የህብር ሬዲዮ ህዳር 28 ቀን 2007 ፕሮግራም !
<... በሁሉም ሕጋዊ መንገድ ሄደናል የተጠየቀው ተራ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ነው ። ስርዓቱ በዚህ ትልቅ ፍርሃት ገብቶታል የጭካኔ እርምጃውን ስናየይ ይሄ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል አለመፈለግ ነው። ይሄ ከተጠናከረ በእርግጠኝነት ይሄ ሕዝብ ስርዓቱን ለመቀየር ይችላል... ኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ ብዙዎቹ አመራሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል።አቤልን ራሱን እስኪስት ነው በብረት ዱላ የመቱት አሁን የዲሞክራሲ ጥያቄ ሳይሆን መጀመሪያ ነጻነት ጥያቄ ነው። ሕዝቡ ከጎናችን ይሁን ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን...>
ወጣት ዮናታን ተስፋዬ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ በመስቀል አደባባይ የተጠራውን ተቃውሞ ለማክሸፍ በአገዛዙ በኩል የተወሰደውን የሀይል ጥቃት እና ቀጣዩን ትግል የታሰሩ ያሉ አመራሮችን እና ሌሎቹ ተቃዋሚዎችን እና ተያያዥ ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<<..መተንፈስ አልቻልኩም...>> የኒዮርክ ነዋሪ የሆነው በፖሊስ የሀይል ድርጊት ሕይወቱ ያለፈው ኤሪክ ጉዳይና በአሜሪካ የተጋረጠው ቀለምን መሰረት ያደረገ የሕግ አስከባሪዎች እርምጃ የት ላይ ይቆማል? (ልዩ ዝግጅት)
የሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ የትብብሩ አመራሮች የወሰዱት እርምጃና ለሕጋዊው መብታቸው የተወሰደባቸው ሕገ ወጥ እርምጃ ስርዓቱን ወዴት ይወስደዋል? እኛስ ምን ማድረግ አለብን? ተቃዋሚዎች ለምን አንድ ላይ አይሆኑም ? የቴዲ አፍሮ ከአገር እንዳይወጣ መታገድ የት ድረስ ይዘልቃል ? ቴዲን ለቃሊቲ እያጩት ወይስ ገፍትረው ሊያስወጡት?(ውይይት ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቹና የሕግ ባለሙያው ተክለሚካኤል አበበ ጋር (ሙሉውን ያዳምጡት)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የፈረንሳይ ባንክ የሕወሃትን አገዛዝ የአንድ ቢሊዮን ዶላር የሶቨርኒ ቦንድን አላሻሽጥም አለ
ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያን የተሳፈሩባት ጀልባ የመን ባህር ዳርቻ ሰጠመች
የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር ትግሉ ይቀጥላል ሲል መግለጫ አወጣ
አሜሪካ በኢትዮጵያ ያሉ ዜጎቿን ለደህነታቸው ሲሉ እንዲጠነቀቁ አሳሰበች
ዋና ዋና አመራሩ የታሰሩበት ሰማያዊ ፓርቲ ትግሉ ወደሁዋላ ሳይል እንዲቀጥል ጥሪ አስተላለፈ
የታሰሩት መሪዎች ጨለማ ቤት ናቸው ሕክምና ተከልክለዋል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊጀምር ያሰበውን አዲስ የጃፓን በረራ በኢቦላ ስጋት ሳቢያ አቋረጠ
ቶኒ ብሌዬር ከህወሃት አገዛዝ ጋር የሚያደርጉት ቁርኝት ትችት ገጠመው
የትብብሩ ዋና ጸሐፊ ከእስር ቤት ትግሉ እንዲቀጥልና ከጉዞዋችን ወደ ሁዋላ አንልም ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ
<<...እኛ እንጸናለን እናንተም በርቱ...>> የሰማያዊ ፓርቲ የስትራቴጂ ሀላፊ ከእስር ቤት
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
No comments:
Post a Comment