የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጉዳይ ፤ ለ15 ሰዓታት እንደተገመገሙ ተገለጸ
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ላለፉት ሁለት አመታት ሕወሃትን በታማኝነት ሲያገለግሉ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። ከጅምሩ አንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሲሞት፣ ቦታዉን የሚይይዘው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ ነበር። አቶ መለስ ሲሞቱ ምክትል ጠ/ሚኒስተር የነበሩት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስተር ለማድረግ ፓርላማ ቀጠሮ ያዘ። ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስተር መባል ጀመሩ። አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠ/ሚኒስተር እንደሚሆኑም ተገለጸ።
ሆኖም ሕወሃቶች ተቃወሙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚመርጠው ፓርቲው እንጂ ፓርላማው አይደለም አሉ። በዚህም ምክንያት አቶ ኃይለማሪያም ጠ/ሚኒስትር እንዳይሆኑ ብሎክ አደረጉ። አቶ ኃይለማሪያም ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር መባላቸው ቀረና ምክትል ጠ/ሚኒስተር ወደ መባል ተመለሱ። ሕወሃቶች ከነርሱ ዉጭ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እንዲያዝ አይፈልጉምና የነርሱን ሰው ለማስቀመጥ ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ። ወ/ር አዜብም ከቤተ መንግስት አልወጣም አሉ። አቶ ኃይለማሪያም በዚህ ምክንያት ሌሊት በጠዋቱ እየወጡ ማታ ነበር ወደ ስራቸው የሚሄዱት።
አቶ ኃይለማሪያምን በቅርበት ለመከታተል፣ አቶ ጸጋዬ በርሔ እና አባይ ጸሃዬ የጠቅላይ ሚኒስተር አማካሪ ሆነው እንደሚሾሙ፣ አቶ ድበረ ጽዩን ደግሞ ፣ ከአቶ ደመቀ መኮንን እና ዘረኛ የኦሮሞ አክራሪውና የአናሌና ጨለንቆ የጥላቻ ሐዉልት አስገንቢው ሙክታር ከድር ጋር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር እንደሚሆኑ፣ ዶር ቴድሮስ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት እንደሚሰሩ ስምምነት ሲደረስ፣ ሕወሃቶች የአቶ ኃይለማሪያምን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተቀበሉ። (በነገራችን ላይ ለአቶ ደመቀ እና ለዶር ቴድሮስ አክብሮት አለኝ)
አቶ ኃይለማሪያም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ እንደመሆናቸው፣ ሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በሕግ ለርሳቸው ተጠያቂ ቢሆኑም፣ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችን አቶ ኃይለማሪያም እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒትሰሮች ተከፋፍለው እንዲመሩ ተደረገ። ቁልፍ ፣ ቁልፍ መስሪያ ቤቶች ለአቶ ደብረ ጽዩን ተሰጡ። ሲስተማሪክ በሆነ መልኩ ህወሃቶች የአቶ ኃይለማሪያም ስልጣን ገፈፉ። የረቀቀ መፈንቅለ መንግስት ይሉታል ይሄ ነው !!

አቶ ኃይለማሪያም «አቶ መለስ በጣም ወዳጄ ነበር። ያምነኝ ነበር። እነርሱ ግን ምንድን ነው ችግራቸው ? » በሚል ሕወሃቶች ለማስደሰትና የነርሱን አመኔታ ለማግኘት ተግተው መስራት ጀመሩ። በንግግራቸውም ሆነ በስራቸው እንደመለስ ዜናዊ ለመምሰል ብቻ ሳይሆን ከአቶ መለስ ዜናዊ በልጦ ለመታየት በጣም ተጉ። ሆኖም ሕወሃቶች የተደሰቱ አይመስልም። እንደዉም የበለጠ ናቋቸው። አቶ ኃይለማሪያምን አሸቀንጥረው በመጣል የራሳቸውን ሰው ጠቅላይ ሚኒስተር ለማድረግ እየተዘጋጁ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ይገመታል።
ፓርቲ ከፈለገ ሊስትሮም ለመሆን ዝግጁ ነኝ በማለት ራሳቸው ሙሉ ለሙሉ ለሕወሃቶች ፍቃድ ባርያ ስላደረጉ ፣ አቶ ኃይለማሪያም ከጠቅላይ ሚኒስተርነት ቢነሱ ብዙ ተቃዉሞ የሚያስነሱም አይመስሉም። «አንድ ሰበብ ፈጠረህ ራስህን ከ እጩነት አዉጣ። አንድ አገር አምብሳደር ሆነህ ትሾማለህ። አርፈህ ኑሮህን ኑር» ይሏቸዋል አለ። ብዙም ሕወሃቶች አቶ ኃይለማሪያም ምን ይላሉ ብለው አይጨነቁም።

ይልቅ ሕወሃቶች በሕዝብና በሌላው ተቃዉሞ እንዳይነሳባቸውም ነው ትልቁ ስጋታቸው። ለዚህም አስቀድመው የተዘጋጁበትን ሲሰሩበት የነበረ ነገር አለ። ላለፉት ሁለት አመታት አቶ ኃይለማሪያም እንዲጠሉና ዶር ቴድሮስ እንዲወደዱ ለማድረግ ሲሰሩ ነበር። ይሄም የተሳካላቸው ይመስላል። አሁን ለምሳሌ ከሊቢያ ወገኖቻችን ካይሮ ሲገቡ የግብጽ መሪ ፕሬዘዳንት ኤል ሲሲ ነበር አይሮ ፕላን ማረፊያ ሄደው የተቀበሏቸው። አዲስ አበባ ሲመጡ ግን ቦሌ የሄዱት አቶ ኃይለማሪያም አልነበሩም። ዶር ቴድሮስ እንጂ። አቶ ኃይለማሪያም ስላልፈለጉ አይመስለኝም። እነ አባይ ጸሐዬ አቶ ኃይለማሪያም ምንም አይነት በሕዝብ ዘንድ «ጥሩ ሰሩ፣ ጥሩ ተናገሩ፣ ጥሩ አደረጉ» የሚባል ነገር እንዲኖር ስለማይፈለጉ፣ ሆን ብለው አግደዋቸው ሳይሆን እንደማይቀር ነው የማስበው።
ለማንኛውም የሚከተለውን የኢሳት ዘገባ ያንብቡ። ፀሐይ ልትጠልቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሯት አቶ ኃይለማሪያም ከሕወሃቶች ጋር ግብግብ ሳይጀመሩ እንዳልቀረ ነው። እራሳቸው ሕወሃቶች ብቃት እንዳይኖራቸው አድርገው፣ አቶ ኃይለማሪያምን ብቃት የለህም እያሉ እንደሆነ ነው ዜናው የሚናገረው።
No comments:
Post a Comment