Translate

Friday, August 18, 2017

አልገብርም ሲል እንደመንግስት አላውቅህም ነው (ዳዊት ዳባ)

Small business owners strike in Ethiopia
አገዛዙ የቀረው በቀጣይ የሚለንም “ፋታ ስጡኝ” ነው። ህዘብ እያደረገ ያለው ትግል አገዛዙን ጨርሶ ሽባ አድርጎታል። ፍፃሜውን ለመስራት ድረስ  ጉልበታም ነው።  ከሁለት ከሶስት አመት  በፊት  ቁርጠኝነት፤ ጨዋነትና ውስብስብነት ያለውን ይህን አይነቱን  ትግል የበዛነው ምን አልባት “በተአምር ከሆነ” ብለን ስናስበው የነበረ ነው። የዚህ አባዜ አሁንም ምልከታችን ላይ ጋሬጣ የሆነ ይመስላል። ትግሉ በሚያሻው ሙሉ ትኩረትን፤ እገዛንና ገለፃን እያገኘ አይደለም።
  አርቲ ብርቲና ሊተገበር የማይችል ወይ በይለፍ ልንጨነቅበት ይገቡ የነበሩ ቁም ነገሮችን መቀነስ አልቻልንም። የተፈጠረውን አጋጣሚ ባግባቡ ተጠቅመን ላንዴና ለመጨራሻ ጊዜ ነፃነታችንን የምናውጅበት መላ ላይ ሙሉ አቅምና ትኩረታችንን ከማድረግ ይልቅ ይቆም ይሆን በሚለው ስጋት ተቀስፈናል። መሽቶ በነጋ ቁጥር ዛሬስ ቀጥሏል? ብሎ መጠየቅን ሞያ አድርገንዋል። ለበዛነው ምክንያቱ ጉጉትና ጭንቀት ቢሆንም በዝቷል። ብዙ ሊደረግና ሊባል በሚገባው ጊዜ ላይ ይህ አስተሳሰብ ቀፍድዶናል። በለውጥ አቀንቃኙ በኩል መፋዘዝ መስሏል።
አላማው ግልፅ ባይሆንመ አንዳንዶች ህዘብ የጀመረውን ትግል  ቆሟል ብሎ ለማወጅ ዳር ዳር ሲሉ ሁሉ ይታያል። እውነታው ትግሉ በተጠናከረ መንገድ ቀጥሏል። ይህን እየፃፍኩ ደንቢዶሎና ጊነቢ ላይ ህዝብ ለአራተኛ ቀን ከተማውን ዘግቷል። ይህን አይነት ትግል ካደባባይ ተቃውሞዎች በላይ ያገዛዙን ፍፃሜ ከመስራት አኳያ ጉልበታም ነው። ቄሮዎች ያስተባብሩት፤ በብዛት ኦሮሚያ ውስጥ ይካሄድ እንጂ ኦሮሞዎች ብቻ እየታሰተፉበት ያለ ትግል በጭራሽ አይደለም። የወጣቶችና የተማሪዎች ብቻም አይደለም። እየተሳተፈበት ያለው የማህበረሰብ ክፍልም ሰፍቷል። ምርቱን ለከተሞች ከሚያቀርበው ገበሬ አንስቶ ጉልት የምትሸጠዋ እናት። ከተማው ውስጥ ካሉ ትላልቅ ነጋዴዎች አንሰቶ መንገድ ላይ ቸርችረው ሂወታቸውን የሚገፉ ዜጎች ደርሻ እያደረጉበት ያለ ትግል ነው። ይህን አይነት ፍፁም ሰላማዊ ጨዋነትና እርጋታ የሚታይበት ውስብስብ ትግል አይደለም እኛ አገር ሌሎች አገሮችም ዘነድ ብዙ ምሳሌ ልናቀርብበት የማንችለው ነው። አገዛዙን እንደገና የጅምላ እስር ውስጥና ህዘብን እርስ በርስ ማጋጨት ውስጥ ለምን ተመልሶ የገባ ይመስለናል።  ትግሉ እንደቁንጫ አሽቶ አሽቶ ግብአተ ሞቱን አይቀሬ ስላደረገው ነው።
ህዝብ ተቸግሮ አደባባይ እየወጣ መንግስት የለም ወይ እያለ ሲጮህ አቤት ማለት ሲገባ ረበሻችሁ፤ አሸበራችሁ እያለ ግማሹን ሲገል ከፊሉን በየእስር ቤቱ ሲያጉረው ከርሞ በተራው እንደመሸበት የሲጋራ ሱሰኛ ባለሱቅ፤ እረ ባለሱቅ- እረ እባካችሁ ክፈቱ እንጂ እያለ ካንዱ ሱቅ ወዳንዱ እየዞረ ልመናን ይዟል። ከተቻለ ቅሬታችሁን በየግል አሰሙ በሚል ልፈፋና ሱቅ በማንኳኳት እንቢተኛነቱን ለማክሸፍ እየሞከሩ ይመስላል። ነጋዴው መኖራያው ነው። ምን ያህል ቀን ይዘጋል። እቅድ ቢጤም ነበረች።  የዚህ አይነቱ አገዛዙ ከህዝብ ጋር እልህ ውስጥ የሚገባበት ነገር ነው ህዘቡን ሀሞተ መራር ያደረገው። ጅሎች ህዝብ የሚመዘው ያልቅበት ይመስላቸዋል። በአንድ ሆኖ ማድረግን እንደው አውቀቆበታል። ከፍቶ ስራውን ቢጀምርና ባይከፍልስ ምን ለማምጣት ነው?። ይህም ብቻ አይደለም ነጋዴው ቢፈልግም እንኳ ህዝብ መሸጥ ከፈለክ ያለ ቫት ሽጥ ማለትና ማስገደድ ሊጀምር ይችላል። ጉዳዩም ወደዚህ የሚሄድ ነው የሚመስለው።

No comments:

Post a Comment