Translate

Saturday, March 30, 2013

የአማረ ገመና ሲገለጥ!(ክፍል-1)


የአማረ ገመና ሲገለጥ!(ክፍል-1)

(ከኢየሩሳሌም አ.)
አዲስ አበባ አየር ማረፊያ፣ ነሃሴ 13 ቀን 1997ዓ.ም ፣ ምሽት 2 ሰዓት…ለእረፍት መጥቶ የነበረ ጓደኛዬን ለመሸኘት በስፍራው ተገኝቻለሁ። ..እንዳጋጣሚ በቅርብ ርቀት የ<ሪፖርተር> ጋዜጣ ባለቤት አማረ አረጋዊን አየሁት፤ ወደርሱ አምርቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ < ወደ አሜሪካ ለእረፍት የላከውን ልጁን ለመቀበል እንደተገኘ > ገለፀልኝ። …ከዛም ወደ ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት በመግባት ወሬ ቀጥልን፤ በመሃከሉ አማረ ፥ « ..ሲሳይና እስክንድር የጋዜጠኝነት ካባቸውን አውልቀው ለምን በግልፅ ፖለቲከኛ አይሆኑም? » ሲል በሹፈት አይነት ጠየቀኝ። « ምን ማለት ነው?» ስል መልሼ ጠየቅኩት፤ ..« በግልፅ የሚፅፉትን አታይም እንዴ?..የቅንጅት ዋና አቀንቃኞች ሆነዋል እኮ..» ካለ በኋላ አያያዘና « ..ይህችን አገር ልደቱና ሃይሉ ሻውል እንዲመሯት ነው የሚፈልጉት?…ልደቱ ነው አገር ለመምራት የሚቀመጠው?..» ሲል ያቺ የማውቃት የአማረ ፌዝና ሹፈት ፈገግታ በስሱ እያሳየኝ፤ …በዛ ሰሞን አማረ <አቋሙን> ይፋ አውጥቶ በቅንጅትና በጋዜጦች በተለይም በኢትኦጵና ምኒልክ ጋዜጦች ላይ በየሳምንቱ ..ለገዢው ፓርቲ የወገነ የቃላት ጦርነት የገጠመበት ወቅት ነበር።

አዳምጬው ሳበቃ እንዲህ አልኩት፥ « አማረ በምርጫው ማግስት ምን ብለህ ነበር የፃፍከው?..የሽግግር መንግስት ይቋቋም..ብለህ አልነበር?.. አሁን አቋምህን ለምን እንደቀየርክ አውቃለሁ!..» ስለው አይኑን በልጥጦ፥ « ምንድነው የምታውቀው?» አለኝ።.. < አዜብ መስፍን በቢቲ ማስታወቂያ ባለቤት ፀጋዬ በኩል አስጠርታህ ሌላ አራተኛ ሰው ጭምር ባለበት ምንድነው የተነጋገራችሁት?..አዜብ ከባለቤቷ የተላከ መልክት ነገረችህ፤ እንዲህ ስትል፥ « ሁሉም ጋዜጦችና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠራርገው እስር ቤት ይገባሉ። አንተም መግባት ትፈልጋለህ ወይ?..በማለት መለስ ንገሪው ብሎኛል፤» ብላ ነግራሃለች። ከዛም አቋምህን ቀየርክ፤ » አልኩት።…ግንባሩን አጨማዶ ገላመጠኝ። ..አያያዝኩና፥ « ደግሞስ አገሪቷን ማን ይምራ ነው የምትለው?..ሕዝብ የመረጠው ማንም ይሁን ማን…ድምፁ መከበር አለበት። አንተ ግን ካለ ሕወሐት/መለስ ሌላ ሊመራ አይችልም ..እያልክ ነው..» አላስጨረሰኝም..ጥሎኝ ሄደ። በወቅቱ ጉዳዩን በኢትኦጵ ጋዜጣ ላይ ፃፍኩት..
አማረ፥ ከማስታወቂያ ሚ/ር ለምን፣ እንዴትና በማን ተባረረ?…« ሪፖርተር » ጋዜጣ በመለስ ዜናዊ <ልዩ> ትእዛዝ እንደተቋቋመ ያውቃሉ?..አሁን የቲቪ ስርጭት እንዴትና በማን ትእዛዝ ሊጀምር ቻለ?…ከነደብረፂዮን ጀርባ በምስጢር የሚሰጠው ድጋፍና ለፓርቲው የሚያደርገው ስውር ተጋድሎ….በሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እመለስበታለሁ።

No comments:

Post a Comment