የመከላከያ ሠራዊት ሕንጻ
የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (Ethiopian Unity and Freedom Force – EUFF) በጎንደር ጭርቆና በምትባለ በርሃ ላይ ከወያኔ አንድ ሻምበል ጦር ጋር ባደረግኩት ውጊያ 25 ወታደሮችን መግደሉን እና 11 ማቁሰሉን አስታወቀ።
የነፃነት ኃይሉ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “ከፌብሩዋሪ 25 እስከ 27 2013 ዓ.ም በአካባቢው የመንግስት አጨብጫቢ ሚሊሻዎች እየተመራ ወደ ነፃ መሬታችን በመምጣት ጥቃት ሊያደርስብን የመጣነውን አንድ ሻምበል ጦር አሳፍረን መልሰነዋል” ብሏል።
በአርማጭሆና በአይከል መካከል በምትገኘው ጭርቆና በረሃ ለ3 ቀናት በተደረገው ውጊያ ከመንግስት ወታደሮች 25 ሰዎች መሞታቸውን፣ 11 መቁሰላቸውን እና 3 ወታደሮችን መማረኩን ያስታወቀው የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (EUFF) ከራሱ ሠራዊትም 5 ወታደሮች በዚህ ውጊያ መሞታቸውን ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (Ethiopian Unity and Freedom Force – EUFF) ከወያኔ ጋር አትሥሩ በሚል ማስጠንቀቂያ ለሰጣቸውና ይህን ማስጠንቀቂያ አልሰማ አሉኝ ላለው ባለፈው ጃንዋሪ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በመተማ የወረዳው አስተዳዳሪ፣ የከተማው የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የከተማው የአቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ 18 ሰዎች በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ሕይወታቸው ወዲያዉኑ ሲያልፍ ሌሎች 4 ሰዎች መቁሰላቸውንና ለዚህም ኃላፊነቱን መውሰዱ ይታወቃል። ከዚህ ቀደም ይኸው ድርጅት “ከኢሕአዴግ ሥርዓት ጋር አትተባበሩ የሚል ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ላልሰሙ ደጋፊዎች ክምር ድንጋይ የሚባለው አካባቢ የነዳጅ ዘይት ማጠራቀሚያ ማጋየቱና፤ እንዲሁምጨጨሆ ላይ ላይ ደግሞ አውቶቡስ ማቃጠሉ መዘገቡ አይዘነጋም። አሁን የመንግስት አንድ ሻምበል ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ ይህን ኃይል ለማጥፋት ወደ ሠራዊቱ ነጻ መሬት (ጭርቆና በርሃ) በመሄድ ውጊያ የገጠመው ቢባልም፤ ከመንግስት ወገን በተለይም ወደ መከላከያ ሚ/ር ደውለን ይህንን ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። – See more at:http://www.zehabesha.com/
No comments:
Post a Comment