የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ጉዞው ያፈራቸው ጄነራል መኮንኖች ከወታደራዊ አመራር ሳይንስ ትምህርት እና ስልጠና አንፃር ሲመዘኑ
መግቢያ
የኢትዮጵያ ሠራዊት በዘመናዊ መልክ ከተቋቋመበት ከ1927 ጀምሮ እስክ 1983 ዓ/ም ድረስ ጊዜው በሚጠይቀው ወታደራዊ ሳይንስ የተማሩ፣ ዘመናዊ ክህሎትንና ሥነ ምግባርን የተላበሰ እና በተግባር የተፈተነ የምድር ጦር፣ የባህር ኃይልና የአየር ሃይል ሠራዊትና ጀገና መሪዎችን ለማፍራት የቻለ ነበር:: በሥራው ዓለምም ሠራዊቱን ፈታኝ በሆኑ የተለያዬ አውደ ፍልሚያዎች መርተው ለድል ያበቁ ከፈተኛ ወታደራዊ ምሁራንና ጄነራል መኮንኖች እንደነበሩ የሚታዎስ ነው:: የማእረግ አሰጣጡም እንዳሁኑ ዘርን መሰረት በማድረግ ሳይሆን የትምህርት ዝግጅትን፣ ወታደራዊ ዲስፕሊንና ሥነምግባርን እንዲሁም በእየእርከኑ ያሳየው ብቃትና ተገቢውን የመቆያ ጊዜ መፈፀሙ ተረጋግጦ ይህንን እንዲያስፈፅም በተዋቀረ ገለልተኛ አካል አቅራቢነት በሀገሪቱ መሪዎች ሹመት ሲሰጥ ኖርዋል።
ቀደም ሲል በተገለፀው የማዕረግ እድገት አሰጣጥ ሂደት መሠረት በአጠቃላይ ከ1927 እስክ 1983 ሀገሪቱ 293 ጄነራል መኮንኖች አፍረታ ነበር።በሌላ መለኩ ወያኔ የመንገሥት ሥልጣን ከወሰደበት ከ1983 ጀምሮ ዘርንና ታማኝነትን ብቻ መሠረት በማደረግ ለ130 የቀድሞ ሽምቅ ተዋጊ መሪዎቹ ከብርጋዲየር እስከ ሙሉ ጀነራልነት ማረግ አድሎአቸዋል።
ከትምህርት ዝግጅት አንፃር 95 በመቶ (123ቱ) የሚሆኑት መደበኛ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀትና ከህሎት የሌላቸው ሲሆን ቀሪዎቹ አምስት በመቶ የሚሆኑት ተገቢውን የወታደራዊ ሳይንስ የተማሩና በቂ ሙያዊ ክህሎትን ያዳበሩ ሰባት የቀድሞ ጦር አባላት ብቻ ነበሩ(አሁን ሁለቱ ብቻ በማገልገል ላይ ሲሆኑ አራት በጡረታ ሲገለሉ አንዱ በፖለቲካ ጉዳይ የተባረሩ ናቸው)። በአጠቃላይ ከነዚህ 130 ጄነራል ውስጥ 66ቱ የህውሓት አባላት የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። የዚህ ፅሁፍ አጠቃላይ ዓላማ ባለፉት 23 ዓመታት የህውሓት/ኢህአዲግ መንግሥት ያፈራቸውን ጀነራል መኮንኖች ከወታደራዊ ሳይንስና ሙያዊ ክህሎት አንፃር መፈተሽና መገምገም ነው። በዚህም መሰረት ይህን መግቢያ(Introduction) ጨምሮ 1ኛ፡ የወታደርዊ አመራር ምንነት እና ዋና ዋና የጦር አመራር እርከኖች ፤ 2ኛ፡የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችና ወደ ወታደራዊ የትምህርት አካዳሚዎች የመግቢያ መስፈርቶች፤ 3ኛ፡ የመኮኑኖች የማዕረግ እድገት፤ 4ኛ፡የጀነራል
መኮኑኖች የማዕረግ እድገት፤ 5ኛ፡የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ትምህርትና የሥልጠና ሂደት 6ኛ፡ አሁን ያለው የጦር ሓይል መኮንኖች የአመራር ሥልጠናና ብቃት፤ 7ኛ ማጠቃለያ ሲሆኑ ከዚህ እንደሚከተለው በቅደም ተከተል ይቀርባሉ።

ሙሉውን በፒዲፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
No comments:
Post a Comment