Translate

Wednesday, August 23, 2017

ይህ ስርዓት በፍጹም አይድንም! (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ
በጌታቸው አሰፋ እና በሳሞራ የኑስ መካከል ያለው ፍጥጫ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል። በሁለቱ አሽቃባጮች ማለትም በኃይሌ ገብራስላሴና በፕሮፌሰር ይሳሃቅ ኤፍሬም በኩል ተጀምሮ የነበረው የማስታረቅ ጥረት ሚስጥሩ በኢሳት በኩል ሾልኮ ከውቀጣ በኋላ ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም አሁን እንደገና በሁለቱም በኩል የተሻለ ተሰሚነት ሊኖራቸው ይችላል ተብለው በሚገመቱ ሙሉ ለሙሉ ከትግራይ በሆኑ የስርአቱ ሰዎች ሌላ የሽምግልና ጥረት እንደቀጠለ ነው።

ጸረ ሙስና በሚል ሽፋን ሰዎችን የማሰሩ ሂደት በሁለቱም ክንፍ በኩል ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ነገር ግን ጌታቸው አሰፋ ጉምቱ የሚባሉ ወታደራዊ ጀነራሎችን በማሰሩ በኩል ያልተሳካለት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ደርሶት ሂደቱ ቅርቃር ውስጥ ገብቷል። በአዋጅ ተቋቁሞ የነበረው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያለ አዋጅ ከፈረሰ ጥቂት ወራት ያስቆጠረ ሲሆን ለግዜው ከወታደራዊ ደህንነቱም ሆነ በጌታቸው አሰፋ ከሚመራው ብሄራዊ ደህንነት የሚላኩትን የሙሰኛ ስም ዝርዝሮች እየተቀበሉ ማሰሩ በጌታቸው አምባዬ በሚመራው አቃቢ ህግ ጽቤት ላይ የወደቀ እዳ ሆኖት አርፏል። በዚህ ሰአት ለሁሉም ግልጽ ሆኖ የወጣው አንድ ነገር ቢኖር ይህ ስርዓት የገባበትን አደገኛ ቀውስ ለመፍታት ምን ያህል አቅም እንዳነሰው; ይበልጡንም ቀኑ እየገፋ በመጣ ቁጥር አደጋው ከቁጥጥር እየወጣ መሄዱንና እስከዛሬ ያልተፈታ ችግር ቀን አልፎ ቀን በተተካ ቁጥር የበለጠ ውስብስብ እየሆነ መሄዱ ነው።ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ጨለማውን ከማውገዝ አንድ ሻማ ማብራት አዋቂነት ነው። “ጠላትህን ወንዝ ሲወስደው ካየህ አንድ ጠብታ ምራቅም ቢሆን እንትፍ” በል የሚለውን ያባቶች ይትበሃል ገንዘብ እናድርግ።

No comments:

Post a Comment