Translate

Saturday, February 27, 2016

Breaking: የቴዲ አፍሮ የአዲስ አበባ ኮንሰርት ተከለከለ – ለምን? ዝርዝር አለን

teddy afro 2
(ዘ-ሐበሻ) የፊታችን ቅዳሜ ማርች 5, 2016 በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል ሊደረግ የነበረው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ተከለከለ፡፡
በመላው ኦሮሚያ እንዲሁም በአማራው ክልል በተለይም በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ውስጥ ውጥረት ውስጥ የገባው ኢሕ አዴግ መንግስት ጦሩን ወደ ኤርትራ ድንበር ካስጠጋና እንደዚሁም ደግሞ በኦሮሚያ በ8 ዞኖች ከፋፍሎ ወታደራዊ አስተዳደር ካወጀ በኋላ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሕዝብ አመጽ ይነሳል በሚል ምክንያት የተለያዩ ዝግጅቶችን በመሰረዝ ላይ ይገኛል::




ለቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ተበትኖ የነበረው ፍላየር
ለቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ተበትኖ የነበረው ፍላየር

ምንጮቻችን እንደገለፁልን ይህን ኮንሰርት ለመስራት ቴዲ በ1.3 ሚሊዮን ብር የተዋዋለ ሲሆን በርካታ ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው ነበር፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ይነሳል በሚል በመንግስት ደህንነቶች በመፈራቱና በተለይም የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሕዝብን በአንድ ላይ ያገናኛል በሚል ፍራቻ ኮንሰርቱ መሰረዙን የደህንነት ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
ለቴዲ አፍሮና አዘጋጆቹ ሐበሻ ዊክሊ ኮንሰርቱ ተከልክሏል ተብሎ የተነገራቸው ከዚህ የተለየ እንደሆነ ያስታወቁት ምንጮች ኮንሰርቱ መከልከሉን ያስተዋለው ቴዲ የቀጣይ አልበሙን ስራ ለማጠናቀቅ ወደባህር ዳር አምርቷል፡፡ የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ለፋሲካ በአል እንደሚወጣ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
ቴዲ አፍሮ በአዲስ አበባ ኮንሰርት ለማድረግ ፈልጎ ከዚህ ቀደም በጸጥታ አስከባሪዎች እጥረት የተነሳ በሚል ሰንካላ ምክንያት መከልከሉ አይዘነጋም::

No comments:

Post a Comment