Translate

Saturday, December 6, 2014

ኢንጂነር ይልቃል እና 300 ሰዎች በፖሊስ ተደብድበው ታሰሩ (ልዩ ዘገባ)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ 9 ፓርቲዎች የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መነሻ – ከዛሬ እስከ ነገ ድረስ የሚቆይ የ24 ሰአት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ላለፉት ሳምንታት አብረው ሲሰሩ ቆይቷል:: ሆኖም ገና ከመነሻው የአዲስ አበባ አስተዳደር ለሰልፉ ፈቃድ በመከልከል ህገ መንግስታዊ መብታቸው የገፈፈ መሆኑን ፓርቲዊቹ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል:: ሌላው ቀርቶ ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩት አባላት እና የፓርቲ አመራሮች፣ ጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ታስረው ነበር፡፡
አሁን ከሰማያዊ ፓርቲ በደረሰን መረጃ መሰረት የፓርቲው አመራሮች ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትና አቤል ኤፍሬም በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል፡፡ ሴቶቹን ጨምሮ በርካቶች እስር ቤት ከገቡ በኋላ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ አቤል ኤፍሬምን ጨምሮ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸውና ራሳቸውን ስተው የነበሩት አመራሮችና አባላት እስከነ ጉዳታቸው ፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የታሰረው የፓርቲው መሪ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
በሌላ በኩል የሰማያዊ ፓርቲ ጥበቃ የሆኑት ቀኖ አባጆቤ ቢሮ ውለው ወደ ቤታቸው በሚሄዱበት ወቅት በደህንነት ታፍነው ታስረዋል፡፡ አቶ ቀኖ የ70 አመት ሽማግሌ ናቸው፡፡ ከዚህም ባሻገር የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ አጠገብ ሱቅ ያላትና በተደጋጋሚ ለፓርቲው አባላት ምንም ነገር አትሽጭ እየተባለች ማስፈራሪያ ይደረስባት የነበረች ነጋዴ፣ ከፓርቲው ቢሮ ጎረቤት የሚኖር ወጣትና ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ከፓርቲዎቹ አመራሮች ጋር መታሰራቸው ታውቋል፡፡
ከትላንት ጀምሮ ደግሞ – የአዳር ሰልፉን የጠሩት የ9ኙ ፓርቲዎች ቢሮ በፌደራል ፖሊስ ተከቦ ነበር፡፡ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብሩ አባል የሆነው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቸርቺል የሚገኘው ጽ/ቤት በፌደራል ፖሊስ ተከቧል፡፡ ከሰማያዊ ጽ/ቤት መውጣትም ሆነ መግባት የማይቻል ሲሆን በርካታ አመራርና አባላት ታፍነው ታስረዋል፡፡
የትብብሩ አመራሮች ስልክ እንዳይሰራ እየተደረገ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ስልክ እንዳይሰራ ተደርጓል፡፡
አመራሮችና አባላቱ ፖሊስ ከ200 ሜትር ርቀት ውጭ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ጽ/ቤት መጠጋት እንደማይችል ቢከራከሩም ፖሊሶቹ ‹‹መመሪያ ተሰጥቶናል፤ አንሄድም!›› ማለታቸው ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ከፖሊስ ጋር ሲከራከሩ የአካባቢው ህዝብ በመውጣቱ ፖሊሶቹ ፓርቲው ጽ/ቤት እንደራቁ ታውቋል፡፡
ዛሬ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅቱ የቀጠለ ቢሆንም – ሰልፉ በሚነሳበት የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በኩል ወደ መገናኛ እና 22 የሚያሳልፈው መንገድ ተዘግቷል፡፡ ከመስቀል አበባይ፣ ፒያሳ፣ አራት ኪሎ በካሳንቺስ አድርጎ የሰማያዊ ፓርቲ የሚገኝበት እንደራሴ በኩል ወደ 22 እና መገናኛ የሚያስኬደው መንገድ ተዘግቷል፡፡ ሆኖም ሰልፉን ከተዘጉ መንገዶች ውጭ 10 የሚሆኑ የመነሻ ቦታዎች የተዘጋጁ ሲሆን የሰልፉ አስተባባሪዎች ከጽ/ቤቱ በሚተላለፍላቸው መመሪያዎች መሰረት ወደቦታው በመሄድ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡
blue4
አሁን ደግሞ መስቀል አደባባይ አካባቢ የሚገኘውን ህዝብ እየበተኑ ነው፡፡ በአካባቢው ሰው እንዳያልፍ እየተደረገ ነው፡፡ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች እየተዘጉ ነው፡፡
መስቀል አደባባይ በፌዴራል ፖሊስ ተጨናንቋል
በሌላ በኩል ከሰማያዊ ጽ/ቤት ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ ሊያቀና በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የት እንዳሉ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ከ300 በላይ አመራሮችና አባላት እንደታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡
letter
EMF

No comments:

Post a Comment