የህወሓት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ፣ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ህወሓት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በተያያዘም “ጉባኤ ይጠራ” በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን … በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።
ethiopianreview.com
No comments:
Post a Comment