ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የወያኔ አገዛዝ የፈረደበትን የሦስት አመት የእስር ጊዜ (ያለ አመክሮ) ሙሉ ለሙሉ ጨርሶ የሚፈታበት ቀን ዛሬ ቢሆንም የዝዋይ እስርቤት ተመስገንን ሊፈታ ፍቃደኛ አለመሆኑን በእስርቤቱ ተገኝቶ የተመስገንን መፈታት ሲጠባበቅ የነበረው ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገልጿል።
“ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይፈታም” የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎችታሪኩ ደሳለኝመንግስት የፈረደውን (ፍርድ ቤት) ሙሉ የ3 አመት እስር ያለ አመክሮ ዛሬ የጨረሰው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእራሳቸው ፍርድ አሰጣጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዛሬ መፈታት ሲኖርበት የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አንፈታም ብለዋል። ይህ ሁኔታ ቀድሞም የተመስገን እስር ፖለቲካዊ እንደነበር ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው።ትላንት ጥቅምት 2/2010 ዓ.ም ተሜን ጠይቄው ስወጣ እግረ መንገዴን እስረኛ አስተዳደር ገብቼ እስሩን ስለሚጨርስ ሰው ላናግራችሁ ነበር ስል አንዱ ሰው “ላጣራልህ” ብሎ ሲነሳ “ስሙን ልንገርህ” ስለው “አቃለሁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይደል” ብሎኝ ወጣ አይ ያውቀዋል፣ ያቁኝል ማለት ነው ብዬ አጣርቶ እስኪመጣ ጠበኩት። ይህ ሰው የስራ ሀላፊነቱን የማላውቀው ጌጡ የተባለ ሰው ነው። እንደመጣ እያየኝ ተመስገን ነገ ነው የሚፈታው አለኝ ሰምቼው ወጣሁ። ለነገሩ ባይለኝም ቢለኝም የተፈረደበትን ሙሉ 3 አመት የሚጨርሰው ነገ ጥቅምት ሦስት ነው።ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንግስት በፍርድ ቤቱ የወሰነበትን እስር ቢጨርስም አሁን ደግሞ የእስር ቤቱን ሌላ እስር ጀምሯል።እንግዲህ የተመስገን ህይወት በተመለከተ የዝዋይ እስር ቤት አስተዳደሮች ሀለፊነቱን ይወስዳሉ። ተመስገን ላይ የሚደርሰው ነገር ሁሉ ያሳስበናል።ዝዋይ እስር ቤት
ጥቅምት 3/2010
ማህሌት ፋንታሁን (የዞን ዘጠኝ ጦማሪ) በበኩሏ ከተመስገን ጋር ባደረገቸውን ቆይታ ተመስገን የተናገረውን እንዲህ በማለት ገልጻዋለች።
“ፍርድ ቤት በእስር እንድቆይ በማረሚያ ቤቱ በአደራ ያስቀመጠኝ እስከ ዛሬ ድረስ ነው። ፍርድ ቤት ዛሬ እንደፈታሁ ነው የሚያቀው። የፍርድ ቤት ትእዛዝ መከበር ነበረበት ከዚህ በኋላ የሚደርስብኝን ነገር ምን እንደምሆንም አላቅም። አንድ እስረኛ አመክሮ የሚከለከለው ከሌሎች እስረኞች ጋር ሲጣላ እና ህግ ሲጥስ ነው። እኔ አመክሮ የተከለከልኩት ያለምንም ምክንያት ነው። አመክሮ መከልከሌን እንኳን የነገረኝ አካል የለም። በወቅቱ ሳልፈታ ስቀር ነው አመክሮ መከልከሌን ያወቅኩት። ”ጋዜጠኛ ተመስገን ዛሬ እንደማይፈታ ሲነገረው በግራ መጋባት መንፈስ ውስጥ ሆኖ የተናገረው ነው። ተሜ ይህን ሲነግረን እስረኛ መጠየቂያ ቦታ ከነበሩት 3 ፖሊሶች በተጨማሪ በ5 ፖሊሶች ታጅቦ ነበር የመጣው።
No comments:
Post a Comment