Translate

Wednesday, March 9, 2016

የሕወሓት ካድሬዎች በኮንዶሚኒየም ቤቶች ላይ የሚያደርጉት ሕገወጥ ተግባር በቆጠራ ተደረሰበት::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አሥር ዓመታት የገነባቸውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ በጀመረው ቆጠራ፣ በሕወሓት ካድሬዎች  በርካታ ሕገወጥ ተግባራት የተፈጸሙባቸው ቤቶች መኖራቸው ታወቀ፡፡

የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው ቆጠራ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን፣ ይቆጠራሉ ከተባሉት 104,258 ቤቶች ውስጥ 35 ሺሕ ያህሉ ተቆጥረዋል፡፡ በዚህ መሠረት በሕወሓት ካድሬዎች   ተሰብረው የተከራዩ፣ ፈርሰው ተቀላቅለው የተሠሩ፣ በግለሰቦች የተያዙ በርካታ ቤቶች መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም ትዳር እየፈረሰና ፍቺ እየተፈጸመ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
በትዳር ውስጥ እየኖሩ ነገር ግን ከሁለት በላይ ቤቶች ይዘው የተገኙ ፍቺ እስከመፈጸም የደረሱ ክስተቶች መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ከዚህ በላይ ተገቢው ክፍያ ያልተፈጸመባቸው ቤቶችን መያዝና ሕጋዊ መረጃ የሌላቸው ቤቶችም መገኘታቸው ተመልክቷል፡፡
ለባንክ ተገቢውን ክፍያ በወቅቱ ያልፈጸሙ፣ በሕገወጥ ድርጊት ከያዙት ቤት የኮበለሉና በሕገወጥ ድርጊታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉ መኖራቸውም ታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘጠኝ ዙሮች ለተጠቃሚዎች ያስተላለፈውን 104,258 ቤቶች ቆጠራ ጀምሯል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተጀመረው ቆጠራ ብዙ ቤቶች በተገነቡባቸው ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌ፣ የካ፣ አቃቂና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍላተ ከተሞች ነው፡፡
በቆጠራው 2,500 ባለሙያዎች፣ ፖሊስ፣ ደንብ ማስከበርና የንግድ ቢሮ ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡
ቆጠራውን በሚመለከት የአዲስ አበባ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝና የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ መስፍን መንግሥቴ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ አስተዳደሩ በእነዚህ ቤቶች ሕገወጥ ተግባራት እየተፈጸመ መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት እንደደረሰው ገልጸው ነበር፡፡
አስተዳደሩ ለልማት ተነሺዎች 8,400 ባለአንድ ክፍልና ስቱዲዮ ቤቶችን አዘጋጅቶ ነበር፡፡ ነገር ግን የልማት ተነሺዎች ፍላጐት ባለሁለት ክፍልና ባለሦስት ክፍል በመሆኑ፣ በርካታ ቤቶች ጥቅም ላይ ሳይውሉ ተዘግተው ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለተጠቃሚዎች ቢቀርቡም ውል ስላልተፈጸመባቸው ርክክብ ያልተፈጸመባቸው 4,137 ቤቶች ይገኛሉ፡፡ በዚህ ሒደት በሕወሓት ካድሬዎች  ደላሎች፣ የጥበቃ ሠራተኞችና ሌሎች አካላት አብዛኛዎቹን ቤቶች በመስበርና በመቀላቀል ለግል ጥቅም ማዋላቸው ተነግሯል፡፡
ቆጠራው ትኩረት የሚያደርገው መኖሪያ ቤቶች፣ ንግድ ቤቶችና የጋራ መጠቀሚያዎች ላይ ነው፡፡ በእነዚህ ግንባታዎች ላይ ሕገወጥ ድርጊት ተፈጽሞ ከተገኘ፣ ሕግ የማስከበር ሥራ እንደሚሠራ አቶ መስፍን በወቅቱ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቆጠራ የሚጠበቀው ከተጠቃሚዎች የሚገኘው መረጃ ከአስተዳደሩ መረጃ ጋር ተመሳክሮ ዕርምጃ እንደሚወስድ ነው፡፡ ቆጠራው ከዚህ በተጨማሪ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ማስተካከያ ማድረግ እንደሚያስችል  ይድነቃቸው ተናግረዋል፡፡
እስካሁን በተደረገው ቆጠራ 42 በመቶ ቤቶች እንደተሸፈኑ፣ 1,339 ቤቶች ባዶ ሆነው መገኘታቸውንና በሕገወጥ ሥራ ተሰማርተው ከተገኙት መሀል 60 ያህሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment