Translate

Monday, February 22, 2016

በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የቀረበው ሃሳብ በሕወሓት ውድቅ ተደረገ::

Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የወያኔን ትንፋሽ በጣረ ሞት የሸበበው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ቀጥሏል::በተለያዩ ወረዳዎች የቀጠለው ተቃውሞ ሕዝቡ በወያኔ አገዛዝ የሚደረግበትን የፖለቲካ ጫና የኢኮኖሚ በደል እና ወታደራዊ እርምጃዎች በመቃውም ተቃውሞውን ለማሰማት አደባባይ የወጣ ሲሆን በየአከባቢው መንገዶችን በመዝጋት ለለውጥ ያለው ቁርጠኝነት በትግሉ እያሳየ ይገኛል::በተለየ ሁኔታ በሃረርጌ ጉራዋ በዳዋ አከባቢ እንዲሁም በበደኖ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በዳዋ ያሉ ነዋሪዎች የአግኣዚ ሰራዊት ወደ በደኖ ዘልቆ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ ድልድዩን በመዝጋት የመግባት አላማውን አጨናግፈውበታል::

በሻሸመኔ በአምቦ በወለጋ ቀለም ወረዳ በተከታታይ የሚደረጉት ተቃውሞዎች በዛሬው እለት ቀጥለው የዋሉ ሲሆን በጉጁ በተደረገው የቦኮ የአገር ሽማግሌዎች በየ8 አመቱ የሚፈጸመው የመሪዎች ሽግግር ክብር እንግዳው አሻንጉሊቱ ሙላቱ ተሾመ የተባለው የወያኔ ሹም ፕረዚዳንት ሲሆን በከፍተኛ የደህንነት እና ወታደራዊ ኮማንዶዎች አጀብ ተከቦ ውሏል::ርእሰ መስተዳደሩ ሙክታር ከድር ለሕክምና ባንኮክ ነው ይባል እንጂ ምናልባት በቁም እስር ላይ ሊሆን ይችላል የሚሉ የደህንነት ማስረጃዎች ቢገኝም በአይነቁራኛ ስር ሆኖ ከአስቴር ማሞ ጋር በበዓሉ እንዲታደም መደረጉ ተጠቁሟል::የአግኣዚ ወታደሮች አብዛናው የኦሮሚያ ክልል ከተሞችን ከበው እጥረት ለመፍጠር ቢሞክሩም ሕዝቡ ያለውን አቋም ዝንፍ ሳያደርግ በተቃውሞ ትግሉን ገፍቶበታል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የኦሕዴድ ከፍተኛ አመራር ሁለት አባላት በወይዘሮ አስቴር በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ሃሳብ አሻንጉሊዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ሳይደርስ በደህንነት ሹሙ በአላቃ ጸጋይ ውድቅ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል::ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ኦሮሚያ የጦርነት ቀጠና ትሆናለች ያሉ አመራሮች ከሕወሓት የተሰጣቸው መልስ ግን ልክ እናስገባቹሃለን የሚል ነው::ከባለፈው ግምገማ በኋላ በሕወሓት እና በኦሕዴድ አመራሮች መካከል ከፍተኛ የከንፈር መነካከስ እንዳለ ሆኖ አለመተማመኑ እና በጥርጣሬ መተያየቱ ስብሰባዎችን እየወገኑ መጥራት እና የማይፈለጉ አባላትን ማግለል እና ማስደንገጥ በሕወሓት እየተፈጸመ መሆኑ ሲገለጽ ተቃውሞውም እየጋለ መምጣቱ ታውቋል::ሕወሓት በአሁን ወቅት ተቃውሞ በርዶ የክልሉን ባለስልጣናት በሰበብ በማሰር በማባረር እና በመበታተን በመፐወዝ ካድሬዎችን አዳዲስ ኦሮሚኛ በተማሩ የሕወሓት ሰዎች በመተካት አዲስ የጭቆና ስልት ለማስፈጸም ዝግጅት እያደረገ ይገኛል::ኦሮሚያ በከፍተኛ ደረጃ በተቃውሞ ባለችበት በዚህ ወቅት ላይ የአግኣዚ ጦር የዘር ማጥፋት ስራ ላይ ተሰማርቶ ባለበት በዚህ ቀውጢ ሰአት ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አላውጅም ሲል ወያኔ ማገዱ ለሕዝብ ሕይወት ደንታ ቢስነቱን ከማሳየቱም በላይ ተቃውሞውን አቅልሎ ለማሳየት መሞከሩ የባሰ እያጋጋለው እንደመጣ ታውቋል::

No comments:

Post a Comment