Translate

Friday, February 28, 2014

የዩናይትድ ስቴትስ የሰብአዊ መብት ዘገባ

በዘገባዉ መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሐሳብን የመግለፅ፥ የፕረስና የሃይማኖት ነፃነት ክፉኛ ተደፍልቋል። ኤርትራ ዉስጥም የሠብአዊ መብት ሙሉ በሙሉ መገደቡን ዘገባዉ አዉስቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በየዓመቱ እንደሚያደርገዉ ሁሉ ባለፈዉ የጎርጎሮሳዉያን ዓመት ሁለት ሺሕ አሥራ-ሰወስት በዓለም ሥለነበረዉ የሠብአዊ መብት ይዞታ ያጠናቀረዉን ዘገባ ትናንት ይፋ አድርጓል። ዘገባዉ የኢትዮዮጵያና የኤርትራን ጨምሮ የሁለት መቶ ሐገራትን የሠብአዊ መብት ይዞታ የዳሰሰ ነዉ። በዘገባዉ

Thursday, February 27, 2014

ሀይለመድህን አበራ፦ የታፈነ ብሶተኛ ወይንስ የሚያደርገውን የማያውቅ የአእምሮ በሽተኛ?

አሰፋ (ከዳላስ)

መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው

Ethiopian Airlines pilot Hailemeden Abera Tegegnየሰሞኑ ትኩስ ዜና በሆነው የረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ የሚያበረውን አውሮፕላን ጠልፎ ስዊዘርላንድ ማሳረፉን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው:: በተለይ የኢትዮጵያው አገዛዝ እና እሱን አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ለመደገፍ የሚፈልጉ ሰዎች የሚስጡዋቸው መላምቶች የሚያስገርሙና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ናቸው:: ከነዚህ አስተያየቶች መካከል ሁለቱን ልጥቀስ:: በአንድ  በኩል ሀይለመድህን የአእምሮ ችግር አለበት ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱንም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስም ያጎደፈ በማለት ለመውቀስ ይዳዳቸዋል::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና …

(ይድነቃቸው ከበደ)

ealines

“የኢትዮጵያ ሃየር መንግድ ለአፍሪካ ኩራት ነው” ሲባል ከቃላት መፈክርነት ባለፈ የአውነትም ኩራት ስለመሆኑ ጥርጣሪ  የሚያድርባቸው ዜጎች እንደሚኖሮ እገምታለው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንግድ በረዥም ታሪኩ ውስጥ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በአንፃራዊነት በተቋሙ ውስጥ ስማቸው እጅግ የገነነ ብቁ አብራሪዎች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች (ግራውንድ ቴክኒሻን) እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በአብዛኛው በኢትዮጵያዊያን የተሞላ ነው፡፡ ለዚህም ነው የአፍሪካ ኩራት ለመባል የበቃው፡፡ ይህ ኩራት እና አድናቆት ከታላቁ አፍሪካዊ የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ጀምሮ ጥቂት በማይባሉ አፍሪካዊያን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ነው፡፡

Wednesday, February 26, 2014

ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር አንቀጾች ስንቃኛቸው

ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር አንቀጾች ስንቃኛቸው
ይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ)
(yiheyisaemro@gmail.com)
መግቢያ
“እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም እርሱ የሚጸየፋቸው ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፡- ‹በንቀት የሚመለከት ዐይን፤ ሐሰት የሚናገር ምላስ፤ ንጹሖች ሰዎችን የሚገድሉ እጆች፤ ክፉ አሳብ የሚያፈልቅ አእምሮ፤ ወደ ክፋት ለመሮጥ የሚቸኩሉ እግሮች፤ በውሸት ላይ ውሸት እየጨመረ የሚናገር ምሥክር፤ በወዳጆች መካከል ጠብ የሚያነሣሣ ሰው› ናቸው፡፡” ምሳሌ 6፣ 16 – 19

በህዝባዊ ሰልፉ ለኦሰካር ሽልማት ከታጨው አደባባይ ምን እንማር

በአብራሃም ዘታዬ ከ ጀርመን
UDJ Bahirdar demonstration
ተቃውሞንም ሆነ ድጋፍን ለመግለጽ ወደ አደባባይ መውጣት የተለመደ ነገር ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ የ አዲስ አበባው መስቀል አደባባይን ብንመለከት እንኳ ያላስተናገደው ሃይማኖታዊ ፖለቲካዊ ማህበራዊ ክንውን የለም። እነዚህ ክንውኖችን በበላይነት የዘመሩባቸው የዘፈኑባቸው የቦተለኩባቸው ግለሰቦች የተለያየ በጣም የማይስማሙ ርዕዮተ አለማት አቀንቃኞች ነበሩ ናቸውም። የኮሚኒስት አስተሳሰብ የነበራቸው የቀድሞዎቹ መሪዎች ኮሎኔል መንግስቱና  መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ አንዱ አንዱን ረግመውበታል። በዝነኛው የ1997 ቱ ምርጫ ሚያዚያ 29 ኢህአዴግ በማግስቱ ሚያዚያ 30 ደግሞ ዋና ተፎካካሪ የነበረው ቅንጅት ማንነታቸውን አሳይተውበታል። አላማው ለየቅል ነበር።

ጠ/ሚ ኃ/ማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው *ኢቴቪና ፌዴራል ፖሊስም ይከሰሳሉ

 በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቅርቡ ከተላለፈው ‘‘ጅሃዳዊ ሃራካት’’ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ የወንጀልና የፍትሃብሔር ክስ ሊመሰረት ነው። ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሻገር በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሬቴድ) እና በፌዴራል ፖሊስ ተመሳሳይ ክስ ይመሰረትባቸዋል።
75f9c-64714_277529845721314_403137022_nከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናቱ እና የተጠቀሱት ተቋማት ላይ ክስ የሚመሰረተው ሰሞኑን ‘‘ጃሃዳዊ ሃራካት’’ በሚል በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ደርጅት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር ያሉትን ተጠርጣሪዎች መብት ሲጣስ መከላከል ባለመቻላቸው፣ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀማቸው፣ በሕዝብ ሐብት ያለአግባብ በመገልገላቸው፣ የተሰጣቸውን የሕዝብ አደራ ባለመወጣታቸውና በሃይማኖት ጣልቃ በመግባታቸው የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ ይመሰረትባቸዋል። ክሱን የሚመሰርቱት በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ባሉት ተጠርጣሪዎች ጠበቆች አማካኝነት ሲሆን ክሱም በሁለት ደረጃ ተከፍሎ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል።

በኢትዮጵያ የማዕድን ሙስናን ለመሸፋፈን የሚደረገው ዘበት

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
The regime in Ethiopia is seeking EITI membershipበኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በማዕድኑ ዘርፍ የሚያካሂደውን ሙስና በማደብዘዝ እና በመሸፋፈን ንጹህ መስሎ ለመታየት እና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን ለማግኘት በማሰብ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት(Extractive Industries Transparency Initiative (EITI)) ለተባለው ድርጅት ዕጩ አባል ለመሆን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ይፍጨረጨራል፡፡ የገቢ ምልከታ ተቋም/Revenue Observation Institute የቦርድ ሊቀመንበር እና የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI የቦርድ አባል የሆኑት አንቶኒ ሪቸር እንደሚሉት ከሆነ እ.ኤ.አ በ2010 ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ነበር፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ‘የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ድርጅት አዋጅ (Proclamation on Charities and Societies) የሲቪክ ህዝብ ማህበራት ቡድኖች ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነው እና በሂደቱም ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዳያደርጉ የሚከለክል ደንቃራ በመሆኑ ነው የሚል ድምዳሜ ሰጥቷል፡፡

Tuesday, February 25, 2014

እኛና “እነርሱ”! (ተመስገን ደሳለኝ)


‹‹…የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ፡፡ የባሕር መዝገቡም ተዘጋ፡፡ …ቀፋፊ ምሽት ነበር፡፡
በእያንዳንዳችንም ፊት ፈገግታ አይታይም፡፡ ከአዳራሹ ሳንርቅ ከራሳችን ጋር ብቻ እየተነጋገርን
በሃሳብም ርቀን እየሄድን አመሸን፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዳራሹ እንድንገባ ተነገረን፡፡
በፍጥነት ገብተን ቦታችንን ያዝን፡፡ ሊቀ-መናብርቱም ቦታቸውን ያዙ፡፡ ‹ዛሬ ስለወሰድነው እርምጃ
ለጦር አዛዦች ማሳወቁ ይበጃል በማለት ጠርተናቸው እዚሁ ይገኛሉ› ብለው ወደ አጃቢዎቻቸው
ፊታቸውን ዘወር አድርገው ‹አስገቧቸው!› የሚል ትዕዛዝ ሻለቃ መንግስቱ ሰጡ፡፡ ጄነራል ጃጋማ
ኬሎ፣ ጄነራል ግዛው በላይነህ፣ ጄነራል ታደሰ ገብሬ፣ ጄነራል ወርቁ መኮንን ተከታትለው ገቡ…››
ለዚህ ፅሁፍ መግቢያ ያደረኩትን ሃሳብ ጨልፌ የወሰድኩት የቀድሞ መንግስት ጠቅላይ ሚንስትር ፍቅረስላሴ ወግደረስ
በቅርቡ ‹‹እኛና አብዮቱ›› በሚል ርዕስ ካሳተመው መፅሐፍ ሲሆን፣ የተጠቀሰው ሃሳብም በተለምዶ ‹ስልሳዎቹ› ተብለው
የሚጠሩት የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ባለሥልጣናት ላይ፣ የተወሰነው የሞት ቅጣት እንዴትና በምን ሁናቴ እንደተፈፀመ
ለጦር አዛዦች ማብራሪያ መሰጠቱን አስመልክቶ ከተረከበት ገፅ 152 ላይ ነው፡፡ ይሁንና የዚህ አጀንዳ ተጠየቅ በጓድ
ፍቅረስላሴ መጽሐፍ ዙሪያ ብቻ የሚያጠነጥን አይደለም፤ ይልቁንም ሶስቱ ስርዓታት (ንጉሣዊው፣ ደርግ እና ኢህአዴግ)
በሀገር ጉዳይና በመንግስት አስተዳደር ላይ የነበራቸውን አመለካከት እና የሄዱበትን ምዕራፍ ባለሥልጣናቱ ራሳቸው
ካዘጋጇቸው መጻሕፍት አንፃር በጨረፍታ መመልከት ነው፡፡ ስለዚህም ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ‹‹ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ››
(በሁለት ቅፅ)፣ ኮሎኔል መንግስቱ ‹‹ትግላችን››፣ ፍቅረስላሴ ወግደረስ ‹‹እኛና አብዮቱ››፣ መለስ ዜናዊ ‹‹የኤርትራ ሕዝብ
ትግል ከየት ወዴት?››፣ እና በረከት ስምዖን ‹‹የሁለት ምርጫዎች ወግ›› በሚል ርዕስ ያዘጋጇቸውን መጻሕፍት
እናተኩርባቸዋለን፡፡

“ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”

ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማውያን ሕግ አጸደቀች!

musevini

የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡

የእርስ በእርስ ግጭት ነገሶበት የከረመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ


saudi ethio13


 በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ማህበር ስራ አመራር አባላት እና በቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር ደጋፊዎች መሃከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ በአባላቱ ላይ አጥልቶ የነበረው የእርስ በእስር ግጨት መቀልበሱን ምንጮች ከሪያድ አስታወቁ። ፌብረዋሪ 21 2014 ምሸት ሲጠበቅ የነበረው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለጽ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል ብለዋል፡፤

ይድረስ ለፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፡- በኢትዮጵያ ታሪክ ተወቃሾቹ የኦሮሞ ሕዝብና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ብቻ ነውን እንዴ?!

በዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን  - nikodimos.wise7@gmail.com

‹‹ዕርቅና ሰላም የሕይወት ቅመም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደውለታ ቢስ ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ የሚሆን መልስ እነሆ!›› በሚል ርእስ የጻፉትን ጦማር እጅግ የማክበርዎና ኢትዮጵያዊው የምሆን ወንድምዎ ደጋግሜ አነብበኩት፡፡ ፕሮፌሰር በትክክል ተረድቼዎት ከሆነ እርስዎ በጽሑፍዎ ለማስተላለፍ የፈለጉት ዋንኛ መልእክትዎ፣ አንድም ‹‹ዕርቅንና ሰላም መስበክ›› ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጠላት ወይም ውለታ ቢስ አድርገው ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ መልስ ይሆናል በሚል እነሆ ያሉት ጦማር እንደሆነ ነው፡፡
ፕሮፌሰር ለረጅም ዓመት ካካበቱት ዕውቀትዎ፣ በትምህርት ዓለም በሥራ፣ በምርምርና ጥናትዎ ከሕይወት ተሞክሮዎና ልምድዎ በመነሳትና እንዲሁም ዕድሜዎን ሙሉ ከመረመሯቸውና በአካዳሚያው ዓለም አንቱ ከተሰኙባቸው፣ ከበሬታን ካተረፉባቸውና ጥንታዊ የኾኑ መዛግብቶቻችንን በመመርመር እስካሁን ድረስ እያካፈሉን ስላለው ሰፊ የሆነ እውቀትዎ ከምስጋና ጋር ዝቅ ብዬ እጅ እነሳለሁ፡፡ ከገለታዬ አስከትዬ ግን በተለያዩ ድረ ገጾች ከሰሞኑን ባስነበቡን ጽሑፍዎ ማዘኔን ልገልጽልዎ እወዳለሁ፡፡

Sunday, February 23, 2014

ከ15 ሺህ ህዝብ በላይ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ በባህር-ዳር [ፎቶ]

udj-bahirdar14የተለያዩ መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች በባህር ዳር የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ በመገኘት ሰልፉን ሲጠባበቁ ነበር በአሁኑ ሰዓት ከ15 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ሰልፉን ተቀላቅሏል:: የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ሰልፉን በቀዳሚነት እየመሩ ይገኛሉ::

በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ በመቃወም ነው የባህር ዳር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገው።

የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም! (ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ/ም ( February 22, 2014 )
I. መግቢያ:
የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የወያኔ/ኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአገር-ውስጥ ጋዘጤኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በድፍረት የሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ብቻ አይደለም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ሆኖ አግኝተነዋል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እግር የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት የመንግሥት ሥልጣንን ብቻ ሣይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከበሬታ-አልባነትንም በሚመስል መልክ ነው ይህንን በጣም የተምታታ፤ በተቃርኖዎች የተሞላና በእጅጉ ኃላፊነት-የጎደለው ጋዜጣዊ-መግለጫ የሰጡት።

ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው

ክንፉ አሰፋ

Ethiopian Airlines Boeing 767-300 flight from Addis Abba to Romeአንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣  ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል።  ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር።  ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ።  ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ።  በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር።  ለሰይጣን፣ ለዚያውም በትንሽ ዋጋ ቤታቸውን ለመስጠት የወሰኑበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ “ሰይጣኑ አልወጣ እንኳን ቢል በጸበል ይለቃል። ካድሬው ገብቶ ቤቴን አልለቅም ቢለኝ ምን ላደርግ ነው?”  ነበር ያሉት ወይዘሮዋ። ከፍ ባለ ገንዘብ ለኢህአዴጉ ሰርቪስ ቤታቸውን ቢያከራዩት ኖሮ ባጭር ጊዜ ዋናውን ቤታቸውን ለቀው የመውጣት ክፉ እድል ይገጥማቸው ነበር።

የመከላከያ ተቋም ተግባር አገርን መጠበቅ ነዉ ወይስ አገርን መዝረፍ?


የአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።

Friday, February 21, 2014

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን (አቤ ቶኪቻው)

አቶ አልምነው“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን

አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተስማ፤በኬኒያ የስደት “ኬዝ” ጋገራ
እኒያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።
“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ውጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።
እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤

Thursday, February 20, 2014

ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ?

“ኢህአዴግ የተጭበረበረ ሪፖርት አቅርቦ” ነበር

world bank foto


ኢህአዴግ “አልመረመርም፣ አልበረበርም” በማለት ሲያንገራግር ከቆየ በኋላ በዓለም ባንክ ቀጭን ትዕዛዝ ለመበርበር መስማማቱን ገልጾ በተለያዩ አካላት ምርመራ ተካሂዶበታል። በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ አካል የሆነው የመጨረሻ ምርመራ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተጠናቋል። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች እንደተናገሩት ስድስት አባላትን ያካተተው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ኢህአዴግን መርምሮ ተመልሷል። የሚጠበቀው የመጨረሻው ሪፖርትና ሪፖርቱ የሚቀርብለት የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ነው። በቅርቡ የሚወጣውን ውሳኔ አቅጣጫ ለማስቀየር በማሰብ ኢህአዴግ ለመርማሪው ቡድን ራሱ የፈጠረውን “የተጭበረበረ ሪፖርት” አቅርቦ ነበር፡፡

የሌላቸው ባለቤቶች (ከበድሉ ዋቅጅራ ሳላስፈቅድ የተዋስሁት)

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

have and notበድሉ ዋቅጅራ ‹የሌላቸው ባለቤቶች› የሚል ቅራኔ ውስጥ የገባው ከተጨባጭ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁኔታ ተነሥቶ ነው፤ አንዳንዴ ሁኔታዎች እያስገደዱን ቅራኔዎችን እንቀበላለን፤ አንድ ጌታ አሽከራቸውን ይጠሩና ባላገር ወደሚኖሩ እናታቸው ዘንድ ይልኩታል፤ ነገር ግን ‹ሞተው ከሆነ እንዳትነግረኝ› ብለው አስጠንቅቀውት ይሄዳል፤ ሴትዮዋ ሞተው ይደርሳል፤ ምን እንደሚያደርግ ግራ ገባው፤ ሲያንሰላስል ብዙ ቀናት ከቆየ በኋላ ጎፈሬውን ለሁለት ከፍሎ ግማሹን ይላጭና ግማሹን ብን አድርጎ ያበጥርና ጌታው ዘንድ ይቀርባል፤ አንዴ ጎፈሬውን እየነካካ፣ አንዴ የተላጨውን እየዳበሰ ጥያቄዎቻቸውን ሲመልስ፣ ጌታው ተቆጡና ‹ምንድን ነው የምታድበሰብሰው አርፈው እንደሁ በወጉ አትነግረኝም!› ብለው ሲጮሁበት ‹አዬ ጌታዬ አርስዎ መቼ በወጉ ላኩኝና!› ብሎ መለሰላቸው።

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ!

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ!

foto saudi
ከተመሰረተ 20 አመታትን እንዳስቆጠረ የሚነገርለት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የተፈጠረው ቅራኔ መልኩን ለውጦ መቀጠሉን የሚናገሩት ምንጮች በቀደሞው የኮሚኒቲው ሊቀመንበር እና በማህበሩ ስራ አመራር መሃከል በተነሳው አለመግባባት የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 21 /2014 ምሸት ስራ አመራሩ በጠራው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አሰቃቂ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል፡፤

“ከአሜሪካ በላይ ራሳችን ተጽዕኖ መፍጠር አለብን” ታማኝ በየነ

“ከአሜሪካ በላይ ራሳችን ተጽዕኖ መፍጠር አለብን” ታማኝ በየነ

ፋክት መጽሄት
Artist Tamagne Beyene's interview with fact magazine የዚህ ዕትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም ጊዜያት በኪነ-ጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ፣ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኢሕአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተ-መንግስት ከተቆጣጠረበት ዕለት (ግንቦት 20/1983 ዓ.ም) ጀምሮ በድፍረት የስርዓቱን አምባገነንነት፣ ከፋፋይነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይ ያለውን ቸልተኝነት… ጠቅሶ ተችቷል።

የኢትዮጵያ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች መደፈር? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም
Mr. Asrat Tasse Ethiopian political party UDJ officialበኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል የይስሙላ የፍትህ ስርዓት (ባሜርካኖች አባባል የካንጋሩ ወይም ባማርኛ የዝንጀሮ የፍርድ ስርዓት) መስርቷል እያልኩ ሁልጊዜ ስጮህ የቆየሁበትን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ማስረጃ የሚሆን ድርጊት በመፈጸሙ እያዘንኩም ቢሆን በመጠኑ ፈገግታ ሰጥቶኛል፡፡ የኢትዮጵያ “ፍርድ ” ቤቶች “በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ/Tigrian Peoples Liberation Front” የፖለቲካ ባላባቶችና ጌቶች የሚዘወሩ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ናቸው፣ በዚህም መሰረት ለዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የህግ የበላይነት የለም እያልኩ ስናገር ቆያቻለሁ:: ባለፈው ሳምንት “ፍርድ ቤትን ዘልፈዋል ደፍረዋል” በሚል ሰበብ የአንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ የቀድሞው ዋና ጸሐፊ የነበሩትን አቶ አስራት ጣሴን ወደ ዘብጥያ ማውረድ በአገሪቱ ባሉ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች በተደጋጋሚ የሚፈጸሙትን የስህተት ኮሜዲዎች (የቀልድ ትእይንቶች) እና የፍትህ ስርዓቱን ሽባ መሆን በተጨባጭ የሚያመላክት ትኩስ ማስረጃ ነው፡፡

Wednesday, February 19, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ ረዳት ካፕቴን መጠለፍ የአገራችንን የአመራር ችግሮችና የሃሣብ ድህነት ክፉኛ አጋልጧል!

በክፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory

የካቲት 17 በጥዋት የጠለፋውን ዜና እንደስማሁ፡ የቅድምያ ተግባሬ ያደረግሁት ለማዘጋጀው ድህረ ገጽ መረጃዎችን ማሰባስብና መረጃዎቹን መመዘን ነበር። ለዚህም ስል: ያሰባስብኩት መረጃ ምን ያህል ለእውነተኝው ሁኒታ ቅርበት አለው የሚለውን በመመዘን ጥቂት ጊዜ አሳለፍሁ።Ethiopian Airlines was absorbed by the TPLF mafia
አንዳንዶቹ ለጊዜው ትክክል ባይሆኑም፡ እንዳለ ማቅረቡ ምክንያታዊ እስከሆኑ ድረስ: ዛሬ ያለውን የመረጃ ጥማት ማርካት ብቻ ስይሆን፡ ለወደፊትም አንድ ሁኔታ በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እንዴት ተዘገበ ለሚለው በምስክርነት ሊረዳ ይችላል።
በወቅቱ በአንድ ጊዜ፡ በተከታታይ በገጼ ላይ እንዳቀረብኩት ሁሉ፡ ብዙ የውጭ ምንጮችን ቃኝሁኝ። ጠቃሚ መረጃዎችንም አገኝሁኝ። በዚያን ወቅት አንድ ነገር ያላድረግሁት ነገር፡ መረጃ ከኢትዮጵያ ለማግኝት መሞከር ነበር። አንደኛ መረጃ ቢኖራቸውም፡ ቀዳሚው መንፈሳቸው የሚቀናው መረጃውን ማፈን ነው!

Tuesday, February 18, 2014

የረዳት አብራሪው እህት መልዕክት በግምገማ አይን…

Abe Tokchaw

የረዳት አብራሪው እህት መልዕክት በግምገማ አይን…
397281_138042889641890_1097458037_nየረዳት አብራሪው እህት በፌስ ቡኳ በኩል እንድ መልዕክት አስቀምጣ አግኝተናል። ይህንኑ መልእክት እንደሚከተለው በገምገማ አይን እናየዋለን!
በመጀመሪያ ይህን ጽሁፍ የምታነቡ ሰዎች በሙሉ የተዝረከረከ ከሆነባችሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ከትናንት ከሰዐት በኋላ ጀምሮ እስካሁን ኢንተርኔትና ቴለቪዥን ላይ ያለማቋረጥ ተተክየ ስለቆየሁና በጥልቅ ሃዘን ስለተመታሁ አይምሮየ ትክክል ላይሆን ይችላል።
(አይዞሽ እታለም ችግርሽ ችግራችን ነውና እስቲ አውጊን እባክሽ….)
‘የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ሮም ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን ጠልፎ ጄነቫ ላይ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ እጁን ለስዊዝ ስጠ። ምክንያቱም ስዊዘርላንድ ውስጥ ጥገኝነት ለመጠየቅ ነው ብሏል።’ የሚለውን ዜና በርካታ የዜና ማሰራጫዎች ከየፊናቸው አስተያየት ጋር አቅርበውታል። የዜና ማሰራጫዎች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ ወገኖች ያሻቸውን ብለዋል። የፖለቲካ ድርጅቶች የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና እንደ አቤ ቶኪቻው ያሉ ቀልደኞች የየራሳቸውን ሃሳብ ለማስተላለፍ ተጠቅመውበታል። በጣም አሳዝኝ ነገር ነው። ሁሉም የየራሱን እምነት ለማስተላለፍ እንጂ እሱስ ምን ሆኖ ይሆን ብሎ አለማሰቡ ልብ ይሰብራል።

የአውሮፕላን ጠለፋውና የህወሃት አመራሮች ስብሰባ


የኢህአዴግ አመራሮች ለአስቸኳይ ጉዳይ ቤተመንግስት ተጠርተዋል:: ሊቀመንበሩን የስብሰባውን አጀንዳ መናገር ጀመሩ::
              ፎቶ ፋይል
እንደምታውቁት መጪው 2007 የምርጫ ጊዜ ነው:: እና ጠላቶቻችን ከአሁኑ ምርጫው ; ፓርቲው እና አገሪትዋ ላይ አደጋ ለማድረስ እየሞከሩ ነው:: ለዛ ምሳሌ የሚሆነው እና ዛሬ የተሰበብንበት ምክንያት ትላንት የተጨናገፈው የአውሮፕላን ጠለፋ ነው:: ፓርቲያችን እንደ ትላንት አይነቱ ጸረ-ልማት የሆነ ተመሳሳይ ተግባር እንዳይፈጸም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት:: ለዚህም አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይጠበቅብናል:: በእዚህ አጀንዳ ላይ ያላችሁን አስተያየት ስጡና እንወያይበት::
አንዱ አመራር እጁን አወጣ:: እንዲናገርም ተፈቀደለት::
ሁሉም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ፌዴራል ፖሊስ መመደብ አለበት:: ለሚኒባስ ታክሲ አንድ ;ለአውቶቡስ ሁለት ከፊት እና ከኋላ ይመደብ:: ምንም እንኳን ኢኮኖሚ ው የሚጎዳ ቢሆንም መጪው ምርጫ ላይ ፈጽሞ አደጋ እንዲጋለጥ መፍቀድ የለብንም::>> እሱ ተናግሮ እንዳበቃ ሌላኛው እጁን አወጣ::

ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ

ለተፈጥሮ ሃብት የጠየቀው ዓለምዓቀፋዊ እውቅና ውድቅ ሆነ

eiti
ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር።

Monday, February 17, 2014

የተጠለፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን

ዛሬ ጠዋት ጄኔቫ - ዚውዘርላንድ ላይ ለማረፍ የተገደደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠላፊ ራሱ የአይሮፕላኑ ረዳት አብራሪው መሆኑ ተረጋግጧል። በርካታ መንገደኞችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ጄኔቫ አየር ማረፊያ ሲራርፍ በመንገደኞቹ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

Genf Flugzeug Entführung Ethiopian Airlines 17.02.2014
ከአዲስ አበባ ወደ ሮም በጉዞ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን እንደታቀደው ሮም ሳይሆን ዛሬ ጠዋት በስዊዘርላንድ የጄኔቫ የአየር ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን ነው የሲውዘርላንድ ፖሊስ የገለፀው።

የኢትዮጵያ አውሮፕላን በገዛ ረዳቱ ጠለፋ ተደረገበት… ለምን… ?

Abe Tokchaw

5265540-3x2-940x627የኢትዮጵያ አውሮፕላን በገዛ ረዳቱ ጠለፋ ተደረገበት… ለምን…  ?
ዛሬ ወደ ሮም ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መጠለፉን ሰማን። ማነው እንዲህ የደፈረን ብለን አቶ ሬደዋንን ብንሰማቸው ጊዜ “አውሮፕላኑ ሱዳን ላይ አርፎ ነበር ምናልባት ጠላፊዎቹ ያኔ ይሆናል የገቡት” ብለው ተናገሩ።  ኋላ ላይ ሲጣራ ግን ጠላፊው የአውሮፕላን አብራሪው ረዳት  መሆኑ ተሰማ፤  ረዳቱ ጠለፋውን የፈፀመው ዋናው አብራሪ በአውሮፕላኑ መፀዳጄ ቤት ጎራ ባለበት ሰዓት ነው።
ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ…
መላ ምት አንድ፤
ዋና አውሮፕላን አብራሪው ፓይለት በሰላም እየበረረ ሳለ መንገድ ላይ የመፀዳዳት አምሮቱ መጣበት እና ረዳቱን፤ “በሰማይ የሰጠውህን በሰማይ እቀበልሃለሁ” በሚል፤ አደራ በሎት መፀዳጃ ቤት ወገቡን ሊፈትሽ ገባ። ይሄን ጊዜ ረዳቱ ሆዬ “ይሄ ሰውዬ ከመፀዳጃ ቤቱ ሲመለስ ሮም አድርሶ ከዛምም ወደ ፍትህ አልባዋ ሀገሬ ከሚመልሰኝ አሁን መሪውን እንደጨበጠኩ የራሴን እድል በራሴ ለምን አልወስንም” አለ እና … መሪውን አለቅም አለ። ሰዊስ ጄኔቭ ላይም ጥገኝነት ትሰጡኝ እንደሆን ስጡኝ ብሎ አሳረፈው።

'' ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈን የማንሰጥ ለመሆናችን ዋስትና እና ጥገኝነት እንዲሰጠን እንፈልጋለን'' የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠለፋ ጉዳይ (latest)

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው የተጠለፈው አይሮፕላን 

-ከ አዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 702 ጄኔቭ ላይ ዛሬ የካቲት 10/2006 ዓም በማዕከላዊ የአውሮፓ ሰዓት ከማለዳው 12 ከ 02 ሲሆን  እንዲያርፍ ተገዷል።

Sunday, February 16, 2014

ተዋርዶ መገዛት ይብቃን!

ተዋርዶ መገዛት ይብቃን!

የወያኔ ሹማምንትና አደርባይ ሎሌዎቻቸው አንገቱን አስደፍተው የሚገዙትንና የሚዘርፉትን ህዝብ ይበልጥ ስብእናውን አዋርደው ሊገዙት ለምን እንደሚፈልጉ የማይገባን ጥቂቶች አይደለንም። እነዚህን ግፈኞች ቀረብ ብሎ ላያቸው ግን ይህ ድርጊታቸው እንቆቅልሽ አይደለም።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝብ አይሰማንም ብለው በር ዘግተው ከሚያካሂዷቸው ጉባኤዎች እያፈተለኩ የሚወጡ የቪዲዮና የድምጽ መረጃዎች የነዚህን ግፈኞች ስነ ህሊና ግልጽ አድርገው ያሳያሉ።
ከወራት በፊት የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሀገር ሽማግሌ ሰብስቦ የወያኔ አላማ ከእሱ ጎሳ ጋር ተባብሮ ሌላውን ብሄረሰብ የበታች አድርጎ መግዛት መሆኑን ሲናገር የሚያሳይ ቪዲዮ ተመልክተን ነበር። የክልሉን ህዝብ የሚጨፈጭፈው ለዚህ ሲባል መሆኑን ለማሳመን ነበር በሩን ዘግቶ የተናገረው።
ሰሞኑን ደግሞ አንድ የአማራ ክልል የወያኔ ሹምና ሎሌ አንደ እንደሶማሌ ሹም ካድሬዎቹን ሰብስቦ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቀ፤ ለ እግራቸው ጫማ የላቸውም በሚላቸው የአማራው ተወላጅ ላይ ለሰሚ በሚሰቀጥጥ ቋንቋ ያወርደው የነበረ ስድብ የሚነግረን ተጨማሪ ነገር ተመሳሳይ የወያኔን ምንነትን ነው።

ወያኔን ካላጠፋነዉ ዘረኝነቱና ዉርደቱ ይቀጥላል

ወያኔን ካላጠፋነዉ ዘረኝነቱና ዉርደቱ ይቀጥላል

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በራሳቸዉ እጅ የጻፉት ማኒፌስቶ በግልጽ እንደሚያሳየን እነዚህ ዘረኞች ጫካ ገብተዉ የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ያነሳሳቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸዉ ጥላቻና መሰረተ ቢስ ቂም በቀል ነዉ። ይህ ጥላቻቸዉ ደግሞ አማራዉን በመግደልና ግዛቱን ሲያሻቸዉ ከራሳቸዉ ክልል ጋር በመቀላቀል አለዚያም ለጎረቤት አገሮች በመሸለም ብቻ ሊቆም ወይም ሊገታ አልቻለም። እነሆ የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።
ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማዳከም፣ ለዘመናት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያገለግለኛል ብሎ ዘመቻ ከከፈተባቸው ብሄረሰቦች አንዱና ዋንኛው የሆነው የአማራ ህዝብ በራሱ ማንነት እንዲያፍርና ብሄራዊ ኩራቱ እንዲሟሽሽ ላለፉት 23 አመታት በግብር ከፋዩ ህዝባችን ገንዘብ በሚተዳደሩ የመንግሥት መገናኛዎች ሳይቀር ከፍተኛ የስነ ልቦና ዘመቻ ተካሂዶበታል። በአማራ ሥም አማራውን የወያኔ አገር የማፍረስ አጀንዳ አስፈጻሚ ለማድረግ የተሾሙበት ተላላኪዎች በህወሃት አለቆቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም በተለያዩ አጋጣሚዎች አማራውን የሚያዋርድና የሚዘልፍ አስተያየት በአደባባይ ሲሰጡ ሰምተናል አይተናል። ይህ ተግባራቸው ለአማራ ህዝብ ቅንጣት ታህል ክብርና ፍቅር ያልነበረው ዘረኛው አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከዚህች አለም በሞት ከተሰናበተ ቦኋላም ተጠናክሮ ቀጥሎአል።

የሰማያዊ ፓርቲ “ወጣቱና ፖለቲካ” በሚል ርዕስ ውይይት አካሄደ

ወጣቱ ጸሀፊና ፖለቲከኛ አስራት አብርሃ በዋና ተናጋሪነት የተገኘበት “ወጣቱና ፖለቲካ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ውይይት ቅዳሜ የካቲት 8 ቀን 2006 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተካሄደ።

የመኖሪያ ፈቃድ – ከራስ ወዳድነት ያልራቀው የስደተኞች የመጨረሻ ግብ

በሳዑዲ ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ዜጎች የእንድረስ ምክክር በኦስሎ

oslo 9
ከራሳቸው አልፎ ባህር ውስጥ ቢደፉት የማይጎድል ሃብት አላቸው። ከሃብታቸው ብዛት የተነሳ ተጨማሪ የነዳጅ ክምችት አግኝተው ጉድጓድ ለመቆፈር ተቃውሞ በመነሳቱ ሪፈረደም አካሂደዋል። ከነዳጅ ይልቅ ውሃ ውስጥ ያለው ህይወት አንደሚብስባቸው በማስታወቅ ድምጽ የሰጡ በመብዛታቸው ነዳጁ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል። ይህ ዜና በተሰማበት ሰሞን ያልተገረመ አልነበረም። ሃብት ካለ ምን ችግር አለ? አንግዲህ እንደዚህ “ብር ይብቃን፤ አሳና የባህር ውስጥ ፍጡራን እንቁራሪትን ጨምሮ ይበልጡብናል” የተባለባት አገር ኖርዌይ ናት።