና መስሪያ ቤቶቻችውን አስጠንቅቀዋል። አባ ዱላ ግን ቀላል ሰው አይደሉም (ኪሏችውን አይድለም… በርግጥ በኪሎም ቢሆን አይታሙም እኔ ግን ቀላል አይደሉም ያልኩት፤ አራዳ ናቸው ለማለት ፈልጌ ነው።) አስቡት እስቲ ለራሳቸው ኮብራ መኪና አላረካ ቢላችው “እስቲ ኮብራ እባቡን ክህንድ አስመጡልኝ የፈጅውን ይፍጅ” ሲሉ እንዳልነበር ዛሬ አዳዲስ ተሿሚዎች ላይ ሲሆን የሀገር ውስጥ መኪና ካልንዳችሁ ብለው ሲቀውጡት፤ ጮካ አልሆኑም ትላላችሁ… (ጮካ ማለት በአራዳ ብሄርሰብ ቋንቋ ብልጥ ማለት ነው… የአባቴ ዘመዶች “ነሚቲ ኩኒ ጩሉሌዳ” የሚሉት አይነት ማለት ነው።
ከሁሉ የገርሙኝ ግን አቶ በርከት ስሞን ናችው። እኛ በአምስት አመት ዕቅድ ሊያጠግቡን ነው ድህነትን ሊያጠፉት ነው ብለን አምነናቸው፤ ድህነት ከመጠፋቱ በፊት ተቃቅፍን ፎቶ እየተንሳን እንጠብቃለን እርሳችው ሆዬ ሰው አይሰማ መስሏችው፤ “ኢህአዴግ ያሰብውን ለማሳካት ከአርባ እስከ አርባ አምስት አመት ይፈልጋል” ይሉናል እንዴ… ኧረ ይደብርዎት አቶ በሬ! (ሃሃ… ለካስ ደግሞ ስማችው ሲያቆላምጡት አይውደልትም!) የምር ግን አቶ በረከት ምን ሆነው ነው… ባለፈው ጊዜ የሁለት ምርጫዎች ወግ መፅህፋቸውን የጻፉ ጊዜ ኢህአዴግ በሀገሪቷ ላይ ለውጥ ለማምጣት አርባ አመት ይፍልጋል ብለውን ነበርኮ… ሌላው ቢቀር ያቺን ያሉበትን እንኳ አስልትው አንድ አራት አመት ቀንሰው ሰላሳ ስድስት አመት እንፈልጋለን ቢሉን ምን ነበረበት፤ ጭራሽ ጨምረው አርባ አምስት አመት እንፈልጋለን ይላሉ እንዴ ሆሆ… አርባ አምስት አመት ከየት ይመጣል…
ለማንኛውም… እኒያ ሰውዬ is in my mind
ምንው እንኳ እያንዳንዳችን እያዋጣን ደሞዝ እየከፈልናቸው እያንዳንዳችንን ሙልጭ አድርግው የሚዝልፉን እና የሚዘርፉን ሰውዬ፤ (ነገሩ ሲገጣጠም ደስ ብሎኝ ጨምርኩበት እንጂ ለግዜው ለዘረፋቸው ማስረጃ የለኝም። ለዘለፋው ግን እድሜ መረጃ እየቀዱ ለሚያስተላልፉ የኢህአዴግ አባላት እና ለኢሳት ቴሌቪዥን ለእያንዳንዳቸን የሚዳረስ መጠን ሰፊ የሆነ ስድብ ባለፍው ሰሞን ብዝግ ስብስባ ሲያውርዱብን ሰምተናችዋል።) የምር ግን ባለስለጣኖቻችን ቢሯችውን ዘግተው እንዴት እንደሚሰድቡን አያችሁልኝ አይደል…! እና ምን እያስብኩ ነው መሰላችሁ… እነዚህ ሰዎች በዝግ ሲሰበሰቡ ካቲካላ ነገር ይዘው ነው እንዴ… አዎና ሰው በሞቅታ ካልሆነ በቀር እንዲህ ያለ የስድብ ችሎታ ከየት ያመጣዋል…
ሰውዬው በስድባቸው መሃል የአማራ ህዝብ እስክ አሁን በባዶ እግሩ ነው የሚሄድው ሲሉም ተናግረዋል። ይህንን ንግግር ሌላ ሰው ቢናግርው ልማቱን ማየት የተሳነው ጭፍን ይባል ነበር። ራሳቸው ‘የልማት አርብኛው’ ሲናግሩት ግን ያስቃል…
በዚህ ሁሉ መሃል አንድ ነገር ይታየኛል… ቀጣዩንም ምርጫ ኢህአዴግ ቢጫውትም ባይጫወትም ከውዲሁ ተሽንፏል። ህዝቡ ውሃ ሲጠይቅ ስድብ የሚያቀርቡ ባለሰይጣኖች ምርጫ ካሸነፉ እነርሱ ኢህአዴጎች ናቸው ማለት ነው!
እና it was in my mind as well as ተቃዋሚዎቻችን… ዝግጁ ናችሁ… “ዝግጁ” ያላቸሁ… እስቲ እንያችሁ…
No comments:
Post a Comment