Translate

Friday, March 18, 2016

የእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ለአቶ ሃለማሪያም ደሳለኝ በድጋሜ የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ

የእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ለአቶ ሃለማሪያም ደሳለኝ በድጋሜ የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ
ላለፉት ሁለት አመታት ያህል በእስር ላይ እየማቀቁ እንደሚገኙ የሚታመነው ከግንቦት 7 መሰራቾች አንዱ እና ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሁኔታ ያሰጋቸው የታላቋ ብሪታኒያ ጠ/ሚ/ር ዲቪድ ካሜሮን ለኢትዮጵያው አቻቸው ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለሁለተኛ ጊዘ ደብዳቤ መጻፋቸውን ( ቡዝ ፌድ ነውስ) የተባለው ድህረገጽ ከእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ያገኘውን መረጃ ትነተርሰሶ በተላንተናው እለት( ሃሙስ መጋቤት 17 2016) እትሙ ዘግቧል።
አንደ ዜና ዘገባው እምነት ከሆነ ምንም እንኳን የደብዳቤው ይዘት እና መቺ እንደተጻፈ ባይጠቀስም “ከሎንዶን ደጎስ ያለ የእርዳታ ገንዘብ (በአመት 350 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ) የሚፈሰላት አዲስ አበባ ከወዳጅ አገር ለቀረበላት (አንዳርጋቸው ባስቸኳይ ይፈቱ ጥያቄ) ብዙም ፈቀቅ ያለ እንቅሰቃሴ (አውንታዊ ምላሽ)አላሳየችም” ተብሏል። ከዚህ አኳያ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው፡ የሰሜናዊ ሎንዶን ነዋሪ የነበሩት፡ የሶስት ልጆች አባት እና ባለትዳሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ሰነእ ላይ ታግተው ወደ አትዮጵያው ማጎርያ ቤት ከተወረውሩ ጀምሮ ለተደጋጋሚ ጊዜያት ደብዳቤዎችን ቢላላኩም ባለው ሁኔታ ላይ ለውጥ በለመገኘቱ የአንግሊዝ ባለሰላጣናት በእጅጉ መበሳጨታቸውን ዘገባው የወጪ ጉዳይ ባለሰልጣናትን ጠቅሶ አሰፍሯል።
በመቀጠልም አቶ አንዳርጋቸው ከዱባይ ወደ ኤርትራ ሲጓዙ የመን ሰነኣ ላይ ባለፈው የፈረንጆቹ ሰኔ 2014 የታሰሩት “ በኢትዮጵያ መንግስት የታገደ ድርጀት በመራራታቸው እና የአገዛዙን የነቀዘ ሙስና በማጋለጣቸው ነው “ የሚሉ ተቆርቋሪ ወገኖች መኖራቸውን የጠቀሰው ዜና ዘገባው የአዲስ አበባ ገዚዎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ያቀረቧቸው ውንጀላዎች በእንግሊዝ የወጪ ጉ/ሚ/ር ባለሰልጣናት ዘንድ ጥርጣሪዎችን ማሳደሩን በውስጥ ዶሴያቸው (ሚሞስ) ገልጸዋል ብሏል። “አቶ አንዳርጋቸው ለጌዜው በጠበቆቻቸው፡ በካውንስለሮች ፣በቤተሰቦቻቸው ፣ በሃይማኖት አባቶች እና በመሳሰሉት እንዲጎበኙ የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች በተደጋጋሚ ጊዜያት ቢገልጽም አገዛዙ ቃሉን ባለመጠበቁ በአጅጉ እዝነናል “ይላል ባለፈው ሃምሌ የ እንግሊዝ የው/ጪ/ጉ/ሚ/ር መስሪያ ቤት የወጣው ማስታወሻ። የእንግሊዝ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ዙሪያ ከ 20 ጊዜያት በላይ ደብዳቤዎችን ቢልክም ለወዳጅ አገር ለ ኢትዮጵያ የቀረበው ተማጽኖው ምንም ውጤት ባለ ማሰገኘቱ ሁኔታውን የመብት ተሟጋቾች “ ጉንጭ አልፋ ጥረት” ሲሉ ተሳልቀውበታል። ዲቪድ ካመሮን ከዚህ ቀደም ከአቶ አንዳርጋቸው ልጆች የተላከላቸውን የተማጸኖ ደብዳቤ ተመርኩዘው የኢሃዲግ መንግስት አባታቸውን (አቶ አንዳርጋቸውን) እንዲፈታላቸው የሚያሳዘን ደብዳቤ “እንደ አባትነታቸው “ መላካቸው አይዘነጋም።
የኣንግሊዙ ጠ/ሚ/ር ደኢቪድ ካሜሮን በቅርቡ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዚህ ጉብኝታቸው ላይ በጸጥታ፡ በጸር ሽብር ዘመቻ በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ ከመወያየታቸው ለጥቆ በሰበዊ መብት አያያዝ በዲሞክራሲ ስር አት ግንባታዎች ላይ በሚነሱት አጀንዳዎች ላይ የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይም ሊነሳ እንደሚችል በርካት የመብት ተሟጋቾች ግምታቸውን ከወዲሁ በመሰንዘር ላይ የገኛሉ።

No comments:

Post a Comment