አባይ ሚዲያ፡ ዛሬ ከደቡብ ሱዳን በደረሰን መልእክት የደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን ልትረዳ ነው መባሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን ዘጋቢያችን ከሱዳን አስታውቆል።
የአባይ ሚዲያ ዘጋቢ ከጁባ እንዳስተላለፈው የደቡብ ሱዳን መንግስት በላፈው 6 ወር ውስጥ የቀድሞውን የጋምቤላ ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ ኦኬሎን ለተቃዋሚዎች ይሰራል በሚል ተላልፎ ለኢትዮጵያ መንግስት መሰጠቱን በማስታወስ፤ በአሁኑ ሰአት ምንም አይነት የፖሊሲ ለውጥ እንደሌለ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደተረዳ ለማረጋገጥ ችሎል።
በተለይም በደቡብ ሱዳን መንግስትና ተቃዋሚዎች መካከል እየከረረ የመጣውን ጠብ ወደ ማስፈራሪያ በመለወጥ የኢትዮጵያ መንግስት የደቡብ ሱዳን አማጺያንን ይረዳል በሚል መረጃ ይህን ለማስፈራራት የወጣ ዜና ካልሆነ በስተቀር የደቡብ ሱዳን መንግስት ምንም አይነት የለወጠው ነገር አለመኖሩን ከስፍራው ሪፖርቱን ልኮልናል።
የጋምቤላ ህዝቦች ወታደራዊ ንቅናቄ የሆኑትን ደውለን ያነጋገርናቸው ሲሆን ጉዳዩን እንደማያውቁና ምንም አይነት የፖሊሲ ለውጥ ይመጣል ብልን በደቡብ ሱዳን መንግስት እንደማይጠብቁ አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች እና የደህንነት አባላት ደቡብ ሱዳን ጁባ በብዛት እንደሚገኙም ጠቁመዋል። አያይዘውም ጉዳዩ የእራስን የፖለቲካ ችግር ወደ ፕሮፖጋንዳ በመለወጥ የተደረገ እንጂ እውነት የደቡብ ሱዳን መንግስት ይህን ያደርጋል የሚል እምነት የለኝም እና ዜናው የተሳሳተ ይመስለኛል። ይህ የሚደረግ ቢሆን መጀመሪያ እኛ ጋር ዜናው ይደርስ ነበር ሲሉ የዜናውን ይዘት አጣጥለዋል።
No comments:
Post a Comment