Translate

Friday, July 12, 2013

ዜና በጨዋታ፤ ድራማው ይብቃ… (ህዝበ ሙስሊሙ) ምን ሰርቼ ልብላ (አርቲስቱ መንግስት)

600540_589521871099173_1142193440_nዜና በጨዋታ፤ ድራማው ይብቃ… (ህዝበ ሙስሊሙ) ምን ሰርቼ ልብላ (“አርቲስቱ” መንግስት)
ዛሬ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በመላው ሀገሪቷ ታላቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ በተቃውሞው በይበልጥ ጎልቶ ከወጡ መፈክሮች መካከል “ድራማው ይብቃ!” የሚል ይገኝበታል… ድራማው… ድራማው… የቱ ድራማ… ሰው ለሰው…? ብለው የጠየቁ እንደሆነ መልሱ አዲስ መስመር ላይ ይገኛል…
መንግስታችን በአርቲስቶች ሽልማት ዘርፍ “የምንግዜም ኮመዲያን” በሚል ሽልማት ሊያገኝ ይገባል… ሲሉ አስተያየታቸውን የሚሰጡ ብዙሃን ናቸው፡፡ እንደ ብዙሃኑ ገለፃ ከሆነ፤ (ደግሞም መሆኑ አይቀርም) “መንግስት በተለያየ ጊዜ ህዝቡን በሳቅ እየገደለው ይገኛልና የሚደርስበት ኮመዲያን አልተገኘም” ስለዚህም ሽልማት ሲያንሰው ነው፡፡ ይህንን ሲያብራሩ የነበሩ ብዙሃን አሁን ደግሞ እያረሩ መንግስት በትራጄዲውም መስክ የሚደርስበት አልተገኘም እና “ኮመዲዮትራጀዲ” ተብሎ ይሸለም እያሉ እየተናገሩ ነው፡፡
ነገሩ ሲብራራ የሚከተለውን መልክ ይይዛል…

ከዚህ በፊት በከተማው ውስጥ ቦንብ እያፈነዳ ኦነግ አፈነዳ ሲል እንደነበር በዛ ሰሞን የተነቃበት መንግስታችን፤ አሁንም በዛው የስራ ልምድ የተለያዩ የፍንዳታ አቅርቦቶችን በተለያዩ ስሞች እቀረበልን ይገኛል፡፡ ይሄው በዚህ ሰሞን  አንድ ምስኪን ሼክ ገድሎ አሸባሪዎች ገደሏቸው ብሏል አሉ፡፡ (እንግዲህ እኔ ከሰማሁ መደበቅ አይሆንልኝም… መንግስታችን አቅም ሳያጣ ካልደገፍነው እያላችሁ አበሳ የምታዩ ሰዎች… ተናግሬ ሳልጨርስ ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ስድቦች አቅርቦት ለማድረግ አትቸኩሉማ… በአነስተኛ እና ጥቃቅን አመራር የተመራነው አንሶ፣ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ጥቅማ ጥቅም የምንታሰረው እና የምንገደለው አንሶ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ስድብ የምንሰደብበት ምክንያት የለም… እንዴ አናሳዝናቹም እንዴ…(ባይሆን ከፍ ከፍ ያለ ስድብ ፈልጉልን እንጂ….))
እና አካባቢው በሙሉ እንደሚያወራው ሼህ ኑሩ ይማም የተገደሉት በመንግስት ድራማ ነው፡፡  ልክ በሰው ለሰው ድራማ ላይ “ይገደሉ… ይገደሉ…” ተብለው እንደሚገደሉት አይነት፡፡ ልዩነቱ በሰው ለሰው ድራማ የሚገደል ሰው በሌላ ድራማ ላይ ይታያል፡፡ በመንግስታችን ድራማ የሚገደል ግን ዳግም አይታይም፡፡
እናም ዛሬ ህዝበ ሙስሊሙ በተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች “ድምፃችን ይሰማ… ድናራማው ይበቃ” ሲል ድምጹን አሰምቷል፡፡ መንግስትም በሆዱ፤ “ድራማው ይብቃ የሚሉኝ ምን ሰርቼ ልበላ ነው” ብሎ ያጉረመረመ ሲሆን፤ …ድምፃችን ይሰማ ሲሉ ሰምቶ ግን ለሌላ ድራማ አርቲስት አውቶብሶችን በብዛት ወደ አንዋር መስጂድ አሰማርቶ ነበር፡፡ ነገር ግን አውቶብሶቹ ድራማውን የሚያሳትፋቸው አጥተው ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡
ይህንን ዘገባ ሚዛናዊ ለማድረግ ደም ግፊት እና ልብ ድካም ከሌለብዎ ኢቲቪን ይመልከቱ

No comments:

Post a Comment