ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?
ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል!
በሐዋሳ ለጊዜው የጉዳቱ መጠን ያልታወቀ የእሣት ቃጠሎ መድረሱን በአደጋው ያዘኑ ገለጹ፡፡ ከስፍራው እንደተሰማው ለሰኞአጥቢያ የተነሳው ቃጠሎ ምናልባትም በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛው ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አደጋው ሲደርስ የእሣት አደጋ “አገልግሎት” በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ አስነስቷል፡፡
ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት ላይ ነፍሳት ባረፉበት ወቅት የደረሰው የእሣት አደጋ መነሻው በትክክል ባይታወቅም ማምለጥ የሚቻልበት ባለመሆኑ አሟሟቱ የከፋ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተለያዩ ወገኖች በምስል ይፋ ያደረጉት ቃጠሎ እንደሚመለክተው የእሣቱ መጠን በቀላሉ የሚቆጣጠሩትና አደጋውን የሚቀንሱበት እንዳልነበረ ያስረዳል፡፡
በሐዋሳ ታሪክ ከፍተኛ ነው የተባለው ይህ ቃጠሎ በህይወት ላይ ያደረሰው አደጋ በትክክለኛው ቁጥሩ ባይገለጽም ከሥፍራውየደረሰን አጭር መልዕክት እንደሚያስረዳው ከሰባት የማያንሱ መሞታቸውን ከ23 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቃጠሎ ደርሶባቸው የተጎዱ እንዳሉ፤ ሌሊት የተነሳ ቃጠሎ በመሆኑ መረጃ ለመሰብሰብ ቢያስቸግርም ደረሰ የተባለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ ከዚህ የበለጠና ምናልባትም ኅሊናን የሚጎዳ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
በዚሁ በደረሰን አጭር መልዕክት እሣቱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የከተማዋ የእሣት አደጋ ብርጌድ “እውን ሐዋሳ የእሣት አደጋ ብርጌድ አላት?” የሚያሰኝ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ለመባሉ ምክንያቱ በዝርዝር አልተገለጸም፡፡ ምናልባትም አደጋው ሌሊት ላይ መከሰቱ በሰው ህይወት ላይ የተመዘገበውን አኻዝ ከሚገመተው በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የዝግጅት ክፍላችን በደረሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት የተሰማውን ልባዊ ሐዘን በዚህ አጋጣሚ ይገልጻል፡፡
No comments:
Post a Comment