በኮንሶ ለወራት በዘለቀው የነዋሪዎቹና የልዩ ኃይል ፍጥጫ ምክንያት ትምህርት ቤቶች እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ ዝግ ሆነዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኮንሶ ወረዳ እና የአካባቢው ባለስልጣናት ለግምገማ ተጠርተው ወደ ክልሉ መቀመጫ ሀዋሳ ቅዳሜ መጋቢት 3 ሄደዋል። የሰሞኑ የኮንሶ ውጥረት የተቀሰቀሰው የአካባቢው ባህላዊ መሪ የሆኑት ካላ ገዛኸኝ ወልደዳዊት መታሰርን ተከትሎ ነው። ካላ ገዛኸኝ በታሰሩበት አርባ ምንጭ በኮንሶ ሰዎች እና በወንድማቸው መጎብኘታቸውን ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
No comments:
Post a Comment