Translate

Monday, October 9, 2017

አልተገናኝቶም (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ
UNREST
ኦህዴድ ብአዴንን ይበልጠዋል የሚለው “ዩኒቨርሳል ትሩዝ” አይነት በመሆኑ ማዎዳደሩ ተገቢ አይመስለኝም። አንድ ቢሉ ምንም እንኩዋን ሁለቱም አሽከርነታቸው ለትግራዩ ገዥ ጉጅሌ ቢሆንም ኦህዴድ ተቦክቶ የተሰራው ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከኦሮሞ ልጆች ሲሆን ብአዴን ግን አፈጣጠሩ ከጨነገፈው የኢህአፓ ሽል ሲሆን ቀስ ብሎ ኢህአዴን ተብሎ በኢትዮጵያዊ ማንነት ለመምጣት ሞከረና ድህረ ደርግ የዘር ፖለቲካ የበላይነት ሲያገኝ የሚገባበት ቢያጣ አማራ ነኝ ብሎ ባህር ዳር ውስጥ ሄዶ ተወሸቀ። ለዚህም ነው በብአዴን ዋናዎቹ የቀድሞ አመራር ውስጥ አማራ የሆነ ሰው ፈልጎ ማግኘት ችግር የሚሆነው። አዲሱ ለገሰ የሚዛን ተፈሪ ኦሮሞ ነው። ተፈራ ዋልዋ ከጊሚራ ብሄረሰብ ነው። ህላዌ ዮሴፍ ትግሬ ነው። በረከት ኤርትራዊ ነው። አያሌ ጎበዜ ትግሬ ነው። መለስ ጥላሁን ትግሬ እያለ ሲቀጥል የዛሬዎቹ ተተኪዎች እነ ካሳ ተክለ ብርሃን እነ አለምነው መኮንን እንዲሁ ነፍሳቸው ከየት እንደተጋገረ እና እንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ ምን ያህል እንደሚጠሉት ግልጽ ሲሆን ደመቀ መኮንንም ህወሃት አድርግ ያለውን ለማድረግ የቆረበ የከሚሴ ኦሮሞ መሆኑን ወዘተ ማየት ነው። ስለዚህ የብሄር ፖለቲካን በመርህ ደረጃ ተቀብለው ሳለ በማይወለዱበት ይልቁንም በጣም በሚጠሉት ህዝብ ላይ የተሾሙ ጋንግሪኖች በየትኛው ሰብእናቸው እንደ አንድ ኦህዴድ ለኦሮሞ የሚቆረቆረውን ያህል እነሱ ለአማራውሊቆረቆሩ ይችላሉ?

ይልቁንም ኦህዴድ በአንድ በኩል ጀርባውን ለወያኔ ኮርቻነት አመቻችቶ በሌላ በኩል የኦነግን ፕሮግራም መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ ተግባራዊ ያደረገ ነው። ዛሬ ኦሮሚያ የምትባል አገር መሬት ላይ ሙሉ ለሙሉ ባትወርድም ከኦሮሚያ ነኝ የሚል፣ አፉን በላቲን የፈታ፣ ኢትዮጵያን በተሰባበረ መስተዋት የሚያይና የዜግነት ጽንሱ በውስጡ የጨነገፈበት አንድ ሙሉ ጀነሬሽን ፈጥሯል።ይህን እውነት መካድ አይቻልም።እርጉሙ ሰውየ “ኦህዴድ ሁሉ እንደፈጣን ሎተሪ ቢፋቅ ኦነግ ነው …” እያለ ሲናገር የነበረው በውጥ ያስጣጠቃቸውን አጀንዳ ስለሚያውቀው ነበር::
ቁምነገሩ ይህ ኦህዴድ የሄደበት የዘር ፖለቲካ በሂደት ለኦሮሞ ህዝብ ምን ያህል አዋጭ ነው የሚለው ነው አደጋው:: የአገሪቱን ጅዲፒ ጨምሮ ሁሉም ነገር አዲስ አበባ በሆነበት፣ እነ ወለጋና ምእራብ ሃረርጌ አዲስ አበባን ባልሆኑበት; ከአገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ እትብታቸውን በጥሰው በቁቤ ፊደል እየጻፉ በፍጥነት እየተለዋወጠ ካለው አለም ጋር ምን ያህል እኩል መራመድ ይችላሉ? ዛሬ የዚህን የዘር ፖለቲካ እንደ ሰማያዊት እየሩሳሌም የመጨረሻ ግብ አድርገው እንዳልተቀበሉ ሄደው ሄደው ፖለቲካው ከወያኔ ጋር አብሮ ሲከስም በዚህ የኦሮሞ ትውልድ ላይ የሚፈጠረው ቀውስ ምን መልክ እንደሚኖረው እርግጠኛውን አስልቶ የሚናገረው ማነው ?
ሲጠቃለል ወያኔ በቅርቡ ወደ ደደቢት ሲመለስ የኦሮሚያን ጽንስ ተጥዶ የሚጠብቀው ምን ያህል የጋለ ብረት ምጣድ እንደሆነ አሁን በምስራቅ ሃረጌና በባሌ ድንበር መካከል ጭምር እየሆነ ያለውን ማየቱ ብቻ በቂ ነው….

No comments:

Post a Comment