Translate

Wednesday, May 6, 2015

ምርጫ ቦርድ ኢሕአዴግ ለፌዴራል ምርጫዉን እንዳሸነፈ አረጋገጠ – የሚሊዮኖች ድምጽ

ከሁለት ሳምንታት በኋላ ምርጫ ይደረጋል። ሆኖም ከምርጫው በፊት ኢሕአዴግ እንዳሸንፈ ምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ ላይ ባስቀመጠው ሰነድ አሳወቀ።
አርባ ሰባት የሚሆኑ ድርጅቶች እንደሚካፈሉ ምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን አርባ አምስት የሚሆኑት ለፌዴራል ፓርላማ ተወዳዳሪዎች አሰልፈዋል።

መንግስት ለመቆጣጠር አንድ ድርጅት 274 የፓርላማ መቀመጫዎችን ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ምርጫ ቦርድ ባሰፈረው ሪፖርት መሰረት፣ ኢሕአዴግ ለ501 የፓርላማ መቀመጫዎች ተወዳዳሪዎች ያሰለፈ ሲሆን (በደቡብ ክልል፣ በአማራዉ ክልል፣ በትግራይ እና በአዲስ አበባ በሙሉ) ፣ በሌሎች ክልሎችም የራሱ አጋር ደርጅቶች በስፋት እንዲወዳደሩ አድርጓል። (በነገራችን ላይ መድረክ በአማራው ክልል ዜሮ ተወዳዳሪዎችን ነው ያሰለፈው)
በመቀጠል በሰንጠረዡ የተቀመጠው መድረክ ነው። መድረክ 270 እጩዎችን ብቻ ነው ያሰለፈው። ሁሉንም መቀመጫዎች ቢያሸንፍ ውንኳን፣ መድረክ መንግስት የመሆን እድል የለውም። 165 መቀመጫ ብቻ ያሰለፈው ኢዴፓም እንደዚሁ። ስለዚህ በሂሳቡ ስሌት መሰረት ( ማቴማቲካሊ) ምርጫዉን ኢሕአዴግ እንዳሸነፈ ምርጫ ቦርድ ከወዲሁ አረጋግጧል ማለት ነው።
የሰማያዊ ፓርቲ 139 የፓርላማ ተወዳዳሪዎችን ብቻ ያሰለፈ ሲሆን፣ በአየለ ጫሚሶ የሚመራው ቡድን 108 ተወዳዳሪዎችን አሰልፏል።
በአቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራው አንድነት፣ ከ500 በላይ የፓርላማ ተወዳዳሪዎች ለማሰለፍ ተዘጋጅቶ እንደነበረ ይታወቃል። ሆኖም ምርጫ ቦርድ ከሕወሃት የተሰጠውን የፖለቲካ ዉሳኔ በመቀበል፣ በትግስቱ አወሉ የሚመራ ተለጣፊ አንድነትን በመመስረት፣ ጠናካራዉን ድርጅት፣ ሕጋዊ እውቅና በመፈቅ ከጨዋታ ዉጭ አድርጓል። አሁን ተለጣፊው (ድንኩ) አንድነት 92 ተወዳዳሪዎች ብቻ ነው ያሰለፈው።
አንድ ወቅት ጠንካራ የነበረ መኢአድም በመካከሉ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከ78 የበለጠ ተወዳዳሪዎች ማሰለፍ አልቻለም።

No comments:

Post a Comment