ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ዲቃላውን ብኣዴንን እየወነጀለ ነው::
ሰሜን ጎንደር ውጥረቱ ከሯል::
ሰሜን ጎንደር ውጥረቱ ከሯል::
የሕወሓት የገደል ማሚቱዎች በጋራ እና በፍቅር የኖረን ሕዝብ በመለያየት ለማናከስ ያደረጉት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ መክሸፉን ካረጋገጡ በኋላ ብኣዴን የሚሉትን ድርጅት ማእከሉን አፍርሰው ዳግም ለመስራት ማቀዳቸው ታውቋል::ሕወሓቶች ብኣዴንን አፍርሰው ለመስራት ያቀዱት በአሁን ሰአት የያዙትን የግዛት ማስፋፋት እያደናቀፈብን ያለው ብኣዴን ነው ከሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው መሆኑ ታውቋል::ብኣዴን የቀድሞ አጼዎችን ስርኣት ዳግም ለመመለስ የሚለው የሕወሓት ኋላ ቀር እና ራስን ከሞቱ ስርኣቶች ጋር የማወዳደር ሱስ በያዝነው የሰለጠነ 21ኛው ክፍለዘመን ላይ አገርሽቶበታል::

ሕወሓት በዘር ጥላቻ የተሞሉ ካድሬዎቹን ቅርሻት ሲተፋ ያላወቀው ነገር ቢኖር የሕወሓትን የመስፋፋት ፖሊሲ ያማረረው የጠላው ሕዝቡ እንጂ ብኣዴን አለመሆኑን ነው::አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የብኣዴን አመራሮችን ማርኛ ተናጋሪ በሆኑ የሕወሓት ካድሬዎች ለመተካት እና ካሰበው የመስፋፋት እቅድ ለመድረስ ብኣዴንን መወንጀሉ ሊያስደንቅ አይገባም ሲሉ የብኣዴን ሰዎች ይናገራሉ::የሕወሓት የግዛት የመስፋፋት እና ታላቋን ትግራይ የመፍጠር ሕልም እየተደናቀፈ ሲሆን የትግራይ ሕዝብ በራሱ የሕወሓትን አካሄድ እንደማይደግፈው ከአረና ፓርቲ አከባቢ የሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ::ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው የጎሳ ፖለቲካ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ጋርጦበታል::እንዲሁም በተጨማሪ የሕወሓትን አካሄድ ከከተማ እስከ ገጠር ያለው ሕዝብ ስለነቃበት ተቃውሞውን እያሰማበት ይገኛል::
#ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment