ለጋሾች ይሰጣሉ ተብሎ የነበረው 7.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አልተገኘም

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሪግራም (UNDP) የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከተለያዩ ለጋሾች 7.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማሰባሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ድጋፍ እንዳላገኘ ተወካዩ ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በተለይ በምርጫ ወቅት በጀቱን ያሳውቅ የነበር ቢሆንም የዘንድሮውን አመት በጀት ይፋ እንዳላደረገ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከለጋሽ አገራትና ድርጅቶች ይሰበሰባል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ገንዘብ ባለመሰብሰቡ እንደሆነ ተገምቷል፡፡
የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሪግራም (UNDP) ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገንዘብ የሚያሰባስብባቸው እና ከአሁን ቀደም ምርጫ የታዘቡ አካላት በዘንድሮው ምርጫ በታዛቢነት እንደማይቀርቡ መገለጹ ይታወሳል፡፡
No comments:
Post a Comment