ከዘመናት በፊት ለስብህናው ዋጋ የሚሰጠው፣ በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍ የሰው እጅ አይቶና ለምኖ ማደርን የማይፈቅደው የሃገሬ ሰው፣ ለእምነቱና ለክብሩ ሟች የነበረው ወገኔ ይኸው በዚህ ዘመን በሃገሩ በልቶ የመኖር ዋስትና አጥቶ፣ ድርሻውን በጥቂት ዘረኞች ተነጥቆ ኑሮው የምድር ሲኦል ሆኖበት ክብሩን አዋርዶና ነውር ትቶ ነብሱን ለማቆየት ይህንን የመሰለ ዘግናኝ የለት ከለት ኑሮ ይገፋል በመሃል አዲስ አበባ፡፡ ስለልማት፣ ስለተሰራው መንገድ፣ ባለጊዜዎች ስለገነቡት ህንፃ የምናወራ ጉደኞች፣ እድገት ምናምን እያልን የምናዜም አንድ ትውልድ ያመከንን ከንቱዎች፣ ወገኖቻችን በእንደዚህ አይነት የሰቀቀን ህይወት ውስጥ እያይን ከራሳችን ባለፈ ማሰብ ተስኖን እንደቀትር እባብ ከደሃው ቀምተን ባገኘነው ሃብት የምንንፈላሰስ ከንቱዎች ጥሩም ሆነ መጥፎ መንግሰታት ያልፋሉ ሃገርና ሕዝብ ግን ህያው ናችው፡፡ ያኔ ምን ይውጣችሁ ይሆን . . . . . . . .
ከ100.000 በላይ ኢትዮጵያውያን በመደበኛነት ከቆሻሻ ገንዳ የተደፉ ምግቦችን በመሰብሰብ ይመገባሉ::ይህ የሚያሳየው ሃገራችንን የሚያስተዳድረው የወያኔ ጁንታ 11% እድገት አለ እያለ ቢሆንም ዉሸት መሆኑን ነው ::ወያኔ እየደረሰበት እያለው ኪሳራ መውድቂያው በመሆኑ ህዝቡን ለከፋ ችግር ዳርጎታል::
No comments:
Post a Comment