በኤምባሲዎች የደህንነት አታቼዎች(ተወካዬች) እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት መካከል ስብሰባ እየተካሄደ ነው።
ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው
በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ ምእራባውያን ዲፕሎማቶች ዘንድ የሚደርሱ እናፈነዳለን መረጃዎች ከፍተኛ የሆነ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኙ እና ለደህንነት አታቼዎች ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎች እንደሚናገሩት መሃል አገርን እና ምስራቅ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪት ክልሎች ይደረጋሉ የተባሉ ፍንዳታዎች ከአልሸባብ የመጡ ማስጠንቀቂያዎች ናቸው ቢባልም በአልሸባብ ውስጥ በተደረገ የመረጃ ማጣራት አልሸባብ ይህንን መረጃ እንዳልበተነ በአዲስ አበባ የአሜሪካን የደህንነት አታቼ ለማረጋገጥ ያደረጉት ሙከራ በከፊል ባይሳካም የሁኔታውን አሳሳቢነት አስመልክቶ በምእራባውያን የኤምባሲ ዲፕሎማቶች የደህንነት አታቼዎች እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል።
No comments:
Post a Comment